Login
Federal Supreme Court of Ethiopia
Search
  • Home
  • About Us
    • President Message
    • President
      • Current President
      • Former President
    • Vice President
      • Current Vice President
      • Former Vice Presidents
    • History and Traditions
    • Judges
      • Former Judges
    • Vision Mission and Mandate
    • Judicial Administration Council
  • Court Services
    • Registry Services
      • Court Forms and Fees
    • Daily Court Trial Schedule
    • Case Tracker
    • Requesting Court Documents
      • Disposed Cases
    • Court Annexed Mediation
    • Interpretation Services
    • Legal Support
      • Child Justice Project Office
      • Public Defenders Office
  • Going to Court
    • Visiting the Court
      • What Can I see and Do?
    • Courtroom Etiquette
      • Courtroom Rules
    • Criminal: Information for the Accused Person
    • Civil Disputes: Information for Parties
    • Representing Yourself
    • Information for Witness
    • Information for Lawyers
    • FAQ
  • Digital Law Library
    • Annual Reports
    • State of the Judiciary
    • Monthly Judges Seminar
    • Federal Laws
    • Archives
    • Publications
      • Journal
      • Federal Cassation Decision Series
      • Newsletter
    • Judgments
      • Cassation Decisions
      • Supreme Court Decisions
  • News Media
    • Announcements
    • Interactives
      • Photos
      • Video
    • Services for Media
      • Press Releases
      • Press Conference
      • Media Advisories
      • Speeches
    • NEWS
  • Contacts
    • Federal Supreme Court
    • Federal High Court
    • Federal First Instance Court
    • Contact and Feedback
  • Tender
  • Judgement Execution Directorate
    • About Judgement Execution Directorate
    • Auction
  • Vacancy
  • Child Justice Project

አቶ ቀኖ ኩታሳ እና ወ-ሮ መሳይ ገመቹ የሰ-መ-ቁ 180936

Wednesday, October 7, 2020 18712

ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 303340 በ11/10/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት በ11/11/11ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡የጉዳዩ አመጣጥ የአሁን ተጠሪ በስር በጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የኖኖ ቤንጃ ወረዳ ፍ/ቤት በአሁን አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በክሱ 1ኛ እና 2ኛ ተራ ቁጥር ላይ የተጠቀሰው ስፋቱ እና አዋሳኙ የተጠቀሰው አንድ ባር ሳር ቤት ግምቱ ብር 4000(አራት ሺህ ብር) የሚያወጣ አለን፤ በክሱ ከተራ ቁጥር 3  እስከ 47 የተጠቀሱትን ንብረቶች አመልካች ድርሻዬን እንዲያካፍለኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው አመልካች ባቀረቡት መልስ ከተጠሪ ጋር የኖርነው አስር ወር ብቻ ነው፤ ክስ የቀረበባቸውን ንብረቶች ከቀድሞ ሚስቴ ወ/ሮ ያደሺ ያንካ ጋር ከ1990ዓ.ም ጀምረን ያፈራናቸው ንብረቶች ተጠሪን አይመለከትም፤ ተጠሪ ያላት ንብረት የቤት ውስጥ እቃ ብቻ ሲሆን እነሱም በተራ ቁጥር 12፤13፤14፤15፤19፤20፤23፤24፤26፤27 ሲሆኑ ያልተመዘገቡ ንብረቶች ደግሞ በተራ ቁጥር 3፤4፤5፤6፤16፤18፤21፤22፤25፤28፤29፤30፤31፤35፤36፤46 ሲሆኑ በተራ ቁጥር 46 ላይ የተጠቀሰው ኑግ የለም፤ በተራ ቁጥር 6 ላይ የተጠቀሰው በሬ የቀድሞ ሚስቴ ንብረት ነው፤ በተራ ቁጥር 45 ላይ  የተጠቀሰው ንብረት ተጠሪን ሳላገባት በፊት በ2007ዓ.ም ውስጥ ከቀድሞ ሚስቴ ጋር የገዛነው ነው፤ በተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ የተጠቀሰውን ንብረት አመልካችን ሳላገባት በፊት በ2007ዓ.ም ከቀድሞ ሚስቴ ጋር አፍርተን የባለቤትነት ማስረጃ ስላለን ተጠሪን አይመለከትም፤ በተራ ቁጥር 47 ላይ ተጠሪ የገለጸችውን ቤት በ2007ዓ.ም ከቀድሞ ሚስቴ ጋር ያፈራነው ስለሆነ ተጠሪን አይመለከትም፤ በ27/1/10ዓ.ም የተፈጸመው ውል ደግሞ ተጠሪ የገጠሩ ኑሮ አቅቶኛል ወደ ከተማ አስገባኝ ብላ በሽማግሌ ስለጠየቀችኝ ያደረኩት ውል እንጂ የሰጠኋት ስጦታ የለም፤ ስጦታ አልተሰጠም እንጂ ተሰጥቷል ቢባል እንኳን በመካከላችን የነበረውን አለመግባባት ለመፍታት የተፈጸመ ውል ስለሆነ ውሉ እንዲፈርስልኝ ፤ በ29/8/09ዓ.ም የተፈጸመውን ውል ደግሞ የቀድሞ ሚስቴን ሳላማክራት የፈጸምኩት ውል ስለሆነ  ከቤተሰብ ህጉ የሚቃረን ውል ስለሆነ ውድቅ እንዲደረግልኝ በማለት የተከራከሩ ሲሆን፤  በስር ጣልቃ ገብ የሆኑት ወ/ሮ ያደሺ አንካ (አሁን በሰበር አቤቱታው ላይ የሌሉ) በጣልቃገብነት ገብተው እንዲከራከሩ ተፈቅዶላቸው ባቀረቡት አቤቱታ ከአመልካች ጋር በ1990ዓ.ም ጋብቻ መስርተን አንድ ልጅ እና ንብረት አፍርተን እያለ አመልካች እና ተጠሪ ጋብቻ ፈጽመው ጋብቻቸውን አፍርሰው ወደ ንብረት ክርክር ሲሸጋገሩ ተጠሪ ከአመልካች ጋር ለአስር ወራት ብቻ የኖረች ሲሆን በተራ ቁጥር 1፤2፤6፤7፤8፤9፤10፤11፤31፤32፤33፤34፤37፤38፤39፤40፤41፤42፤43፤44፤45፤47 ላይ ተጠሪ የጠቀሰችው ንብረት እኔ ያፈራሁት ንብረት ስለሆነ ከክርክሩ ይውጣልኝ፤ በ29/8/10ዓ.ም የተደረገውን  የስጦታ ውል በተመለከተ አመልካች ከጣልቃገብ ፍላጎት ውጪ የጋራ ንብረታችን የሆነውን ለ3ኛ ወገን ለማስተላለፍ መብት የሌለው በመሆኑ ውሉ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡..........

Read more

አቶ ጉዕሽ ሃይሉ ደሞዝ እና ወ-ሮ ፅጌ ገ-ሂወት የሰ-መ-ቁ 180326

Wednesday, October 7, 2020 16668

ይህ የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ክርክር የተጀመረዉ በመቐለ ከተማ በ02 ቀበሌ ማህበራዊ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ተከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ  የሥር ከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.115041 በ12/09/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።የአሁን ተጠሪ በቀበሌ ማህበራዊ ፍ/ቤት ባቀረበችዉ ክስ ከአመልካች ጋር ያለን ጋብቻ እንዲፈርስ፣ ትዳር ሲንመሰርት በባንክ ወደ አመልካች የሂሳብ ቁጥር ገቢ ያደረኩኝ ገንዘብ እንዲከፍለኝ፣ ለጥሎሽ ከሚገዛ ወርቅ ቀንሶ የወሰደዉ ብር 8190 እንዲከፍለኝ በማለት ዳኝነት ጠይቃለች፣ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ ዘርዝራለች።የአሁን አመልካች በዚህ ክስ ላይ ባቀረበዉ መልስ ተጠሪ ይህን ገንዘብ ለመጠየቅ መብት የለትም፣ ትዳር ሲንፈጽም ባደረግነዉ ዉል እኔም ገንዘብ በመግጠም በመቐለ ከተማ 16 ቀበሌ ዉስጥ የአልኮል ማከፋፈያ ከፍተን ኪራይ ብር 6000 ስንከፍል ቆይተን ስምምነት ስናጣ አሁን ለዋርድያ ብር 500 እየከፈልን እየተጠበቀ ስለሆነ ለትዳር መግጠሚያ ያቀረበችዉን ገንዘብ መጠየቋ ተገቢ አይደለም፣ በትዳር ዉስጥ ትርፍም ኪሳራም የጋራ ነዉ፣ ይህ ንብረት ተቆጥሮ በገንዘብም ሆነ በዓይነት እንዲንካፈል በማለት ተከራክሯል፣ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ ጠቅሷል።…………

Read more

አቶ ወንድማገኝ መንግስቱ ማሞ እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ-መ-ቁ 191629

Tuesday, October 6, 2020 17287

ይህ የሰበር ጉዳይ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለው ተጠሪ በአመልካች ላይ 3 የወንጀል ህግ ድንጋጌዎችን በመጥቀስ ተደራራቢ  ወንጀል ፈፅሟል በማለት ያቀረበው ክስ በደቡብ ክልል ኮንታ ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን መርምሮ በ 2 ድንጋጌ ጥፋተኛ በማድረግ በ 11 ዓመት ፅኑ እስራት እና በብር 5,000.00  እንዲቀጣ የሰጠው ውሣኔ በይግባኝ ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመቅረቡ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ቅጣቱን በማሻሻል በ 7 ዓመት ከ 8 ወር ፅኑ እስራት እና በብር 2,500.00  እንዲቀጣ ሲወሰን ለክልሉ ከ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ሁለቱን ድንጋጌ በመተው በወንጀል ህግ አንቀፅ 543/3 ስር ብቻ ጥፋተኛ በማድረግ 5 ዓመት ፅኑ እስራት እና በብር 1,000.00 የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የፈፀመ በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ ሲል አመልካች የሰበር አቤቱታ በማቅረቡ መነሻነት ነው፡፡የጉዳዩን አመጣጥ እንዲህ ነው፡፡…….

Read more

አቶ ኢሳያስ አድማሱ አለማየሁ እና ወ-ሮ አልማዝ ተድላ ደስታ የ-ሰ-መ-ቁ 183547

Tuesday, October 6, 2020 16580

 ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት መናገሻ ምድብ 2ኛ ፍ/ብሄር ችሎት በኮ.መ.ቁ 62214 በ13/3/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ፤ የፌ/ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ 230102 በ28/10/11ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ ቅር በመሰኘት በ7/1/12ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡የጉዳዩ አመጣጥ አመልካች በስር የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ ሟች አባቴ አቶ አድማሱ አለማየሁ በ29/10/03ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ አመልካችን ከወራሽነት የነቀለ እና የወራሽነት ድርሻ የሌለኝ ያደረገ ስለሆነ ይህ ኑዛዜ ተሰርዞ በፍ/ብ/ህ/ቁ 842(1) መሰረት ከሌሎች ወራሾች እኩል ድርሻ ያለኝ መሆኑ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው 1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሟች ህጋዊ ሚስት ስሆን ወራሽ ባልሆን ከሚስት እና ከባለቤቴ ንብረት ድርሻ ግማሹ(50%) የኔ መሆኑ እስከታወቀ ከሌሎች ወራሾች ጋር መከሰስ የሌለብኝ በመሆኑ፤ አመልካችም ከ1ኛ ተጠሪ የሚፈልገው መብት እና ጥቅም ስለሌለ ክሱ በ1ኛ ተጠሪ ላይ መቅረቡ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 33 መሰረት ተቀባይነት የለውም የሚል ሲሆን፤ ተጠሪዎች በጋራ ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሟች አቶ አድማሱ አለማየሁ ግንቦት 29 ቀን 2003ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ በአርባ ቀን መታሰቢያው የካቲት 5 ቀን 2009ዓ.ም ሲነበብ አመልካችም በአካል ተገኝቶ የሰማ በመሆኑ ይህን ደግሞ መቃወም የሚችለው በፍ/ብ/ህ/ቁ 973(2) በ15 ቀን ውስጥ ብቻ ሲሆን አመልካችም ለሽምግልና ዳኞች ይህን ያላደረገ በመሆኑ፤ በአንቀጽ 973(2)(3) መሰረትም እስከ 3 ወር ግዜ ውስጥ ያላቀረበ በመሆኑ ክሱ በፍ/ብ/ህጉ እና በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 244(2)(ለ) መሰረት በይርጋ ቀሪ ነው በማለት የተከራከሩ ሲሆን፤ ፍ/ቤቱም በመቃወሚያዎቹ ላይ ክሱን ከሰማ እና የግራቀኙን ምስክሮች ቃል ከሰማ በኋላ አመልካች ኑዛዜው ሲነበብ ሰምተዋል ወይስ አልሰሙም? ያልሰሙ ከሆነ የአመልካች ክስ በይርጋ የሚታገድ ነው ወይስ አይደለም? የሚሉትን ጭብጦች በመያዝ ጉዳዩን መርምሮ የአመልካች ምስክሮች በሰጡት ቃል አመልካች ኑዛዜው ሲነበብ በቦታው እንዳልነበሩ እና በእለቱም አብረው መዋላቸውን ገልጸዋል ይሁን እንጂ የአመልካች እናት አመልካች የ40 ቀን መታሰቢያው ቦታ እንዲሄድ በምስክሮች በኩል ያደረጉ ቢሆንም አመልካች ግን ሳይሄድ እንደቀረ መስክረዋል፤ የተጠሪዎች ምስክሮች በበኩላቸው አመልካች የሟች አባቱ የ40 ቀን መታሰቢያ ቀን የካቲት 5 2009ዓ.ም እዛ እንደነበር ፤ የኑዛዜው ኮፒ ለአመልካች እንደተሰጠ እና ስሙም በሄኖክ አድማሱ በሚባል ተራ ቁጥር 13 ላይ የሰፈረ ነው፤ የአመልካች ስም በሄኖክ አድማሱ ስም እንደሚታወቅ ለዚህም ማሳያ የአመልካች እናት የአመልካች ስም ሄኖክ ነው ማለታቸውን 1ኛ ምስክር መስክረዋል፤ አመልካች ጠዋት 1 ሰአት ጀምሮ እዛ እንደነበር እና የኑዛዜው ድርሻ አንሶኛል ያለውም ከ1 ወር በኋላ ነው በማለት በመመስከራቸው ከግራቀኙ ምስክሮች ቃል አመልካች ኑዛዜው በሚነበብበት ወቅት ቦታው የነበረ መሆኑን የተጠሪዎች ምስክሮች ከአመልካች ምስክሮች በበለጠ እና በአሳማኝ መልኩ በመግለጻቸው የፍ/ብሄር ህግ አንቀጽ 973(2) (3) ከደነገገው አንጻር ኑዛዜው የተነበበው የካቲት 5 ቀን 2009ዓ.ም ሲሆን የአመልካች ክስ የቀረበው በ22/12/09ዓ.ም በመሆኑ ይህም ሲቆጠር ከ15(አስራ አምስት) ቀናት በኋላ ብሎም ከ3(ሶስት) ወር በኋላ በመሆኑ ፤ አመልካችም በኑዛዜው ላይ ስማቸው እስከሰፈረ ድረስ የፍ/ብ/ህ/ቁ 939 ከደነገገው እና የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 36604 እና 53223(ቅጽ 8 እና 12) ከሰጣቸው አስገዳጅ ውሳኔዎች አንጻር ከኑዛዜው ተነቅያለሁ የሚባልበት አግባብ የለም ስለሆነም ክሱ በፍ/ብ/ህ/ቁ 973(1) እና 244(2) (ረ) መሰረት በይርጋ ይታገዳል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፌ/ከ/ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱም በሰጠው ትእዛዝ ይግባኙን ሰርዞታል፡፡……….

Read more

ወ-ሮ ገነት ገሠሰ ቸኮል እና የአ.አ ከተማ የየካ ክ-ከተማ አሰ-ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ-ቤት፣ የአ.አ ከተማ የየካ ክ-ከተማ አስተዳደር የትምህርት ፅ-ቤት የሰ-መ-ቁ 180001

Tuesday, October 6, 2020 16525

ጉዳዩ ከሚመለከተው የመንግሰት አካል የግንባታ ፈቃድ ተሰጥቶ ግንባታው ከተጀመረ በኋላ ፈቃዱ የተሰጠው በተጠቀሰው ትምህርት ቤት የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ተፅዕኖ እንደሚፈጥር በጥናት በተለዬ ይዞታ ላይ ነው በሚል የተሰጠውን የግንባታ ፈቃድ አግዶ የተጀመረው ግንባታ እንዲቆም መደረጉ የሁከት ተግባር ነው በሚል የቀረበውን ክስ የመረመረው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች በአመልካች መብት ላይ የፈጠሩት ሁከት የለም ሲል በሰጠው ውሣኔና ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የአመልካችን ይግባኝ በመሰረዙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ፈፅመዋል ተብሎ እንዲታረም የቀረበን  ክርክር የሚመለከት ነው፡፡………….

 

Read more
FirstPrevious28293031323334353637Next

Categories

  • 2011 Expand/Collapse
  • 2012 Expand/Collapse
  • 2013 Expand/Collapse
    Contacts
  • TEL : +251-11-1-55-34-00 /
  •          +251-11-1-11-04-32
  • Fax : +251 111-550278 /
  •          +251 111-565583
  • Email : fscpublicrelation@gmail.com
  • Address: 6 Killo , Addis Ababa, Ethiopia
Quick Links
  • About Us
  • E-Filing 
  • Calendar
  • Press Release
  • Case Tracker
  • FAQ
    Connect With Us
  • Privacy Policy
  • |
  • Site Map
Copyright © The Federal Supreme Court of Ethiopia- All rights reserved
Powered By Bsquare IT Solutions