18
የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ፤ ተጠሪ 2ኛ ተከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ አመልካች በቀን 26/11/2010 ዓ/ም በተጻፈ ያቀረቡት ክስ በሥር 1ኛ ተከሳሽ ስም ቁጥር 51/99/ሀ የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር ውስጥ በመደራጀት በንፋስ ስልካ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ስፋቱ 175 ካሬ ሜትር በቀን 10/02/1998 ዓ.ም በካርታ ቁጥር 01/91155313/00 የተሰጠና በ1ኛ ተከሳሽ ስም የተመዘገበ ነው፡፡ 1ኛ ተከሳሽ በቦታው ላይ ቤቱን መስራት ስላልቻለች እኔ በእራሴ ገንዘብ እንደሰራ ፈቅዳልኛለች፡፡ በዚሁ መሰረት ከ2003 ዓ.ም - 2005 ዓ.ም በብር 4063074.06 ብር የሚገመት ባለ አንድ ፎቅ ሕንጻ የሰራሁ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የቤቱ ግምት 6,000,000.00 ብር ነው፡፡ በመሆኑም ቤቱ በከሳሽ ልፋትና ገንዘብ የተሰራ ስለሆነ በቤቱ ላይ ያለኝ መብት ይረጋገጥልኝ፤ እውቅና እንዲያገኝ ይወሰንልኝ፤ ተከሳሽ ቤቱን ሽጠው አለአግባብ ለመበልጸግ የሚያደርጉት እንዲቆም ይወሰንልኝ፤ ይህ የማይቻል ከሆነ ወቅታዊ የቤቱን ዋጋ 6000000 ብር ቤቱ ከተሰራበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር እንዲከፍለኝ ወጪና ኪሳራ እንዲከፍለኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ..
14
ጉዳዩ ሁከት እንድወገድ የቀረበ ክርክር ሆኖ በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ በከሳሽነት ፤ አመልካች ደግሞ በተከሳሽነት ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ ሟች ወ/ሮ በቀለች ዳኜ በተከራዩት የቀበሌ ቤት ከ17 ዓመት ዕድሜያቸው ጀምሮ እንደልጅ አሳድገው እና አስተምረው በ1995 ዓ/ም በቅጽ ላይ ተመዝግበው የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ በማውጣት አገልግሎት እያገኘ መሆኑ እየታወቀ የተጠሪ አሳዳጊ በ2008 ዓ.ም ስሞቱ በመመሪያ ቁጥር 5/2011 አንቀጽ 16(ሐ) መሰረት መስተናገድ ሲገባቸው አከራካሪውን ቤት ለቀው እንድወጡ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ የሁከት ተግባር በመሆኑ ፤ የሁከት ተግባሩ ተወግዶ በቤቱ ላይ የኪራይ ውል እንድዋዋሉ ውሳኔ እንድሰጥ ጠይቀዋል፡፡ አመልካች ለክሱ በሰጠው ምላሽ የአከራካሪው ቤት ህጋዊ ተከራይ ወ/ሮ በቀለች ዳኜ ሲሆኑ ፤ ተጠሪ ተከራይም ሆነ ከተከራይ ጋር እንደልጅ ማደጋቸውን የሚያውቀው ነገር ባለመኖሩ እና በመመሪያው አግባብ ተስተናግደው አከራካሪው ቤት ስላልተሰጣቸው ቤቱን እንዲለቁ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ በሕጉ አግባብ በመሆኑ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ውድቅ ሆኖ ከበቂ ኪሳራ ጋር ከክሱ እንዲሰናቱ እንድወሰንላቸው ጠይቀዋል፡፡ጥሩ ንባብ..
17
የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ሲታይ በስር ፍ/ቤት ከሳሽ ተጠሪ ሲሆኑ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ተጠሪ ባቀረቡት ክስ በአመልካችና በተጠሪ መካከል ጥቅምት 02 ቀን 2001ዓ.ም በተደረገ ቤትን ገንብቶ የማስረከብ ውል አመልካች ከመንግስት በሊዝ ከተረከበው ቦታ በቦታ ቁጥር A-936 የቤት አይነት 1/ በመነሻ/1001.7 ካ.ሜ በሆነ የግቢ ስፋት የስምምነቱ አካል በሆኑት የቦታ ፕላን፣ የቤት ፕላን፣ የስራ ዝርዝር እና የግንባታ እቃዎች ዝርዝር የኤሌክትሪክ፣ውሃና የስልክ መስመር እንዲሁም ዋና ዋና የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገዶችን ጨምሮ ቤት ገንብቶ በ18 ወራት ውስጥ አጠናቆ ለማስረከብ ተጠሪ ለቤቱ እና ተጓዳኝ አገልግሎቶች ግንባታ ቫትን ጨምሮ የሚስፈልገውን ብር 2‚894‚285.50 (ሁለት ሚሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና አራት ሺህ ሁለት መቶ ሰማኒያ አምስት ከ50/100) ለመክፈል ተዋውለዋል፡፡አመልካች ግንባታውን ለማጠናከቀቅና ለማስረከብ የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የኮንስትራክሽ ግብዓት ላይ የዋጋ ንረት የገጠማቸው እና የዋጋ ጭማሪ ማስተካከያ እንዲደረግላቸው እና ቤቶቹ ከሚያዚያ 2003 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 2004 ዓ.ም ለማስረከብ በተደረገ ስምምነት መሰረት የዋናው ክፍያ እና የጭማሪ ዋጋ ማስተካከያ እንዲሁም ከ2000 ዓ.ም እስከ 2007 ዓ.ም ላለው ስምንት አመት ጊዜ ውስጥ የሚከፈል የሊዝ ክፍያን ጨምሮ ተጠሪ አጠቃላይ ብር 3‚426‚248.47 (ሶስት ሚሊዮን አራት መቶ ሃያ ስድስት ሺ ሁለት መቶ አርባ ስምንት ከ47/100) የከፈሉ ሲሆን በውሉ መሰረት አመልካች ቤቱን ገንብቶ እንዲያስረክባቸው፣በወቅቱ ግንባታውን ገንብቶ ባለማጠናቀቁ የውሉ 10% ብር 342‚624.85 (ሶስት መቶ አርባ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ሃያ አራት ከ85/100) መቀጮ እንዲከፍላቸው፣ቤቱን በወቅቱ ገንብቶ ባለማጠናቀቁ ከቤቱ በኪራይ ያገኙ የነበረውን በወር ብር 10‚000 (አስር ሺህ) ከታህሳስ 2004 ዓ.ም ጀምሮ ክሱ እስከ ቀረበበት ቀን ድረስ 87 ወራት ብር 870‚000 (ስምንት መቶ ሰባ ሺህ ብር) እና ወጪና ኪሳራ እንዲከፈላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ጥሩ ንባብ…
21
የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው የገጠር ውርስ መሬትን የሚመለከት ሲሆን የሥር ፍርድ ቤቶች ለውሳኔው መሠረት ያደረጉት አወራሾች በሞቱበት ጊዜ በሥር የነበረው የገጠር መሬት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 133/1998 እና ደንብ ቁጥር 51/1999 ነው፤ አመልካቾች ደግሞ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 መሠረት የውርስ ጉዳዩ ሊገዛ የሚገባው መሆኑን በመጥቀስ የመሬቱ ወራሽ ነን በማለት ተከራክረዋል፡፡ጥሩ ንባብ…
16
ክርክሩም በተጀመረበት በጋምቤላ ከተማ መስተዳደር የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ከሳሾች እና አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ተጠሪዎች በአመልካች ላይ ያቀረቡት ክስ ስሆን ይዘቱም በአጭሩ፡በአመልካች ድርጅት ውስጥ ተጠሪዎች ተቀጥረው ለሰባት አመት ከአራት ወር በማንተር የስራ መደብ ላይ እየሰሩ እንደሚገኙ እና በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/11 መሰረት አንድ ሰራተኛ የሙከራ ጊዜውን ጨርሶ እስካልተሰናበተ ድረስ ቀጣሪው አካል እንደ ቋሚ ሰራተኛ ያላቸውን መብትና ግዴታ እንደሚኖራቸው የሚደነግግ መሆኑን፡፡ሆኖም የአመልካች ድርጅት ተጠሪዎች በስራ ውላችን መሰረት የሙከራ ጊዜያችንን የጨረስን ቢንሆንም ወደ ቋሚነት ያልቀየረን በመሆኑ ቋሚ ሰራተኛ እንድንሆን እና በህገመንግስቱ አንቀፅ 25 መሰረት ከሰራተኛ ጋር እኩል መብታችን ተጠብቆ የ2007 ዓ/ም፤2009 ዓ/ም፤ 2011 ዓ/ም፤ የ2012 ዓ/ም እና 2013 ዓ/ም የሚገባንን ቦነስ ከሐምሌ 1/2013 ዓ/ም ጀምሮ ያልተከፈለንን የበረሃ አበል እና የውሎ አበል እንዲሁም የስራ ሴፍቲዎች እንዲሟላልን ቋሚ ሰራተኛ እንድንሆን ይወሰንልን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ጥሩ ንባብ…