Login
Federal Supreme Court of Ethiopia
Search
  • Home
  • About Us
    • President Message
    • President
      • Current President
      • Former President
    • Vice President
      • Current Vice President
      • Former Vice Presidents
    • History and Traditions
    • Judges
      • Former Judges
    • Vision Mission and Mandate
    • Judicial Administration Council
  • Court Services
    • Registry Services
      • Court Forms and Fees
    • Daily Court Trial Schedule
    • Case Tracker
    • Requesting Court Documents
      • Disposed Cases
    • Court Annexed Mediation
    • Interpretation Services
    • Legal Support
      • Child Justice Project Office
      • Public Defenders Office
  • Going to Court
    • Visiting the Court
      • What Can I see and Do?
    • Courtroom Etiquette
      • Courtroom Rules
    • Criminal: Information for the Accused Person
    • Civil Disputes: Information for Parties
    • Representing Yourself
    • Information for Witness
    • Information for Lawyers
    • FAQ
  • Digital Law Library
    • Annual Reports
    • State of the Judiciary
    • Monthly Judges Seminar
    • Federal Laws
    • Archives
    • Publications
      • Journal
      • Federal Cassation Decision Series
      • Newsletter
    • Judgments
      • Cassation Decisions
      • Supreme Court Decisions
  • News Media
    • Announcements
    • Interactives
      • Photos
      • Video
    • Services for Media
      • Press Releases
      • Press Conference
      • Media Advisories
      • Speeches
    • NEWS
  • Contacts
    • Federal Supreme Court
    • Federal High Court
    • Federal First Instance Court
    • Contact and Feedback
  • Tender
  • Judgement Execution Directorate
    • About Judgement Execution Directorate
    • Auction
  • Vacancy
  • Child Justice Project

አቶ ቴዎድሮስ መስፋን ህንፃ ሥራ ተቋራጭእና አዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት (በአሁኑ - የአ/አ ቤ/ልማት ኮርፖሬሽን) የሰበር መ/ቁ 253303

Wednesday, June 4, 2025 4660

በዚህ መዝገብ የተያዘው ጉዳይ የግንባታ ዉልን የሚመለከት ነዉ፡፡ ጉዳዩ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ አመልካች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 04664 እና መ/ቁ 06910 አጣምሮ ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ/ም የሰጠዉን ዉሳኔ ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 37544 ህዳር 28 ቀን 2015 ዓ/ም የሰጠዉን ዉሳኔ ፤ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 40218 ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ/ም የሰጠዉን ዉሳኔ በመቃወም ነው፡፡

ተጠሪ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ  ከአመልካች ጋር መስከረም 26 ቀን 2008 ዓ/ም ጠቅላላ ዋጋዉ የብር 19,044,907.52 (አስራ ዘጠኝ ሚሊዮን አርባ አራት ሺ ዘጠኝ መቶ ስባት ከ52/100) የህንፃ ግንባታ ዉል የፈፀምን ሲሆን መንግስት ለዜጎች የስራ እድል ከመፍጠር አኳያ በዘርፉ የሚገኙ ተቋራጮች በአንድ ዘርፍ ብቻ እንዲሳተፉ ስለተደረገ አመልካች በአዲስ አበባ አስተዳደር የቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ ሥር በግንባታ ስራ ያለመሳተፍ ማስረጃ አንዲያቀርብ ተጠይቆ ተጠሪ መስከረም 12 ቀን 2008 ዓ/ም የተፃፈ ሀሰተኛ ማስረጃ በማቅረቡ በዉሉ አንቀፅ 2 መሰረት የማጭበርበር ስራ የፈፀመ በመሆኑ ዉሉ የተቋረጠ ሲሆን አመልካች አለአግባብ የወሰደውን ብር 3,264,297.15 (ሶስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ስልሳ አራት ሺ ሁለት መቶ ዘጠና ስባት ከ15/100) ቅድመ ክፍያ ለመመለስ ፍቃደኛ ስላልሆነ ይህን ገንዘብ ከወለድ ጋር እንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል፡፡መልካም ንባብ…..

Read more

ደጀኔ ደበላ አልቀረበም እና ኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 251700

Wednesday, June 4, 2025 5405

ጉዳዩ ይለፍ ወረቀት ሳይይዙ የግብርና ምርቶችን ማጓጓዝ ወንጀል የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ የተጀመረው በሰሜን ሸዋ ዞን ወራ ጃርሶ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡በተጠሪ የቀረበውም ክስ አመልካች የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ያወጣውን የገበያ ቁጥጥርና የምርት ጥራት አዋጅ ቁጥር 234/2013 አንቀፅ 26(3) እና 5 በመተላለፍ ታህሳስ 03 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 4፡00 ሰአት በወራ ጃርሶ ወረዳ ቀሬ ጎሃ ከተማ ቀበሌ 02 ልዩ ቦታው ኬላ ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ የሰሌዳ ቁጥር 3-16932 ኢት በሆነ ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ላይ 220(ሁለት መቶ ሃያ) ኩንታል ባቄላ ግምቱ 836,000 (ስምንት መቶ ሰላሳ ስድስት ሺህ) የሆነውን ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል አቅጣጫ በመጓዝ ላይ እያለ ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ሲደርስ በኬላ ተቆጣጣሪዎች ሲፈተሽ የንግድ ፍቃዱና የመነሻ እና መድረሻ የይለፍ ወረቀት ሳይይዝ በመጓዙ ያለ ፍቃድ የግብር ምርቶችን በማጓጓዝ ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ…..

Read more

እነ ወ/ሮ ዘውዲቱ ድንቁ(2ሰዎች)የቀድሞ አርጋፋ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት (በአሁን አርጋፋ ማዘጋጃ ቤት)የሰ/መ/ቁ፡- 250597

Wednesday, June 4, 2025 5841

የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች ሐምሌ 03 ቀን 2015ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 26960፤ ጥቅምት 28 ቀን 2015 የሰጠው ውሳኔ እና ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 42102፤ ሚያዝያ 03 ቀን 2015ዓ.ም መወሰኑ የመሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው፡፡

ጉዳዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 6 መሠረት የቀረበን የዳግም ዳኝነት ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ከመነሻው በዋናው ጉዳይ ክርክር የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል አጋርፋ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች ከሳሽ፤ የአሁን ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ፡፡መልካም ንባብ…..

Read more

አቶ ኩማ መልኩ እና አቶ ሰለሞን ዘለቀ የሰበር መ/ቁ/250546

Wednesday, June 4, 2025 5508

መዝገቡ ለሰበር ችሎት የቀረበዉ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ የህግ ስህተት የለዉም በማለት በመ/ቁ/ 423754 ላይ በቀን 11/09/2015ዓ.ም የሰጠዉ ትእዛዝ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል በዚህ ሰበር ችሎት እንዲታረም በማለት አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ነዉ፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ በስር ፍርድ ቤት አመልካቹ ከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን የተከራከሩ ሲሆን ጉዳዩ እርሻ መሬት ይዞታ የሚመለከት ነዉ፡፡አመልካች ሃምሌ 12 ቀን 2014ዓ.ም በዲጋሉና ጢጆ ወረዳ ፍርድ ቤት ባቀረበው አቤቱታ በዲጋሉ አራቢ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘውን አዋሳኞቹ በክሱ የተጠቀሰ መሬት ከአያቴ ከበደ ዋቅጅራ እና ሴት አያቴ ወ/ሮ የሺ ተ/ማሪያም በመ/ቁ/43575 በሆነው በዉርስ ተወስኖልኝ በመ/ቁ 43575 ተፈጽሞልኝ እያለ ተጠሪ ምንም መብት ሳይኖረዉ ስለያዘብኝ እንዲለቅልኝ ሲል የጠየቀ ሲሆን ተጠሪ ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ባቀረበው መልስ ይዞታው የአመልካች አያቶች ሳይሆን በቅይይር ከአቶ ታደሰ ከበደ ያገኘሁት የግል ይዞታዬ ነው፤የተቀያየርነውን ይዞታ ሰዎች ተቀብለው የመኖሪያ ቤት የሰሩበት ሲሆን እኔም ይዞታውን እየተጠቀምኩበት ስለሆነ ክሱ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል፡፡መልካም ንባብ…..

Read more

እነ ወ/ሮ ጌጤ ሙለታ(3ሰዎች) እና ወ/ሮ ብርሃኔ ካባ የሰ/መ/ቁ 249367

Wednesday, June 4, 2025 5450

ለዚህ የሰበር አቤቱታ መቅረብ ምክንያት የሆነዉ ጉዳይ የዉርስ ክርክርን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩ የተጀመረዉ በአምቦ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን በወረዳዉ ፍርድ ቤት አመልካቾች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካቾች በአምቦ ወረዳ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ሟች አባታቸዉን ሙለታ ካባን ተክተዉ ከሟች አያቶቻቸዉ አቶ ካባ ዳባ እና  ወ/ሮ ብርቱካን ፈካንሳ በዉርስ ሊያገኟቸዉ የሚገቡ በአምቦ ወረዳ ኢላሙ ጎርሚቲ ቀ/ገ/ማኅበር ዉስጥ በስድስት በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙትን የገጠር እርሻ ይዞታዎችን፣ በይዞታዎቹ ላይ የተፈሩ ቋሚ ሀብቶችንና የተለያዩ ከብቶችን ተጠሪ ከድርሻቸዉ በላይ ይዘዉ የሚገኙ መሆናቸዉን ገልፀዉ የዉርስ ሀብቶቹ ተጣርተዉ የሟች አባታቸዉን የዉርስ ድርሻ እንዲሁም ከፊሎቹ ከሳሾች ራሳቸዉን ችለዉ በጥገኝነት ሊያገኙ የሚገባቸዉን የዉርስ ድርሻ እንዲያገኙ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት በመጠየቅ ክስ አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ…..

Read more
FirstPrevious234567891011NextLast

Categories

  • 2011 Expand/Collapse
  • 2012 Expand/Collapse
  • 2013 Expand/Collapse
    Contacts
  • TEL : +251-11-1-55-34-00 /
  •          +251-11-1-11-04-32
  • Fax : +251 111-550278 /
  •          +251 111-565583
  • Email : fscpublicrelation@gmail.com
  • Address: 6 Killo , Addis Ababa, Ethiopia
Quick Links
  • About Us
  • E-Filing 
  • Calendar
  • Press Release
  • Case Tracker
  • FAQ
    Connect With Us
  • Privacy Policy
  • |
  • Site Map
Copyright © The Federal Supreme Court of Ethiopia- All rights reserved
Powered By Bsquare IT Solutions