Login
Federal Supreme Court of Ethiopia
Search
  • Home
  • About Us
    • President Message
    • President
      • Current President
      • Former President
    • Vice President
      • Current Vice President
      • Former Vice Presidents
    • History and Traditions
    • Judges
      • Former Judges
    • Vision Mission and Mandate
    • Judicial Administration Council
  • Court Services
    • Registry Services
      • Court Forms and Fees
    • Daily Court Trial Schedule
    • Case Tracker
    • Requesting Court Documents
      • Disposed Cases
    • Court Annexed Mediation
    • Interpretation Services
    • Legal Support
      • Child Justice Project Office
      • Public Defenders Office
  • Going to Court
    • Visiting the Court
      • What Can I see and Do?
    • Courtroom Etiquette
      • Courtroom Rules
    • Criminal: Information for the Accused Person
    • Civil Disputes: Information for Parties
    • Representing Yourself
    • Information for Witness
    • Information for Lawyers
    • FAQ
  • Digital Law Library
    • Annual Reports
    • State of the Judiciary
    • Monthly Judges Seminar
    • Federal Laws
    • Archives
    • Publications
      • Journal
      • Federal Cassation Decision Series
      • Newsletter
    • Judgments
      • Cassation Decisions
      • Supreme Court Decisions
  • News Media
    • Announcements
    • Interactives
      • Photos
      • Video
    • Services for Media
      • Press Releases
      • Press Conference
      • Media Advisories
      • Speeches
    • NEWS
  • Contacts
    • Federal Supreme Court
    • Federal High Court
    • Federal First Instance Court
    • Contact and Feedback
  • Tender
  • Judgement Execution Directorate
    • About Judgement Execution Directorate
    • Auction
  • Vacancy
  • Child Justice Project

አቶ ቢኒያም ግርማ ታደሰ እና አቶ ያሬድ በፍቃዱ ሀይሌ የሰ/መ/ቁጥር 214002

Monday, July 18, 2022 13506

አመልካች መስከረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም በአጭር ሥነ-ሥርዓት ባቀረቡት ክስ ተጠሪ በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አክስዮን ማህበር አዲሱ ገበያ ቅርንጫፍ በሒሳብ ቁጥር 7000003133678 የተመዘገበን ሒሳብ ለማንቀሳቀስ ካወጡት ቼክ ውስጥ ቁጥሩ ቢቲ3209475 በሆነ ቼክ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺ) እንዲከፈለኝ ሐምሌ 17 ቀን 2012 ዓ.ም ፈርመው ሰጥተውኛል፡፡ አመልካችም ክፍያ እንዲፈፅምልኝ ቼኩን ለባንኩ ቅርንጫፍ ያቀረብኩ ቢሆንም የቼክ ቁጥሩ ስለታገደ መክፈል የማይችል መሆኑን ገልጾ ነሐሴ 21 ቀን 2012 ዓ.ም ማረጋገጫ ሰጥቶኛል፡፡ ተጠሪም ክፍያውን እንዲፈጽምልኝ በተደጋጋሚ ብጠይቀውም ፍቃደኛ ስላልሆነ ብር 500,000፣ በሕጉ የተደነገገውን ኮሚሲዮን፤ ህጋዊ ወለድ እንዲሁም ወጪ እና ኪሳራ እንዲከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ መልካም ንባብ……….

Read more

ወ/ሮ ፀሀይ ተፈራ እና ወ/ሮ ወይንሸት ከበደ የሰ/መ/ቁጥር 206083

Monday, July 18, 2022 13773

አመልካች ሰኔ 1 ቀን 2010 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት ክስ የስር ተከሳሾች በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥሩ 154 የካርታ ቁጥሩ 20913 የሆነን ቤት ግንቦት 3 ቀን 1998 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭ ውል በብር 125,000 ሸጠውልኝ ብር 92,000 ተቀብለው ስመ ሀብቱን ለማዘወውር ተዋውለው ቤቱን ተረክቤያለው፡፡ ነገር ግን ስመ ሀብቱን  ሊያዛውሩልኝ ፍቃደኛ ስላልሆኑ ቤቱ የእኔ መሆኑ ተረጋግጦ ስመ ሀብቱን እንዲያዛውሩልኝ እንዲሁም ወጪ እና ኪሳራ እንዲተኩልኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ……..

Read more

ኮለኔል ይርጋለም ፍቃዱ አባይ ወታደራዊ ዐ/ሕግ የሰ/መ/ቁጥር 221416

Monday, July 18, 2022 14739

ጉዳዩ በተጀመረበት የሀገር መከላከያ ቀዳሚ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪ የካቲት 17ቀን 2013ዓ/ም በተፃፈ ክሱ አመልካች የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባል መሆናቸውን፣ ጥቅምት 24ቀን 2013ዓ/ም የትግራይ ክልል ልዩ ሐይል በሐገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ ሰራዊቱ በውጊያ ላይ በሆነበት  ጊዜ አመልካቹ የውትድርና አግልግሎታቸውን በመተው ኮብልለው ህዳር 12ቀን 2013ዓ/ም ጧት 2፡00 አፋር ክልል ዞን ሁለት ኢረብቲ ወረዳ ላኩራ ከተማ ተገኝተው በፖሊስ መያዛቸውን በመዘርዘር የወንጀል ሕግ አንቀፅ 288(2) የተደነገገውን ተላልፈው የኩብለላ ወንጀል ፈፅመዋል የሚል ክስ አቅርቦባቸዋል፡፡ መልካም ንባብ…….

Read more

ኮ/ል መንግስቱ ማሩ እና የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤሕግ የሰ.መ.ቁ 220703

Monday, July 18, 2022 14529

ጉዳዩ ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡ የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካች ላይ በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ይዘት በአጭሩ፡- አመልካች የወንጀል ሕግ ቁጥር 669/2/ለ ድንጋጌን በመተላለፍ ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለራሱ ለማግኘት በማሰብ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በሲ.ኤም.ሲ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል መከላከል የስራ ባልደረባ ሆኖ ሲሰራ በቀን 27/2/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ሲሆን ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 08 ልዩ ቦታው ሴፍ አየር መንገድ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን አስመልክቶ የወ/ሮ ብስራት ሐጎስን መኖሪያ ቤት በሚበረብሩበት ወቅት የግል ተበዳይ ንብረት የሆነውን ግምቱ ብር 15000 የሆነ A 31 ሳምሰንግ ሞባይል የወሰደ በመሆኑ በፈጸመው የስርቆት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ…

Read more

ሙሉ አብረሃ ኮንስትራክሽን አቅራቢ እና አቶ ተስፋሚካዔል ገብረጻድቃን የሰ.መ.ቁ. 220380

Monday, July 18, 2022 13775

ጉዳዩ የአፈጻጸም ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በሥር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች የፍርድ ባለመብት፤ የአሁን ተጠሪ ደግሞ የፍርድ ባለዕዳ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ያቀረቡት የአፈጻጸም ክስ ይዘት በአጭሩ፡- የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 186610 በቀን 25/01/2013 ዓ.ም የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በማሻሻል አመልካች ለተጠሪ ብር 597,662.20 (አምስት መቶ ዘና ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ሁለት ብር ከሃያ ሳንቲም) እና ወጪ ኪሳራው በዚሁ ልክ እንዲከፍላቸው ወስኗል፤ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ለተጠሪ በእላፊ የከፈልኩትን ዋና ገንዘብ ብር 397,169.90 (ሶስት መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ አንድ መቶ ስልሳ ዘጠኝ ብር ከዘጠና ሳንቲም) በውሳኔው መሰረት የተመለሰልኝ ሲሆን በእላፊ ከከፈልኩት ወጪ እና ኪሳራ ብር 66,369.48 (ስልሳ ስድስት ሺህ ሶስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ብር ከአርባ ስምነት ሳንቲም) ተመላሽ የሚደረግልን ብር 25.511 ሃያ አምስት ሺህ አምስት መቶ አስራ አንድ ብር) ስለሚሆን ይመለስልኝ ሲል ዳኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው፡፡መልካም ንባብ…………

Read more
Previous12345678910NextLast

Categories

  • 2011 Expand/Collapse
  • 2012 Expand/Collapse
  • 2013 Expand/Collapse
    Contacts
  • TEL : +251-11-1-55-34-00 /
  •          +251-11-1-11-04-32
  • Fax : +251 111-550278 /
  •          +251 111-565583
  • Email : fscpublicrelation@gmail.com
  • Address: 6 Killo , Addis Ababa, Ethiopia
Quick Links
  • About Us
  • E-Filing 
  • Calendar
  • Press Release
  • Case Tracker
  • FAQ
    Connect With Us
  • Privacy Policy
  • |
  • Site Map
Copyright © The Federal Supreme Court of Ethiopia- All rights reserved
Powered By Bsquare IT Solutions