Login
Federal Supreme Court of Ethiopia
Search
  • Home
  • About Us
    • President Message
    • President
      • Current President
      • Former President
    • Vice President
      • Current Vice President
      • Former Vice Presidents
    • History and Traditions
    • Judges
      • Former Judges
    • Vision Mission and Mandate
    • Judicial Administration Council
  • Court Services
    • Registry Services
      • Court Forms and Fees
    • Daily Court Trial Schedule
    • Case Tracker
    • Requesting Court Documents
      • Disposed Cases
    • Court Annexed Mediation
    • Interpretation Services
    • Legal Support
      • Child Justice Project Office
      • Public Defenders Office
  • Going to Court
    • Visiting the Court
      • What Can I see and Do?
    • Courtroom Etiquette
      • Courtroom Rules
    • Criminal: Information for the Accused Person
    • Civil Disputes: Information for Parties
    • Representing Yourself
    • Information for Witness
    • Information for Lawyers
    • FAQ
  • Digital Law Library
    • Annual Reports
    • State of the Judiciary
    • Monthly Judges Seminar
    • Federal Laws
    • Archives
    • Publications
      • Journal
      • Federal Cassation Decision Series
      • Newsletter
    • Judgments
      • Cassation Decisions
      • Supreme Court Decisions
  • News Media
    • Announcements
    • Interactives
      • Photos
      • Video
    • Services for Media
      • Press Releases
      • Press Conference
      • Media Advisories
      • Speeches
  • Contacts
    • Federal Supreme Court
    • Federal High Court
    • Federal First Instance Court
    • Contact and Feedback
  • Tender
  • Judgement Execution Directorate
    • About Judgement Execution Directorate
    • Auction
  • Vacancy
  • Child Justice Project

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል ገቢዎች ቢሮ እና አቶ አዕምሮ ዘሪሁን የሰ/መ/ቁ.210727

Tuesday, February 22, 2022 9066

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው ተጠሪ በባሕር ዳር ከተማ ገቢዎች መምሪያ የታክስ ኦዲትና የሕግ ማስከበር የሥራ ሂደት አስተባባሪነት ከነበሩበት ኃላፊነት ተነስተው ከደረጃ 9 ወደ ደረጀ 8 ዝቅ ብለው በሽያጭ መመዝገቢያ ኤክስፐርት ሆነው እንዲሰሩ በመመደባቸው ቅሬታ አቅርበው ተቀባይት በማጣቱ ለአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የአስተዳደር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ይግባኝ ጥፋት ሳይኖረብኝና የዲሲፕሊን ክስ ሳይቀርበብኝ ከሥራ መደቡ መነሳቴ ሆነ ከደረጃና ደመወዝ ዝቅ መደረጌ አግባብ አይደለም የሚል ሲሆን አመልካች ባቀረበው መልስ በደንብ ቁጥር 79/2003 አንቀጽ 9(4) መሠረት ማንኛውም የሥራ ሂደት አስተባባሪ በአሳማኝ ምክንያት ከኃላፊነት ሲነሳ ከያዘው መደብ ዝቅ ብሎ እንደሚመደብ ስለሚገልጽ በዚህ አግባብ የተከናወነ ነው ብሏል፡፡…………

Read more

ፌደራል ስነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን እና ወ/ሮ ፍሬህይወት ተረፈ የሰ/መ/ቁ፡- 209987

Tuesday, February 22, 2022 8631

ጉዳዩ ተጠሪ በአመልካች ኮሚሽን አለአግባብ ከደረጃና ከደመወዝ ዝቅ ተደርጌያለሁ በማለት ለፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ አስተዳደር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ይግባኝ መነሻ የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ተብሎ የቀረበዉን የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ ተጠሪ በአመልካች ላይ በአስተዳደር ፍርድ ቤት ዘንድ ባቀረቡት ይግባኝ ከንብረት አወጋገድ፣ከሂሳብ አዘጋግ፣ በኦዲት ግኝት ለይ የተሰጠዉን ምክረ ሀሳብ ተግባራዊ ከማድረግ እና ሥራዎቼን በወቅቱ ከመፈጸም አንጻር የፈጸምኩት ጥፋት ሳይኖር አለአግባብ ከነበርኩበት ሥራ መደብ አንድ ደረጃ ዝቅ አድርጎ መድቦኛል፡፡ በመሆኑም አመልካች የሰጠኝ የዲሲፕሊን ውሳኔ አግባብ አይደለም ተብሎ ወደ ቀድሞ የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ደረጃ -15 ስራ መደብ ላይ እንዲመልሰኝ እንዲሁም በእግድ ምክንያት ያልተከፈለኝን የሐምሌ እና የነሐሴ ወር 2012 ዓ/ም ደመወዝ ብር 20,300.00 አመልካች እንዲከፈለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡………..

Read more

እነ አቶ ከበደ ደሴ እና ወ/ሮ እልፍነሽ አብደላ የሰ/መ/ቁ.209757

Tuesday, February 22, 2022 9168

ጉዳዩ የሽያጭ ውል የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪዎች ከሳሽ በመሆን በአመልካቾች ላይ በሁለት የተለያዩ መዝገቦች ላይ ባቀረቡት ክስ አመልካቾች በደራጀማ ሆቴል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ውስጥ  ስድስት አክሲዮኖችን ከአንድ ሱቅ ጋር እንሸጥላችኋለን በማለት በ2004 ዓ.ም በተደረገው ውል ለ1ኛ ተጠሪ በብር 450,000.00 እንዲሁም ለ2ኛ ተጠሪ በብር 480,000.00 የሸጡልን ቢሆንም ውሉ ከህግ ውጪ የተደረገ በመሆኑ አመልካቾች በሽያጭ ውሉ መሰረት የወሰዱት ገንዘብ እንዲመልሱልን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡አመልካቾች በበኩላቸዉ ውሉ የተደረገው በቃል መሆኑንና አንደኛው ተዋዋይ በውሉ ጥቅም አለማግኘቱ የውል ማፍረሻ ምክንያት አይሆንም፣የተሸጠው በሱቅ የመጠቀም መብት እንጂ የሱቅ ባለሀብት እንዲሁም የአክሲዮን ድርሻ ላይ አይደለም፣ተጠሪዎች ሱቁን በመረከብ ሲጠቀሙበት ቆይቷል፤ይህም በሱቁ ላይ ጥቅም ሲያገኙ እንደነበር የሚያሳይ ነው፣ተጠሪዎች የከፈሉት ገንዘብ የሚመለስበት የህግ አግባብ የለም፣ማህበሩ የሚሰራበት ቤት ከቤቶች ኮርፖሬሽን በመከራየት ነዉ፤በመሆኑም ተጠሪዎች ያቀረቡት ክስ ውድቅ እንዲደረግ በማለት ተከራክረዋል፡፡………………..

Read more

እነ አቶ ዮሴፍ ኃይሌ እና ፎራንክ ቢዝነስ ግሩፕ አክሲዮን ማህበር የሰ/መ/ቁ. 209266

Tuesday, February 22, 2022 8546

ጉዳዩ የስራ ስንብትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካቾች ከሳሽ፣ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካቾች በተጠሪ ላይ በቀን 22/10/2012 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ በተጠሪ ድርጅት ውስጥ በተለያየ የቅጥር ዘመን በሽያጭ ባለሞያ የስራ መደብ ላይ ተቀጥረን ስንሰራ ብንቆይም ተጠሪ ከህግ ውጪ ከቀን 26/08/2012 ዓ.ም ጀምሮ አሰናብቶናል፡፡ ስለሆነም ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ተብሎ ተጠሪው ካሳ፣ የአገልግሎት፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ ቅጣት፣ ከግንቦት ወር ጀምሮ የኮሮና ወረርሺኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እስከሚበቃበት ጊዜ ድረስ ያለው የወር ደመወዛችን እና የዓመት እረፍት በገንዘብ ተቀይሮ እንዲከፈለን ይወሰንልን በማለት የጠየቁትን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡እንደሚከተልው ቀርቧል…………….

Read more

እነ አቶ ግርማ ገብራይ እና ወ/ሮ ወሰኔ ገብራይ የሰ/መ/ቁ፡-207081

Tuesday, February 22, 2022 8605

ጉዳዩ ከገጠር መሬት ጋር የተያያዘ የውርስ ክርክርን የሚመለከት ነዉ፡፡ አመልካቾች በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ወረዳ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ ተጠሪ የእናታችንን እና የአባታችንን የውርስ ይዞታ አዋሳኞቾቻቸዉ በክሱ ይዘት የተጠቀሱትን በአራት ቦታ የሚገኙ የእርሻ መሬቶችን እንዲሁም በሻሸመኔ ከተማ ዉስጥ በ2000 ካሬ ሜትር ላይ የሚገኝ አዋሳኙ በክሱ የተጠቀሰ መኖሪያ ቤት በጋራ እያስተዳደሩ ቆይተዉ ተጠሪ ድርሻችንን ሊያካፍሏቸዉ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ በመግለጽ ድርሻቸዉ አንዲያካፍሏቸዉ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡        

ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስ አመልካቾች የዉርስ ሀብት ነዉ የሚሉት መሬቶች ከ1980 ዓ/ም ጀምሮ በግላቸዉ ይዘዉ የሚጠቀሙበት እንደሆነ መኖሪያ ቤቱንም በግላቸዉ የሰሩት እንደሆነ በመግለጽ ክሱ ዉድቅ እንዲደረግላቸዉ በመጠየቅ ተከራክረዋል፡፡እንዲሁም የዉርስ ንብረት በአመልካቾች እጅ እንደሚገኝ በመግለጽ አመልካቾች እንዲያካፍሏቸዉ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በማቅረብ ተከራክረዋል፡፡…….

Read more
FirstPrevious234567891011NextLast

Categories

  • 2011 Expand/Collapse
  • 2012 Expand/Collapse
  • 2013 Expand/Collapse
    Contacts
  • TEL : +251-11-1-55-34-00 /
  •          +251-11-1-11-04-32
  • Fax : +251 111-550278 /
  •          +251 111-565583
  • Email : fscpublicrelation@gmail.com
  • Address: 6 Killo , Addis Ababa, Ethiopia
Quick Links
  • About Us
  • E-Filing 
  • Calendar
  • Press Release
  • Case Tracker
  • FAQ
    Connect With Us
  • Privacy Policy
  • |
  • Site Map
Copyright © The Federal Supreme Court of Ethiopia- All rights reserved
Powered By Bsquare IT Solutions