የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካቾች በቀን 24/04/2012 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 178872 በቀን 26/01/2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን በማለት ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ የጀመረው በስር የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካቾችና በዚህ ፍርድ ቤት ተከራካሪ ያልሆኑት ዋና ሳጅን ደረሰ ዘለቀ ከሳሾች ነበሩ፤ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ነበሩ፡፡
ከሳሾች በቀን 07/03/2010 ዓ.ም በተፃፈ የውርስ ይጣራልን አቤቱታ የሟቾች አቶ ዘለቀ በቀለ እና ወ/ሮ ደደፌ ዱጉማ የመጀመሪያ ደረጃ እና ተተኪ ወራሾች መሆናቸውን፤ በመግለጽ ውርስ እንዲጣራላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ በማስረጃነትም ሟች አቶ ዘለቀ በቀለ በ16/01/1996 ዓ.ም እና ወ/ሮ ደደፌ ዱጉማ በ14/03/2008 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን የሚገልፅ የወራሽነት ማስረጃ አቅርበዋል፡፡እንደሚከተለው ቀርቧል………