ጉዳዩ የቤት ሽያጭ ውል አፈጻጸም የሚመለከት ጉዳይ ነዉ፡፡የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ፡- ክርክሩ የተጀመረው በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን በአሁኑ አመልካቾች ላይ ባቀረበው ክስ አመልካቾች በዱራሜ ከተማ ውስጥ በ460.6 ካ.ሜ ላይ ያላቸውን መኖሪያ ቤት በብር 2,250,000.00 በቀን 24/01/2012 ዓ.ም በተደረገው ውል ሽጠውልኝ ቀብድ ብር 1,000,000 መቀበላቸዉን እንዲሁም የተጠሪ ወኪል በ1ኛ አመልካች የባንክ ሂሳብ ብር 800,000.00 ገቢ በማድረጋቸው በአጠቃላይ ብር 1,800,000.00 የተቀበሉ መሆኑን ገልጾ አመልካቾች በውሉ መሰረት ቤቱን እንዲያስረክቡ እንዲወሰን ይህ ካልሆነ በፍ/ብ/ህ/ቁ.1885(2) መሰረት የተቀበሉትን ቀብድ አጠፌታ እና ገንዘቡ ተከፍሎ እስከሚያልቅ ህጋዊ ወለድ ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዲከፍሉ እንዲወሰን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል መልካም ንባብ……..