Login
Federal Supreme Court of Ethiopia
Search
  • Home
  • About Us
    • President Message
    • President
      • Current President
      • Former President
    • Vice President
      • Current Vice President
      • Former Vice Presidents
    • History and Traditions
    • Judges
      • Former Judges
    • Vision Mission and Mandate
    • Judicial Administration Council
  • Court Services
    • Registry Services
      • Court Forms and Fees
    • Daily Court Trial Schedule
    • Case Tracker
    • Requesting Court Documents
      • Disposed Cases
    • Court Annexed Mediation
    • Interpretation Services
    • Legal Support
      • Child Justice Project Office
      • Public Defenders Office
  • Going to Court
    • Visiting the Court
      • What Can I see and Do?
    • Courtroom Etiquette
      • Courtroom Rules
    • Criminal: Information for the Accused Person
    • Civil Disputes: Information for Parties
    • Representing Yourself
    • Information for Witness
    • Information for Lawyers
    • FAQ
  • Digital Law Library
    • Annual Reports
    • State of the Judiciary
    • Monthly Judges Seminar
    • Federal Laws
    • Archives
    • Publications
      • Journal
      • Federal Cassation Decision Series
      • Newsletter
    • Judgments
      • Cassation Decisions
      • Supreme Court Decisions
  • News Media
    • Announcements
    • Interactives
      • Photos
      • Video
    • Services for Media
      • Press Releases
      • Press Conference
      • Media Advisories
      • Speeches
    • NEWS
  • Contacts
    • Federal Supreme Court
    • Federal High Court
    • Federal First Instance Court
    • Contact and Feedback
  • Tender
  • Judgement Execution Directorate
    • About Judgement Execution Directorate
    • Auction
  • Vacancy
  • Child Justice Project

ብርሃን ባንክ አ/ማ እና ብርሃን ባንክ መሠረታዊ የሠራተኞች ማሕበር የሰ/መ/ቁ. 263727

Wednesday, June 4, 2025 5284

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበር፡፡ ተጠሪ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ/ም ጽፎ ባቀረበው ክስ አመልካች ድርጅት ለሁሉም ሰራተኞች በሚል በተጻፈ ጥቅማጥቅም የተወሰነ መሆኑ ተገልጾ እያለ የቤት አበል በተለምዶ በጽሕፈት መደብ ላይ ያልሆኑ /non-clericals/ የሚሰሩ ሰራተኞች አልከፍልም ማለቱ የእኩልነት መብት የሚጥስ በመሆኑ የቤት አበል እንዲከፈል እንዲወሰን ዳኝነት ጠይቋል፡፡ አመልካች በሠጠው መልስ ደብዳቤው ለሁሉም ሠራተኞች በሚል የተጻፈው የተለያየ የጥቅማጥቅም ሁኔታዎች የተካተቱበት ስለሆነ ነው፣ በጽሕፈት መደብ ላይ ላልሆኑ ሰራተኞች የቤት አበል ጥቅማጥቅም አልተወሰነም፣ ጥቅማጥቅም ሳይወሰን ክፍያ እንዲፈጸም ዳኝነት ሊጠየቅበት አይችልም፣ በተመሳሳይ የሥራ መደብ ላይ ለሚሰራ ሠራተኞች የተለያየ ጥቅማጥቅም እንዲያገኙ ያልተወሰነ በመሆኑ የእኩልነት መብትን አልተጣሰም፣ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል፡፡መልካም ንባብ…

Read more

ተወልደ ግደይ የኤሌክትሪክ ኬብል እና ዋየር ፋብሪካ እናየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰ/መ/ቁጥር 262505

Wednesday, June 4, 2025 5186

ጉዳዩ ለቅድመ ጥንቃቄ ዕዳን መልሶ የማዋቀር ሥነ ሥርዓትን የሚመለከት ነው፡፡ጉዳዩ የተጀመረው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአመልካች አቤቱታ አቅራብነት ነው፡፡በአመልካች የቀረበው አቤቱታ ይዘትም በአጭሩ ከተጠሪ ጋር ግንቦት 22 ቀን 2003 ዓ.ም እና ነሀሴ 28 ቀን 2011 በተደረገ የብድር አከፋፈል ስምምነት ብር 692,389,514.50 የብድር ገንዘብ ያለበት መሆኑን፤ብድሩ ተከፍሎ የሚያልቀው የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑን፤ከዚህ ውሰጥ ብር 419,224,378.70 መክፈሉን፤ ባጋጠመው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት የፋይናንስ እጥረት ያጋጠመው ቢሆንም አሁን የፋይናንስ እጥረት መሰረት የሆነው የጥሬ እቃ አቅርቦት ችግር በመፈታቱ የፋይናንስ ችግሩ በቅርብ የሚቀረፍ መሆኑን እና ይህም በሚዋቀርለት የዕዳ መክፈያ ጊዜ ውስጥ በተጨባጭ ዕዳውን መክፈል የሚያስችለው መሆኑን እንደዚሁም ሌሎች ምክንያቶችን በመዘርዘር ለቅድመ ጥንቃቄ ዕዳን መልሶ የማዋቀር ሥነ ሥርዓት ተፈቅዶለት ዕዳው ተዋቅሮ የሚከፍልበት ጊዜ እንዲሰጠው፤ዕዳው ሊከፈል የሚችልበትን አማራጭ መፍትሄዎች የሚያጠና ለፍ/ቤቱ፤ለአመልካች እና ለተጠሪ እንዲሁም ሌሎች ገንዘብ ጠያቂዎች ድጋፍ የሚያደርግ እና ሪፖርት የሚያቀርብ ባለሙያ እንዲሾም ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…

Read more

አቶ አሸናፊ ተስፋዬ እና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት የሰ/መ/ቁ 259817

Wednesday, June 4, 2025 5334

ጉዳዩ የመንግሰት ሰራተኛ በመስሪያ ቤቱ በተሰጠ ዉሳኔ ላይ ለአስተዳደር ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ የሚችልበት ሁኔታ እና የጊዜ ገደብ የሚመለከት ነዉ፡፡

በኢ.ፌ.ድ.ሪ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስተዳደር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር አመልካች አመልካች ተጠሪ ተጠሪ ነበሩ፡፡ አመልካች በቀረበባቸው ክስ ከባድ የዲስፕሊን ጥፋት ፈፅመዋል ተብሎ ከሥራ እንዲሰናበቱ ውሳኔ የተሰጠባቸው  እና በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ለአስተዳደር ፍርድ ቤት ይግባኝ ከማቅረባቸው በፊት የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው ያለፈባቸው መሆኑን በመግለፅ ይግባኙ እንዲፈቀድላቸው የይግባኝ ማስፈቀጃ አቅርበው ውድቅ በመደረጉ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው፡፡መልካም ንባብ…

Read more

አቶ ሳሙኤል ድረስ ደመቀ እና ዳሽን ባንክ አ.ማ የሰ/መ/ቁ 259234

Wednesday, June 4, 2025 5304

ጉዳዩ የስራ ክርክርን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩ የተጀመረው በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡በስር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡

አመልካች መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም በተጻፈ ክስ በተጠሪ ባንክ ዉስጥ በምክትል ሥራ አስኪያጂነት የስራ መደብ ከሚያዝያ 24 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ በራሴ ፍቃድ የስራ ዉሉን እስካቋረጥኩበት ታህሳስ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጠቅላላ ብር 46,191.01(አርባ ስድስት ሺ አንድ መቶ ዘጠና አንድ ከ01/100) እየተከፈለኝ በቋሚነት ተቀጥሬ እሰራ የነበረ ሲሆን ስራዉን በገዛ ፍቃዴ ስለቅ ተጠሪ ሊከፍለኝ የሚገባዉን የተጠራቀመ ፕሮፊደንት ፈንድ፣ የአገልግሎት ክፍያ፣ የተጠራቀመ የአመት ፍቃድ፣ ጠቅላላ ብር 541,422.78(አምስት መቶ አርባ አንድ ሺ አራት መቶ ሃያ ሁለት ከ78/100) ሊከፍለኝ ስላልቻል ይህን ክፍያ እንዲከፍለኝ እንዲሁም ክፍያዉ ለዘገየበት የካሳ ክፍያ፣ ያለስራ ለተቀመጥኩበት የሶስት ወር ደመወዝ ካሳ እና የስራ ልምድ ከእዳ ነፃ ተብሎ እንዲሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ…    

Read more

አቶ መንገሻ መሮ እና እነ መ/ር መስፍን መንገሻ (2ሰዎች) የሰ/መ/ቁጥር 258429

Wednesday, June 4, 2025 5077

በአመልካቾች የይግባኝ አቤቱታው የቀረበለት የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤትም ተጠሪዎች ከወላጆቻቸው ይዞታ በመውሰድ በራሳቸው ጉልበት እና ገንዘብ ያለሙ እና ለምርትም ሲደርስ ለአመልካች እና ባለቤታቸው እኩል በማካፈል በጋራ ሲጠቀሙ የነበሩ በመሆናቸው እንዲሁም የቤተሰብ አባል በመሆን በቤተሰብ በተመዘገበ ይዞታ ላይ እየተጠቀሙ የነበሩ በመሆናቸው የመጠቀም መብታቸው ቀሪ ሊሆን እና ያፈሩትንም ንብረት ሊያጡ አይገባም፣የስር ፍ/ቤቶችም ተጠሪዎች በይዞታው ላይ መብት የላቸውም በማለት የሰጡት ውሳኔ ተጠሪዎች በይዞታው ላይ ካላቸው መብት እና የቤተሰብ አባልነት አኳያ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውም ይዞታው ላይ የሚገኝ ቡና እና ኮረሪማ ባልና ሚስቱ ሊካፈሉ አይገባም፣አመልካች እና ባለቤታቸው ከተጠሪዎች ጋር በጋራ ሊጠቀሙ ይገባል በሚል ወስኗል፡፡ አመልካችም የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በሚል ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡ ሲሆን አቤቱታው የቀረበለት ችሎትም ውሳኔው የህግ ስህተት አልተፈጸመበትም በማለት ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡

አመልካችም ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ በአጭሩ ተጠሪዎች በውል ወይንም በውርስ ያገኙት የይዞታ ባለቤትነት መብት ሳይኖራቸው መከራከራቸው በህገ መንግስት አንቀጽ 40/7/8 የተቀመጠውን መብት ጥሰት ነው፡፡ተጠሪዎች መሬቱን ከ2000 ዓ.ም ጀምረው አልምተውታል ቢባል እንኳን አባታቸውን ስላገዙ የባለቤትነት መብት አይሰጣቸውም፡፡የክርክር መነሻ የሆነውን ይዞታ ያገኘሁት በአዋጅ ቁጥር 110/99 መሰረት አርሶአደር በመሆኔ ሲሆን ተጠሪዎች የከተማ ነዋሪዎች እና የመንግስት ሰራተኞች በመሆናቸው በውርስም ከሆነ ከሞትኩ በኃላ የሚፈፀም ይሆናል እንጂ በህይወት እያለው ይዞታውንና ንብረቱን ሊካፈሉ አይችሉም በሚል የተሰጠው ውሳኔ እንዲታረም ጠይቀዋል፡፡  መልካም ንባብ…

Read more
FirstPrevious3456789101112NextLast

Categories

  • 2011 Expand/Collapse
  • 2012 Expand/Collapse
  • 2013 Expand/Collapse
    Contacts
  • TEL : +251-11-1-55-34-00 /
  •          +251-11-1-11-04-32
  • Fax : +251 111-550278 /
  •          +251 111-565583
  • Email : fscpublicrelation@gmail.com
  • Address: 6 Killo , Addis Ababa, Ethiopia
Quick Links
  • About Us
  • E-Filing 
  • Calendar
  • Press Release
  • Case Tracker
  • FAQ
    Connect With Us
  • Privacy Policy
  • |
  • Site Map
Copyright © The Federal Supreme Court of Ethiopia- All rights reserved
Powered By Bsquare IT Solutions