ተጠሪ ባቀረቡት አቤቱታ ከሳሽና ተከሳሽ በባልና ሚስትነት አብረን ስንኖር ተማሪ ጌጤ ገብሬ እድሜ 16፣ ተማሪ ጥሩ አየሁ እድሜ 14፣ ተማሪ አማረ ገብሬ እድሜ 10 የሆኑ ልጆች ወልደን ሀብት አፍርተን መግባባት ባለመቻላችን በሽማግሌ ከፊል ሀብቴን አካፍሎ ከፊሉን ከልክሎኛል፤ ስለሆነም አዋሳኙ በክሱ የተጠቀሰውን መሬት እንዲያካፍለኝ ፣ የፍልጥ ባህር ዛፍና ጌሾ በግምቱ መሰረት እንዲያካፍለኝ፣ 100 ዚንጎ የገጠር ቆርቆሮ ቤት ግምቱ 33,000.00 (ሰላሳ ሶስት ሺህ) ከሆነው ከግማሽ ድርሻየ ላይ ብር 13,000.00 (አስራ ሶስት ሺህ) የሰጠኝ ሲሆን ቀሪ ብር 3500.00 (ሶስት ሺህ አምስት መቶ) እንዲከፍለኝ፣ እንዲሁም የልጅ ቀለብ እንዲከፍል እንዲወሰን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ መልካም ንባብ…..