ይህ የሰበር አቤቱታ ሊቀርብ የቻለው አመልካች እና በስር ፍርድ ቤት ከ1ኛ እስከ 3ኛ የተመለከቱት ተከሳሾች አከራካሪውን ቤት ለተጠሪ ሊያስረክቡ ይገባል በማለት የስር የጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች መፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አመልካች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ መነሻ በማድረግ ሲሆን ተጠሪ በጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበሩ ሲሆን አመልካች 1ኛተከሳሽ ነበሩ፡፡
ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በአመልካች እና በስር ፍርድ ቤት ከ1ኛ እስከ 3ኛ በተመለከቱት ተከሳሾች ላይ ባቀረቡት ክስም አዋሳኙ በክሱ ላይ የተመለከተውን 400 ካሜ ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤት ከነሰርቪሱ የካቲት 27 ቀን 2011 ዓም በተደረገ የሽያጭ ውል ከ1ኛ እስከ 3ኛ ከተመለከቱት ተከሳሾች በብር 200,000.00 ገዝቼ ካርታ በስሜ የተሰጠኝ ቢሆንም ቤቱን ከአመልካች ነፃ በማድረግ ያላስረከቡኝ በመሆኑ ፤አመልካችም በአደራ ይዤ የምጠቀመው ነው በማለት ምንም መብት ሳይኖረው ለማስረከብ ፍቃደኛ ስላልሆነ ከ1ኛ እስከ 3ኛ የተመለከቱት ተከሳሾች ቤትና ይዞታውን ከ3ኛ ወገን ነፃ አድርገው እንዲያስረክቡኝ አመልካችም የፈጠረውን ሁከት አቁሞ ቤትና ቦታውን እንዲያስረክበኝ ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል፡፡……..