17
የጉዳዩ አመጣጥ ተጠሪ በስር የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ በቀድሞው ወረዳ 24 ቀበሌ 14 አዲሱ ወረዳ 07 ልዩ ስሙ እንፎ መኪና ማሰልጠኛ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ውስጥ የሚገኝ ከአባቴ አቶ ኩምሳ በዳዳ በውርስ ያገኘሁት እና በግምት 1000ካ.ሜ የሆነ በአራቱም አቅጣጫ መንገድ የሚያዋስኑትን ወላጅ አባቴ ከ1971ዓ.ም እስከ 1991ዓ.ም ድረስ የመንግስት ግብር እየገበረ ቆይቶ ከወላጅ አባቴ ሞት በኋላ እስከ 2011ዓ.ም ድረስ የመሬት ግብር እየገበርኩበት የሚገኝ የሰነድ አልባ ይዞታ ያለኝ ሲሆን በዚህ ይዞታ በ1997ዓ.ም በተነሳው ጂአይኤስ ላይ ግንባታው የሚታይ ቤት አለበት፡፡ተጠሪ የአርሶአደር ይዞታዎችን በተመለከተ የይዞታ ማረጋገጫ አገልግሎት አሰጣጥን አስመልክቶ ባወጣው መመሪያ ቁጥር 20/2013 መሰረት በይዞታው ላይ አገልግሎት ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ ባለሁበት ወቅት አመልካች ይዞታዬን ለግሪን ኤርያ አገልግሎት የሚውል መሆኑን በፕላን በማያመለክትበት መኪያ ከድር ለምትባል ግለሰብ በግሪን ኤርያነት እንድትጠቀም በ27/6/12ዓ.ም ሰጥቷል፡፡ስለሆነም አመልካች ይዞታዬን በመንጠቅ ለ3ኛ ወገን አስተላልፎ የሰጠበት በ27/6/12ዓ.ም የፈጸመው ውል እንዲሰረዝ፤ የተሰጣቸው ግለሰቦች ይዞታዬን ለቀው ይዞታዬን እንዲመልስ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…
18
ክርክሩ በተጀመረበት በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ እና ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት አመልካች በተጠሪ ላይ መጋቢት 15 ቀን 2013 ዓም በተጻፈ በመሰረቱት ክስ ተጠሪ በአዲስ አበባ ከተማ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ስሙ ድጋፌ ሰፈር አካባቢ ኮንስትራክሽን ስራ የተሰማሩና ባለቤት ናቸው፡፡ ተጠሪ በድርጅታቸው ግቢ ውስጥ በርካታ ውሾች አሏቸው ተጠሪ በባለቤትነት የያዟቸውን ውሾች በአግባቡ መያዝና መጠበቅ ሲገባቸው ከጊቢ ውጪ በመልቀቃቸው አመልካች በብድር ብር የማረባቸውን ዶሮዎች በቁጥር 127 የሚሆኑትን በውሾቻቸው እንዲበሉ በማድረጋቸው ኪሳራ ደርሶብኛል፡፡ ተጠሪ ቀደም ሲልም 2 በጎችን አስበልተውብኝ ውሾቹን እንዲጠብቁ ቢነገራቸውም ሌላ ኪሳራ እንዲደርስብኝ አድርገዋል፡፡ በመሆኑም ተጠሪ ተገቢውን ጥበቃ ማድረግ ሲገባቸው በውሾቻቸው የተበሉትን 127 ዶሮዎች ግምት ብር 63,500(ስልሳ ሶስት ሽህ አምስት መቶ ብር) በዚህ ምክንያት ለወጣው ወጪና ኪሳራ ጭምር እንዲከፍሉኝ እንዲወሰንለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ጥሩ ንባብ…
15
ጉዳዩ ካሣን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን ተጠሪ ከሳሽ፤ የአሁን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ፤ በዚህ የሰበር ክርክር የሌለው የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ደግሞ 2ኛ ተከሳሽ ነበሩ፡፡ የአሁን ተጠሪ በሥር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- በ1996 ዓ.ም በኢንቨስትመንት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ ከጃሪ ስሬ ቀበሌ ውስጥ ለግብርና ልማት የሚውል 250 ሔክታር መሬት ተሰጥቶኝ ሳለማ ቆይቻለሁ፤ ከዚሁ ይዞታ ውስጥ 90 ሔክታር በአመርቲ ነሺ መብራት ሀይል ካሳው ተገምቶ ተወስዷል፤ ቀሪው 160 ሔክታር ፊንጭአ ስኳር ፋብሪካ ሸንኮራ ሊያመርትበት ወስዶታል፤ በዚሁ መሬት ላይ የተለያዩ ሰብሎችን በማምረት ያደረግኩት ማሻሻያ ተገምቶ ሊከፈለኝ ሲገባ ከመሬቴ ላይ አፈናቅሎኛል፤ ከመሬቱ ማግኘት የሚገባኝንም ጥቅም እና ገቢ አሳጥቶኛል፤ ስለሆነም በቦታው ለይ ያመረትኳቸው የተለያዩ ሰብሎች ግምት እና ለመንገድ ስራ ያወጣሁት ወጪ በድምሩ ብር 29,002,828.80 አመልካች እንዲከፍለኝ፤ የስር 2ኛ ተከሳሽ ደግሞ መሬቱን እንዳለማሁ እና አመልካች እንደወሰደው እያወቀ በውላችን አንቀጽ 6 ላይ የገባውን የዋስትና ግዴታ በመተው ያለካሳ እና ያለአንድም ምትክ መሬት እንድለቅ ያደረገ በመሆኑ ከአመልካች ጋር ተጠያቂ ነው ተብሎ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ ጥሩ ንባብ…
49
የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሾች በሥር ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ፡- ከሳሾች በተከሳሽ ድርጅት በጥበቃ አገለግሎት ሥራ እያንዳንዳቸዉ የተቀጠሩበትን ቀን እና ሲከፈላቸዉ የነበረዉን ደመወዝ በመጥቀስ መንግስት ህዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም የተከሳሽን ድርጅት በማገድ በኋላ ደግሞ የሥራ ፈቃዱን የሰረዘ በመሆኑ፣ መንግስት ለሰራተኞች ከሥራ ስንብት ጋር ተያያዥነት ያላቸዉን ክፍያዎች እና መብቶችን እንዲጠብቅላቸዉ በመወሰኑ፣ የሥራ ዉላችን በመቋረጡ ምክንያት የስራ ስንብት፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ እና ያልተጠቀምንበት የዓመት እረፍት በደመወዛችን ልክ ታስቦ ለእያንዳንዳቸዉ እንዲከፈለን እንዲሁም የስራ ልምድ ምስክር ወረቀት እንዲሰጠን እንዲወሰን በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡...
44
ክርክሩ የጀመረዉ ከፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሆኖ አመልካች ተከሳሽ ተጠሪዎች ከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል፡፡የክርክሩ መነሻ በአመልካች ላይ ተጠሪዎች በመሰረቱት ክስ ስሆን በአመልካች ተቋም 1ኛ ተጠሪ በብር 5¸347(አምስት ሽህ ሶስት መቶ አርባ ሰባት )ደመወዝ እየተከፈላቸዉ ከ2004 ዓም ጀምሮ ፤2ኛ ተጠሪ ብር 5¸040(አምስት ሽህ አርባ) ደመወዝ እየተከፈላቸዉ ፤3ኛ ተጠሪ ብር 5¸347(አምስት ሽ ሶስት መቶ አርባ ሰባት)አየተከፈላቸዉ ከ2012/2004 ስሰሩ የነበሩ መሆኑን፤4ኛ ተጠሪ ከ2001/1993 ጀምሮ በብር 5¸347(አምስት ሽህ ሶስት መቶ አርባ ሰባት )እየተከፈላቸዉ በአመልካች ድርጅት ዉስጥ ስያገለግሉ የነበረ መሆኑን የአመልካች ድርጅት ከህዳር 04 ቀን 2013 ዓም ጀምሮ መንግስት በወሰደዉ እርምጃ የአመልካችን የስራ ፈቃድ የሰረዘ ለዘለቄታ የተዘጋ ሰለሆነ የሰራተኞችን ከስንብት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ክፍያዎችና መብቶችን የ2 ወር ደመወዝ ፤የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፤ ያልወሰዱት የአመት እረፍት ፈቃድ ወደ ገንዘብ ተቀይሮ፤ስራ ስንብት ክፍያ፤የማስጠንቀቂያ ክፍያ እና ክፍያ ለዘገየበት እንዲከፍላቸው የስራ ልምድ እንድሰጣቸዉ እንዲወሰንላቸው ዳኝነት ጠይቋል፡፡ ...