ጉዳዩ የስራ ዉል መቋረጥ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ፤ የአሁኑ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡
ከመዝገቡ እንደሚታየዉ የተጠሪ ክስ የሚለዉ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ከፍተኛ የህዝብ አገልግሎት ሀላፊ ሆኜ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በወር ብር 15,304 እየተከፈለኝ እየሰራሁ እያለ በህገ ወጥ መንገድ በቀን 15/11/2011 ዓ.ም ከስራ ያሰናበተኝ ስለሆነ ወደ ስራዬን እንዲመልሰኝ ወይም በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሰረት ክፍያዎች እንዲከፍለኝ በማለት ዳኝነት የጠየቀች ሲሆን አመልካች በበኩሉ ተጠሪ ደንበኞች ያላመጡትን ሂሳብ እንዳመጡ በማድረግ የሌላቸውን የሂሳብ ሚዛን ወይም ቀሪ ሂሳብ በመፃፍ የማይገባቸውን ጥቅም እንዲያገኙ አድርጋለች፣እንዲሁም ይህንን የድርጅት ሰነድ አስመስላ በመስራት የወንጀል ድርጊት ፈጽማለች፣በአጠቃላይ ወደ ባንኩ የመጣ ገንዘብ እና ከባንኩ የወጣ ገንዘብ በሌለበት በአየር ላይ የገቢና የወጪ ገንዘብ እንዳላቸው በማስመሰል ጽፋላቸዋለች፡፡ስለዚህ ባንኩ ማግኘት ያለበት ጥቅም ለሶስተኛ ወገን ጥቅም እንዲውል አድርጋለች፣ይህ ደግሞ በአዋጅ ቁ/1156/2011 አንቀጽ 27/1/መ መሰረት ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውል እንዲቋረጥ የሚያደርግ ጥፋት በመሆኑ ተጠሪ የተሰናበተችዉ በህጋዊ መንገድ በመሆኑ የካሳ፣የአገልግሎት፣የማስጠንቀቂያ እና ሌሎች ክፍያዎች አይከፈላትም፣ሌሎች በአንቀጽ 36 እና 38 የተጠየቀው ክፍያ ክሊራንስ ካጠናቀቀች በኋላ የሚከፈል ክፍያ ነው በማለት ተከራክረዋል፡፡…………………