Login
Federal Supreme Court of Ethiopia
Search
  • Home
  • About Us
    • President Message
    • President
      • Current President
      • Former President
    • Vice President
      • Current Vice President
      • Former Vice Presidents
    • History and Traditions
    • Judges
      • Former Judges
    • Vision Mission and Mandate
    • Judicial Administration Council
  • Court Services
    • Registry Services
      • Court Forms and Fees
    • Daily Court Trial Schedule
    • Case Tracker
    • Requesting Court Documents
      • Disposed Cases
    • Court Annexed Mediation
    • Interpretation Services
    • Legal Support
      • Child Justice Project Office
      • Public Defenders Office
  • Going to Court
    • Visiting the Court
      • What Can I see and Do?
    • Courtroom Etiquette
      • Courtroom Rules
    • Criminal: Information for the Accused Person
    • Civil Disputes: Information for Parties
    • Representing Yourself
    • Information for Witness
    • Information for Lawyers
    • FAQ
  • Digital Law Library
    • Annual Reports
    • State of the Judiciary
    • Monthly Judges Seminar
    • Federal Laws
    • Archives
    • Publications
      • Journal
      • Federal Cassation Decision Series
      • Newsletter
    • Judgments
      • Cassation Decisions
      • Supreme Court Decisions
  • News Media
    • Announcements
    • Interactives
      • Photos
      • Video
    • Services for Media
      • Press Releases
      • Press Conference
      • Media Advisories
      • Speeches
    • NEWS
  • Contacts
    • Federal Supreme Court
    • Federal High Court
    • Federal First Instance Court
    • Contact and Feedback
  • Tender
  • Judgement Execution Directorate
    • About Judgement Execution Directorate
    • Auction
  • Vacancy
  • Child Justice Project

እነ አቶ ሁሴን አሊ እንድሪስ እና ወ/ሮ ዘሀራ ዱሌቦ የሰበር መዝገብ ቁጥር 214803

Friday, July 22, 2022 14434

ጉዳዩ ተጠሪ የሟቹ ሚስት መሆናቸውን እንዲሁም በሰበር ክርክሩ የሌሉት ሌሎች አራት ሰዎች ደግሞ የሟቹ ልጆች ስለሆኑ የሟች ሐጂ አሊ እንድሪስ ሙሳ ውርስ እንዲጣራ ውርስ አጣሪ እንዲሾምላቸው 1ኛ አመልካችን ተጠሪ በማድረግ አቤቱታ አቅርበው 1ኛ አመልካችም ውርሱ ቢጣራ እንዳማይቃወሙ መልስ የሰጡ ሲሆን ፤ ቀሪዎቹ አመልካቾችም የሟቹ ልጆች መሆናቸውን በመግለጽ ጣልቃ ገብተው የውርስ ማጣራት ክርክሩ ተካፋይ ለመሆን ጠይቀው ፍርድ ቤቱም ውርሱ ተጣርቶ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቶ ውርሱ ተጣርቶ ሪፖርቱ ቀርቧል፡፡ አመልካቾች በሟቹ ስም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ቁጥሩ 1588 የሆነው ቤት እና በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ቁጥሩ 1577 የሆነው ጋራዥ ቤት ተሸጦ የተገኘው ገንዘብ ሟች አባታቸው ሐጂ አሊ እንድሪስ ከሟቿ እናታቸው ወ/ሮ ዘውድነሽ ጋር በጋራ ያፈሩት ነው በማለት አስተያየታቸውን ስያቀርቡ ተጠሪ ሟች ንብረቱን ያፈሩት ከእሳቸው ጋር መሆኑንና ከሟቹ ጋር በጋብቻ ውስጥ እያሉ በቤት ቁጥር 1588 ላይ ከሁለት ሚልዮን ብር በላይ በማውጣታቸውንና ጋራዥ ቤት ተሸጦ በ1ኛ አመልካች እጅ የሚገኘው የሽያጭ ገንዘብ ግማሹ እንዲሰጣቸው ተከራክረዋል፡፡መልካም ንባብ……..

Read more

ወ/ሮ ለምለም ቅጣው እና ወ/ሮ ዘቢባ የሱፍ የሰ/መ/ቁ 214325

Friday, July 22, 2022 14165

ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው የአሁን ተጠሪ በቀን 09/06/2012 ዓ.ም ባቀረቡት አቤቱታ ሟች አባቴ የሱፍ ኢብራሂም በቀን 05/05/1987 ዓ.ም በሞት ተለይቷል፡፡ የአባቴን ወራሽነት በደዋ ጨፋ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁ 0302372 አረጋግጫለሁ፡፡ አባቴ በህይወት ሲኖር ተከሳሽን አግብቶ 6 ልጅ ያላቸው ሲሆን እኔ ደግሞ ከበፊት ሚስቱ ወ/ሮ ሀሊማ ኡስማን የወለደኝ ስሆን አባቴ በህይወት እያለ በከሚሴ ከተማ ውስጥ 528 ካ.ሜ በሆነ ቦታ ላይ የሚገኝ 1 ትልቅ ቆርቆሮ ቤት በውስጡ 2 ክፍል ያለው፣1 ትልቅ ቆርቆሮ ቤት 6 ክፍል ያለው እንዲሁም 6 ክፍል ሰርቪስ ቤት ያለው ሁሉንም በጋራ አፍርተዋል፡፡ አባቴ ሲሞት ህጻን ስለነበርኩ ካደኩኝ በኋላ በተከሳሽ ስር እንደ ወላጅ እናት በማየት በፍርሀትና በማክበር ክስ ሳላቀርብ ቆይቼ ንብረት እንድታካፍለኝ በሽማግሌ ብጠይቅም ለማካፈል እንቢ ስላለች የውርስ ንብረት ድርሻዬን እንድታካፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ………

Read more

እነ መ/ር ገመቹ ቹዋታ እና የየጋምቤላ ብ/ክ/መ/ ጠ/ዓ/ህግ ሰ/መ/ቁጥር 214184

Thursday, July 21, 2022 15430

ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ በቀን ታህሳስ 15/2013 ዓ.ም በጻፈው የወንጀል ክስ በአሁን አመልካቾች እና በሌሎች 6ኛ፤7ኛ እና 8ኛ የስር ተከሳሽች ላይ በጋምቤላ ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ የመጀመሪያ ክስ  በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ድ.ሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ/፣37/1/ሀ እና 539/1/ን በመተላለፍ አመልካቾች በክሱ በተገለፀው ልዩ ቦታ፣ቀንና ሰዓት 1ኛና 2ኛ አመልካቾች ከስር ተከሳሾችና ከሌሎች አመልካቾች ጋር በመገናኘት 2ኛ አመልካች ለግል ተበዳይ ተማሪ ቤር አጆክ ስልክ በመደወል ቴድባሌ ወደሚባል ሰፈር በመውሰድ አንገቷን ቆርጠው ህይወቷ ካለፈ በኋላ ሞተር ሳይክል እንዲመጣ ለ3ኛ አመልካች ደውለው ሬሳውን በሞተር ሳይክል ጫካ ውስጥ የጣሉ መሆኑንና አባሪ ተባባሪ በመሆን የግድያ ወንጀል የፈጸሙ መሆኑን በመጥቀስ የከሰሰ ሲሆን፣ ሁለተኛው ክስ በ2ኛ፣ 3ኛ  4ኛና 5ኛ አመልካቾች ላይ የቀረበ ሲሆን በ1996 ዓ.ም በወጣውን የኢፌድሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ/ እና አንቀጽ 841/1//1 ን በመተላለፍ  ከላይ  በተገለፀው ልዩ ቦታ፣ቀንና ሰዓት በፈጸሙት ሬሳ የማንገላታት ወንጀል ክስ ተከሰዋል የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ………

Read more

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና አቶ ተከስተ ካሴ የሰ/መ/ቁ. 212603

Thursday, July 21, 2022 15553

ጉዳዩ የስራ ስንብትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ተጠሪ ባቀረቡት ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ እ.አ.አ. ከቀን 22/04/2020 ዓ.ም ጀምሮ በወር ብር 42,863.37 እየተከፈለኝ በአውሮፕላን ጥገና አሰልጣኝነት ሳገለግል ቆይቻለሁ፡፡ ከመስከረም 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በድርጅቱ ውስጥ በተቋቋመው የሰራተኛ ማህበር ውስጥ ምክትል ፀኃፊ በመሆን እያለገልኩ ቆይቻለሁ፡፡ ይሁን እንጂ አመልካች ስለእኔ እውነት ያልሆነ መረጃ በማስተላለፍ ስም እና ዝናዬን አጥፍተሃል፣ ከሌሎች ሰራተኞች ጋር በስራ ቦታ መተባበር እና ሰላማዊ የስራ ግንኙነት እንዳይኖር አድርገሃል በማለት የስራ ውሌን አቋርጦታል፡፡ ከስራ ስሰናበት በህብረት ስምምነቱ መሠረት በተቋቋመው ኮሚቴው ውስጥ የሰራተኛ ማህበር ተወካይ አልነበረም፡፡ ስለሆነም ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ተብሎ ያልተከፈለኝ ደሞዝ ተከፍሎኝ ወደ ስራዬ እንድመለስ ይወሰንልኝ፤ ወደ ስራ ልመለስ የማልችልበት አግባብ ካለ ደግሞ የስራ ስንብት ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ የሚያዝያ ወር ሙሉ ደሞዝ፣ እ.አ.አ. የ2020 ዓ.ም የዓመት እረፍት ክፍያ እንዲከፍለኝ እና የስራ ልምድ እንዲሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት የጠየቁትን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡መልካም ንባብ……..

Read more

የደቡብ ክልል ዐ/ሕግ እና እነ በረከት በየነ የሰ/መ/ቁጥር 211689

Thursday, July 21, 2022 15767

ጉዳዩ የሰው መግደል ወንጀል የሚመለከት ክስን  የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነበር፡፡ የአሁን አመልካች ጳጉሜ 4ቀን 2011ዓ/ም በተፃፈ ክሱ 1ኛ ተጠሪን 3ኛ ተከሣሽ 2ኛ ተጠሪን ደግሞ 5ኛ ተከሣሽ በማድረግ ተጠሪዎች ከሌሎች ተከሣሾች ጋር ሆነው የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1)(ሀ) እና 540 የሚደነግገውን ተላልፈው የካቲት 24ቀን 2011ዓ/ም ከምሽቱ በ2ሰዓት አረካ ከተማ ቀበሌ 04 ትምህርት ቤቶች ፅ/ቤት ፊት ለፊት ሟች አዲሱ በለጠን 4ኛ ተከሣሽ ስሙን ጠርቶ እንዲቆም አድርጎ ለስላምታ የሟችን እጅ ጨብጦ እንደያዘው፤ 1ኛ ከሣሽ ከኋላ በኩል በፌሮ ብረት የኋላ ጭንቅላቱን 2 ጊዜ ሲመታው፤ 2ኛ ተከሣሽ በጌጠኛ ድንጋይ (ኮብል ስቶን) የግራ ጭንቅላቱን 3ኛ ተከሣሽ(1ኛ ተጠሪ ) የሟችን ጀርባ በክራንች ሁለት ጊዜ፤   5ኛ ተከሣሽ(ሁለተኛ ተጠሪ) ሟቹ እንደወደቀ ጉረሮውን እና ሆዱን ከረገጠው በኋላ ሮጠው ማምለጣቸውን ሟች በድብደባው ስለደከመ በዱቦ ሆስፒታል ሲታከም ቆይቶ መጋቢት 5ቀን 2011ዓ/ም መሞቱን በመዘርዘር የሰው መግደል ወንጀል ፈፅመዋል የሚል ክስ አቅርቦባቸዋል፡፡መልካም ንባብ………….

Read more
Previous12345678910NextLast

Categories

  • 2011 Expand/Collapse
  • 2012 Expand/Collapse
  • 2013 Expand/Collapse
    Contacts
  • TEL : +251-11-1-55-34-00 /
  •          +251-11-1-11-04-32
  • Fax : +251 111-550278 /
  •          +251 111-565583
  • Email : fscpublicrelation@gmail.com
  • Address: 6 Killo , Addis Ababa, Ethiopia
Quick Links
  • About Us
  • E-Filing 
  • Calendar
  • Press Release
  • Case Tracker
  • FAQ
    Connect With Us
  • Privacy Policy
  • |
  • Site Map
Copyright © The Federal Supreme Court of Ethiopia- All rights reserved
Powered By Bsquare IT Solutions