6150
ጉዳዩ የሰራተኛ ጥቅማ ጥቅም ክፍያ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን ሃብሩ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪዎች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ አመልካች ተከሳሽ በመሆን የተከራከሩበት ነዉ፡፡ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ አመልካች ከአዋሽ- ኮምቦልቻ- ሃራ ገበያ ድረስ በሚያከናውነው የባቡር መንገድ ስራ ጊራና ሳይት ላይ ተቀጥረን ሲንሰራ የቆየን ሲሆን ያልተከፈለን የትርፍ ሰዓት፣ የሳምንት እረፍት፣ የህዝብ በዓላት ቀን ክፍያ እና የአልጋ አበል እንዲከፈለን ይወሰንልን የሚል ሲሆን አመልካች በበኩሉ የክፍያ ጥያቄ በይርጋ ይታገዳል፣ተጠሪዎች እነዚህ ክፍያዎች የሚገባቸው መሆኑን በማስረጃ አላረጋገጡም፣ትርፍ ሰዓት ስራ እንዲሰሩ አሰሪው ግልፅ ትዕዛዝ አልሰጠም፣የትርፍ ሰዓት መስራታቸዉ አልተመዘገበም፣ 9ኛው ተጠሪ የድርጅቱ ሰራተኛ አይደለም፣ የአልጋ አበል ለመክፈል አመልካች የገባው የውል ግዴታ የለም፣ለመክፈል አይገደድም በማለት ክሱ ውድቅ እንዲደረግ መከራከሩን መዝገቡ ያሣያል እንደሚከተልው ቀርቧል…………….
6026
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪዎች ከሳሾች ነበሩ፡፡ ተጠሪዎች ሠኔ 12 ቀን 2012 ዓ/ም ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ ከአመልካች ጋር የዓለም ምግብ ፕሮግራምን እንድንጠበቅ የጥበቃ ሥራ ውል ከግንቦት 23 ቀን 2011 ዓ/ም ጀምሮ እየሰራን እንገኛለን፡፡ የግል አሠሪና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲን አስመልክቶ በ2012 ዓ/ም በወጣው መመሪያ መሠረት አመልካች ከሚያገኘው ጠቅላላ ክፍያ ውስጥ ለሠራተኛው የሚከፍለው ደመወዝ ከ80% በታች መሆን እንደሌለበት ተመልክቷል፡፡………………
6369
ጉዳዩ የዲስፕሊን ዉሳኔ በመቃወም የቀረበ ክስ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ ተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ ነዉ፡፡የክሱ ይዘት ባጭሩ በተጠሪ ድርጅት ውስጥ ከታህሳስ 26 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ በከባድ መኪና ሹፌር የስራ መደብ ተቀጥሬ በማገልገል ላይ ሳለሁ ነሐሴ 6 ቀን 2010 ዓ.ም ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እያሽከረከርኩ እያለ በጅቡቲ ውስጥ አርታ(ዊያ) በተባለ ቦታ የመልከዓ ምድሩ አቀማመጥ አስቸጋሪ ቁልቁለትና መታጠፊያ በሆነበት ቦታ ሌላ መኪና ደርቦ የእኔን መስመር ይዞ በመምጣቱ አደጋውን ለመከላከል በድንገት ፍሬን ሲያዝ አደጋ ያጋጠመ ሲሆን አደጋው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት የደረሰ ስለመሆኑ ከጅቡቲ ሪፐብሊክ የመንገድ ደህንነት የሰጠው የምርመራ ሪፖርት የሚያረጋግጥ ቢሆንም የተጠሪ ድርጅት የዲስፕሊን ኮሚቴ ከባለሙያ ሪፖርት ውጭ እና አመልካች ሃሳብ ባልሰጠሁበት ሁኔታ በንብረት ላይ የደረሰው አደጋ ግምት ዋጋ ብር 2,820,778.92 መሆኑን የዚህን ግምት ዋጋ 3% ሂሳብ ከአመልካች ደመወዙ በየወሩ 1/3ኛ እየተቀነሰ እንዲከፍል ውሳኔ አስተላልፎ ከሀምሌ ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ እየተቆረጠ ይገኛል፣ በመሆኑም በተጠሪ ንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት በመድን ፖሊሲው ሽፋን መሰረት ንብረቱ ተጠግኖ እያለ ያለአግባብ የአደጋ ተጠያቂና ጥፋተኛ በማድረግ የተወሰነብኝ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዲነሳልኝ እና የአደጋው ግምት 3% እንዲከፍል የተወሰነብኝ ከህግ ውጭ ነው ተብሎ የተቆረጠውም እንዲመለስልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቆ ተጠሪ በበኩሉ የፖሊስ ማስረጃ አመልካች አደጋውን ማስቀረት ወይም መቀነስ በሚችልበት ሁኔታ አደጋው የተከሰተ በመሆኑ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ነዉ በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት እንደሌለዉ፣አመልካች ለዲስፕሊን ክስ የጽሁፍ መልስ፣ ከፖሊስ ሪፖርት ጋር እንዲሁም ከህብረት ስምምነት ድንጋጌ ጋር በማጣራት የፈፀመው ጥፋት ከስራ የሚያሰናብተው ቢሆንም ያለፈ መልካም አገልግሎት ግምት ውስጥ በማስገባት አመልካች ላይ የተወሰደው አስተዳደራዊ የቅጣት እርምጃ ተገቢ እና ህጋዊ በመሆኑ ሊነሳ አይገባም በማለት ተከራክረዋል፡፡…………
5484
ጉዳዩ የውርስ ሀብት ነዉ የተባለዉን የመሬት ይዞታ አስለቅቆ ለመረከብ በቀረበ ክስ መነሻ የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ተብሎ የቀረበ አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ አመልካቾች በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ሮቢት ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ በመሰረቱት ክስ ሟች አባታችን እንድሪስ አደም ከባለቤቱ ከስር 1ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ አሊያ አህመድ ጋር በባልና ሚስት በነበሩበት ጊዜ ከ1966 ዓ/ም ጀምሮ ይዘዉ በኋላም በ1989 ዓ/ም በነበረው የመሬት ሽግሽግ በሕጋዊ መንገድ ተደልድሎ የተሰጣቸዉ እና ከ1978 ዓ/ም ጀምሮ ግብር የሚገብሩበት በሸዋ ሮቢት ከተማ 05 ቀበሌ ውስጥ አዋሳኞቻቸዉ በክሱ የተጠቀሰ ልዩ ቦታዉ እስላም ቀብር ተብሎ በሚታወቅበት አካባቢ 2 ጥማድ መሬት፣ልዩ ቦታዉ ንብ እርባታ ተብሎ በሚታወቅበት አካበቢ 1 ጥማድ መሬት እንዲሁም እንስርቱ ዉሃ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ እሩብ ጥማድ መሬት 1ኛ ተከሳሽ ለብቻቸዉ ይዘዉ እየተጠቀሙ ሊያካፍሉን ፈቃደኛ ስላልሆኑ ድርሻችንን እንዲያካፍሉን ይወሰንልን፡፡ እንዲሁም 2ኛ ተጠሪ አለአግባብ ስለያዘብኝ ለቆ እንዲያስረክበን ይወሰንልን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡እንደሚከተለው ቀርቧል…………….
6486
ይህ ጉዳይ የተጀመረው በአሶሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች በተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ በአሶሳ ከተማ የሚገኘውንና እና የይዞታ መለያ ቁጥሩ 72/30/19 የሆነውን ሱቅ ወ/ሮ ትርንጎ በላይ እና አቶ በላይ አበበ ከተባሉ ግለሰቦች ላይ በውል ገዝቼ ውሉ ፀድቆ ስመ-ሀብቱ ወደ እኔ ዞሮ ቁጥሩ 355/164 የሆነ የምስክር ወረቀት ተሰጥቶኝ ለ10 ዓመታት ያክል ስሰራበት ቆይቻለሁ፡፡ ይሁን እንጂ ወ/ሮ ማሪቱ መንጌ የተባለች ግለሰብ በ2008 ዓ.ም በአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይዞታ ይገባኛል ክርክር አቅርባ ጉዳዩን እንዲያጣራ የታዘዘው ተጠሪ ለፍርድ ቤቱ በላከው ማስረጃ አመልካች 15.18 ካ.ሜ ይዞታ እንዳለፍኩኝ ለአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመግለጽ በህጋዊ መንገድ ያገኘሁትን ይዞታ በፍርድ አሳጥቶኝ ለከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ የዳረገኝ በመሆኑ ለደረሰብኝ ጉዳት ብር 3,000,000.00 ካሳ እንዲከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት የጠየቀዉን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡ክሱ እንደሚከተለው ቀርቧል…………….