Login
Federal Supreme Court of Ethiopia
Search
  • Home
  • About Us
    • President Message
    • President
      • Current President
      • Former President
    • Vice President
      • Current Vice President
      • Former Vice Presidents
    • History and Traditions
    • Judges
      • Former Judges
    • Vision Mission and Mandate
    • Judicial Administration Council
  • Court Services
    • Registry Services
      • Court Forms and Fees
    • Daily Court Trial Schedule
    • Case Tracker
    • Requesting Court Documents
      • Disposed Cases
    • Court Annexed Mediation
    • Interpretation Services
    • Legal Support
      • Child Justice Project Office
      • Public Defenders Office
  • Going to Court
    • Visiting the Court
      • What Can I see and Do?
    • Courtroom Etiquette
      • Courtroom Rules
    • Criminal: Information for the Accused Person
    • Civil Disputes: Information for Parties
    • Representing Yourself
    • Information for Witness
    • Information for Lawyers
    • FAQ
  • Digital Law Library
    • Annual Reports
    • State of the Judiciary
    • Monthly Judges Seminar
    • Federal Laws
    • Archives
    • Publications
      • Journal
      • Federal Cassation Decision Series
      • Newsletter
    • Judgments
      • Cassation Decisions
      • Supreme Court Decisions
  • News Media
    • Announcements
    • Interactives
      • Photos
      • Video
    • Services for Media
      • Press Releases
      • Press Conference
      • Media Advisories
      • Speeches
    • NEWS
  • Contacts
    • Federal Supreme Court
    • Federal High Court
    • Federal First Instance Court
    • Contact and Feedback
  • Tender
  • Judgement Execution Directorate
    • About Judgement Execution Directorate
    • Auction
  • Vacancy
  • Child Justice Project

የፌደራል ዐቃቤ ህግ እና አቶ አበበ ወንድሙ ኤጋ የሰ/መ/ቁጥር 251759

Tuesday, June 17, 2025 5264

አመልካች በስር ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ ተጠሪ የወ/ህ/ቁ.539(1)(ሀ) ን ተላልፈው ሰው ለመግደል አስቀድሞ በነበረው ሀሳብ ጨካኝነቱንና ነውረኝነቱን በሚያሳይ ሁኔታ ወንድሙን ሟች ጀንበሩ ወንድሙን ከአሁን በፊት ሰድቦኛል እንዲሁም በሚያሽከረክረው መኪና ሊገጨኝ ሞክሯል በማለት በቂም በቀል በመነሳት ሽጉጥ ተኩሶ ማጅራቱን ሲመታው ሲወድቅ በተደጋጋሚ ሶስት ጊዜ ተኩሶ ግንባሩን በቀኝ በኩል አንገቱንና በግራ በኩል አንገቱን በመምታት የጥይት እርሳስ ጉዳት በራስ ቅሉ የኋለኛው ክፍል፤የክብ ቅርፅ ያለው ጥይት እርሳስ የገባበት ቁስል በራስ ቅሉ የኋለኛው ክፍል፤ሳተላይት ቅርጽ ያለው የጥይት እርሳስ የወጣበት ቁስል፤በግራ ግንባሩ የፊተኛው ክፍል ላይ የአጥንት መሰበር ጉዳት፤በራስ ቅሉ ፊተኛው የታችኛው ክፍል ላይ እንዲደርስበት፤የመበሳት ጉዳት በአንገቱ ላይ እንዲደርስበት ፤በአንጎሉ የላይኛው ሽፋን ክፍል የተሰራጨ የደም መፍሰስ እንዲሁም የአየር ባንቧው የመበለዝ ጉዳት እና በዙሪያው ከፍተኛ ደረጃ ያለው የውስጥ ደም መፍሰስ ጉዳት እንዲደርሰበት እና ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጓ በዚህም ከባድ የሆነ የሰው ግድያ ወንጀል ፈፅሟል በማለት ከሷል፡፡መልካም ንባብ….

Read more

ህብረት ኢንሹራንስ አ.ማ እና ኤም.ኢ.ኤስ.ፒ. አፍሪካ ኃ.የተ.የግ. ማህበር ፤የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጀት የሠ/መ/ቁጥር 251398

Friday, June 13, 2025 5591

የክሱ ይዘት በአጭሩ፡- ከቻይና ሀገር ለሚያስመጣቸው ብራንዳቸው ችንት የዋጋ ግምታቸው ብር 4,899,067.12 (አራት ሚልዮን ስምንት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺህ ስልሳ ሰባት ከ12/100) የሆኑ1,176(አንድ ሺህ አንድ መቶ ሰባ ስድስት) ካርቶን የተለያዩ የኤሌክትሮኒክ ዕቃዎች ከቻይና ተጓጉዘው ሞጆ ደረቅ ወደብ እስኪደርሱ ድረስ ጉድለትን ጭምሮ ለሚደረስ ማንኛውም ጉዳት በመድን ፖሊስ ቁጥር GU/34/2011/2019/00114 አጠቃላይ የመድህን ሽፋን የሰጣቸው ዕቃዎች ሞጆ ደረቅ ወደብ ደርሰው ከሳሽ ከመረከቡ በፊት ዕቃዎች ገበያ ላይ በመታየታቸው ፍተሻ ተደርጎ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት እንዲፈፀም ህዳር 15 ቀን 2012 ዓ.ም ከሳሽ አቤቱታ አቅርቦ የጉምሩክ ጽ/ቤት ተወካይ፤አጓዡ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጀት እና የከሳሽ ማኅበር ተወካዮች በተገኙበት ህዳር 17 ቀን 2012 ዓ.ም ዕቃዎቹ የመጡበት ኮንቴነር ተከፍቶ ሲፈተሸ የዋጋ ግምታቸው ብር 1,827,753.64 (አንድ ሚልዮን ስምንት መቶ ሃያ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ሶስት ከ64/100) የሆነ 171 እሽግ መጉደሉ ተረጋግጦ አጓዡ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጀት የጎደሉ ዕቃዎችን በዝርዝር በመያዝ ወደ መጋዘኑ ማስገባቱንና ተከሳሹ ህብረት ኢንሹራንስ አ.ማ አጓዡ ኃላፊነት ወስዶ የጉድለት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ስላልሰጠው የካሳ ክፍያ ጥያቄውን ማስተናገድ አልችልም ማለቱን ጠቅሶ ተከሳሹ ህብረት ኢንሹራንስ አ.ማ በገባው የማሪን ውል መሰረት የጎደሉ ዕቃዎች ዋጋ 1,827,753.64 (አንድ ሚልዮን ስምንት መቶ ሃያ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ሶስት ከ64/100) ካሳ ማስጠንቀቂያ ከደረሰው ከግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ፤ ከወጪ እና ኪሳራ ጭምር እንዲከፍለው ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ….

Read more

ሲሲኢሲሲ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ እና አቶ ቤልሻጽር ሀይለልዑል መ/ጽድቅ የሰ.መ.ቁ.250942

Thursday, June 5, 2025 5497

ይህ የስራ ስንብት ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር፡፡ ጉዳዩ ለዚህ ሰበር ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.296508 በ29/10/2015 ዓ.ም የሰጠዉ ፍርድ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልን በማለት በማመልከቱ ነዉ፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች በሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበዉ የክስ አቤቱታ፡ አመልካች በተጠሪ ድርጅት በብሮ ስራ መሃንዲስ የሥራ መደብ ተቀጥሬ በወር 80,000 (ሰማንያ ሺህ) እየተከፈለኝ በአርሲ ሮቤ ዋቤ ሪቨር ፕሮጀክት ሲሰራ የቆየሁ ሲሆን ተጠሪ በ02/12/2014 ዓ.ም በሕገወጥ መንገድ ከሥራዬ ስላሰናበተኝ ተገቢ ክፍያዎችን እንዲከፍለኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መለካም ንባብ….

Read more

እነ አቢብ አብዲ (3) ሰዎች እነ ዓሊ ዮሜ ዩሱፍ የሰ/መ/ቁጥር---250757

Thursday, June 5, 2025 5688

ክስ ይዘት በአጭሩ: - ለ60 ዓመት በይዞታቸዉ ስር አድርገዉ ጫት በመትል፤ ቦቆሎና ማሽላ እየዘሩ ሲጠቀሙበት ነበረዉን በጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 20 ዉስጥ የሚገኘዉን ስፋቱ 60 ቆጢ የእርሻ መሬት ይዞታቸዉን በኃይል ወረራ በማድረግ አመልካቾች ይዘዉት በፀጥታ አስከባሪዎች እንዲያቆሙ ትዕዛዝ ቢሰጣቸዉም ከድርጊታቸዉ ሳይገቱየዘሩት እህል በከፊል አዉድመዋል፡፡ ስለሆነም አመልካቾች የፈጠሩት ሁከት እንዲወገድላቸዉ እንዲወሰን የሚጠይቅ ነዉ፡፡መልካም ንባብ….

Read more

ወ/ሮ አዳነች ሞኝነት እና አቶ ይልቃል አቤ የሰ.መ.ቁ 250332

Thursday, June 5, 2025 5046

ለዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነው ክርክር የተጀመረው በአማራ ክልል ባሶ ሊበን ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን በወረዳው ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ በባሶ ሊበን ወረዳ ፍርድ ቤት ላይ ባቀረቡት ክስ አመልካች የተጠሪ አያት የሟች እማሆይ ጥሩ በላይ የቤተሰብ አባል ሳትሆንና ከሟቿ ጋር በአንድ ላይ ሆኖም ሆነ ከውጭ ሆኖ ሟቿን ሳትጦርና ሳትንከባከብ እንደጦረች እንደተንከባከበችና የሟቿ የቤተሰብ አባል እንደሆነች አስመስላ የሟቿን የእድሜ ባለፀጋነትን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሟቿ ከቢሮ ሳይሄዱ እንደሄዱና በስጦታ እንዳስተላለፉላት በማድረግ ከመሬት ባለሙያ ጋር በመመሳጠር በ13/10/1998ዓ.ም የስጦታ ውል በማስሞላት የኑዛዜ ስጦታውን በመሬት አስተዳደር ጽ/ቤት በማስመዝገብ የኑዛዜ ስጦታ አለኝ በማለት አጭበርብራ ማስረጃ እንደያዘች” ገልጸው የመሬት ስጦታ ውሉም ሆነ ማስረጃው እንዲሰረዝላቸው ዳኝነት በመጠየቅ ክስ አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ….

Read more
Previous12345678910NextLast

Categories

  • 2011 Expand/Collapse
  • 2012 Expand/Collapse
  • 2013 Expand/Collapse
    Contacts
  • TEL : +251-11-1-55-34-00 /
  •          +251-11-1-11-04-32
  • Fax : +251 111-550278 /
  •          +251 111-565583
  • Email : fscpublicrelation@gmail.com
  • Address: 6 Killo , Addis Ababa, Ethiopia
Quick Links
  • About Us
  • E-Filing 
  • Calendar
  • Press Release
  • Case Tracker
  • FAQ
    Connect With Us
  • Privacy Policy
  • |
  • Site Map
Copyright © The Federal Supreme Court of Ethiopia- All rights reserved
Powered By Bsquare IT Solutions