Login
Federal Supreme Court of Ethiopia
Search
  • Home
  • About Us
    • President Message
    • President
      • Current President
      • Former President
    • Vice President
      • Current Vice President
      • Former Vice Presidents
    • History and Traditions
    • Judges
      • Former Judges
    • Vision Mission and Mandate
    • Judicial Administration Council
  • Court Services
    • Registry Services
      • Court Forms and Fees
    • Daily Court Trial Schedule
    • Case Tracker
    • Requesting Court Documents
      • Disposed Cases
    • Court Annexed Mediation
    • Interpretation Services
    • Legal Support
      • Child Justice Project Office
      • Public Defenders Office
  • Going to Court
    • Visiting the Court
      • What Can I see and Do?
    • Courtroom Etiquette
      • Courtroom Rules
    • Criminal: Information for the Accused Person
    • Civil Disputes: Information for Parties
    • Representing Yourself
    • Information for Witness
    • Information for Lawyers
    • FAQ
  • Digital Law Library
    • Annual Reports
    • State of the Judiciary
    • Monthly Judges Seminar
    • Federal Laws
    • Archives
    • Publications
      • Journal
      • Federal Cassation Decision Series
      • Newsletter
    • Judgments
      • Cassation Decisions
      • Supreme Court Decisions
  • News Media
    • Announcements
    • Interactives
      • Photos
      • Video
    • Services for Media
      • Press Releases
      • Press Conference
      • Media Advisories
      • Speeches
    • NEWS
  • Contacts
    • Federal Supreme Court
    • Federal High Court
    • Federal First Instance Court
    • Contact and Feedback
  • Tender
  • Judgement Execution Directorate
    • About Judgement Execution Directorate
    • Auction
  • Vacancy
  • Child Justice Project

እነ ወ/ሮ ተናኜ ሞላ ብርሐኔ(3ሰዎች) እና አቶ ሳሙኤል ተገኝ ኃይሌ የሰበር መዝገብ ቁጥር - 257774

Wednesday, June 4, 2025 5126

ጉዳዩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን በስር ፍርድ ቤት አመልካቾች ተጠሪዎች ተጠሪ ደግሞ አመልካች በመሆን ተከራክረዋል፡፡በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካቾች ላይ ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ ወላጅ አባት ሟች አቶ ኃይሌ ተገኝ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ኑዛዜ የፈፀሙ መሆኑን አመልካች የሟች ብቸኛ ልጅ መሆኑን ለተጠሪዎች ኑዛዜ በመፈፀም ከሚደርሰው ድርሻ ከሩብ በላይ ጉዳት እንዲደርስበት ያደረገ በመሆኑ ከኑዛዜው እንድነቀል ተደርጊያለሁ ስለዚህ ሟች ፈፀመውታል የተባለው ኑዛዜ እንዲሻርልኝ የሚል ነው፡፡

ከአመልካቾች በኩል የተሰጠው መልስ በአጭሩ ኑዛዜው በህግ ፊት የፀና ነው ሟች ማንም ሰው ሳያስገድዳቸው በራሳቸው ፍቃድና ፍላጎት በትክክለኛ አእምሮ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ፊት ቀርበው የኑዛዜው ሰነድ ተነቦላቸው በምስክሮች ፊት የቁም ኑዛዜ ያደረጉ ስለሆነ ኑዛዜው ህጋዊ መሆኑን ሟች ጥር 29 ቀን 2012 ዓ.ም ባደረጉት የቁም ኑዛዜ በተራ ቁጥር 2፣ 3 እና 4 የተጠቀሱት የኑዛዜ ተቀባዮች በሟች ስም የሚጠሩ መሆናቸውን ኑዛዜ አድራጊው ልጆች ናቸው ብሎ የተቀበላቸውን ግለሰቦች 3ኛ ወገን ተወላጆች ስላልሆኑ የኑዛዜ ስጦታ ሊበረከትላቸው አይገባም ብሎ መከራከር የሟችን በንብረቱ ላይ የማዘዝ መብትን የሚጥስ በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የኑዛዜ ተቀባዮች ተወላጆች አይደሉም ቢባል እንኳን የኑዛዜ ስጦታ ለተወላጅ ብቻ የሚሰጥ መብት ነው የሚል የህግ ድንጋጌ ያለመኖሩን አመልካች ሟች አባታቸው ባደረጉት ኑዛዜ የኑዛዜ ተቀባይ ነው እንጂ በኑዛዜው ከውርስ አልተነቀለም፡፡ አመልካች ከጠየቁት ዳኝነት አንፃር በኑዛዜው የሚደርሳቸውን ድርሻ በትክክል ለይተው አልጠየቁም የሟች ቁም ኑዛዜ ፈራሽ የሚሆንበት በቂ ምክንያት ስላልቀረበ የአመልካች ክስ ውድቅ እንዲደረግ የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ…  

Read more

ወ/ሮ ሰላማዊት ያደሳ እነ አቶ ፀሀዬ ጌታቸው(2ሰዎች) የሠ/መ/ቁጥር 256923

Wednesday, June 4, 2025 4778

ጉዳዩ አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር እንደባልና ሚስት አብረዉ በኖሩበት ጊዜ ያፈራነዉ ንብረት ነዉ ያሏቸዉን ንብረቶች ለመካፈል ያቀረቡት ክስ አስቀድሞ ዉሳኔ ባገኘ ጉዳይ ለሁለተኛ ጊዜ የቀረበ ክስ ነዉ በሚል ዉድቅ በመደረገ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል በቀረበ የሰበር አቤቱታ መነሻ የተደረገዉን ክርክር የሚመለከት ነዉ፡፡ ክርክሩ በተጀመረበት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች በ1ኛ ተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ የአሁን 2ኛ ተጠሪ ጣልቃ በመግባት የተከራከሩ ሲሆን የክሱ ይዘት በአጭሩ - ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ከቀን 15/04/1999 ዓ.ም ጀምሮ እንደባልና ሚስት አብረን ስንኖር ያፈራነው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ክልል ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 121 የይዞታ መለያ ቁጥር AA000070806106 የሆነና በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ስፋቱ 403 ካሬ ሜትር የሆነ 8 የሚከራዩ ሰርቪስ ቤቶች እና 4 ክፍል ያለው ዋና ቤት እና ቦታ የጋራ ሀብት ስለሆነ ተጠሪ ድርሻዬን እንዲያካፍለኝ በማለት ሌሎች ንብረቶችንም እንደዚሁ በመጥቀስ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡   መልካም ንባብ…

Read more

እነ አቶ ዮሐንስ ገ/ሚካኤል(5ሰዎች) እና ወ/ሮ ሃና ደርሶልኝ(2ሰዎች) የሰበር መዝገብ ቁጥር - 256463

Wednesday, June 4, 2025 5510

አመልካቾች ሚያዚያ 2 ቀን 2015 ዓ.ም በተፃፈ የመቃወም አቤቱታ ሟች አባታቸው አቶ ገ/ሚካኤል ኃ/ማርያም በህይወት እያሉ እንዲሁም አባታቸው ከሞቱ በኃላ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ የሆኑት፣ አመልካቾችና የ 96 አመት የሆኑት የግራ ቀኙ እናት ጋር በአልኮልና በለስላሳ ማከፋፈያ እንዲሁም በሸቀጣሸቀጦች ጅምላ ንግድ ስራ ተሰማርተው በቁጥር ስምንት የሆኑ የተለያዩ ተሸከርካሪዎች፤ ደምቢዶሎ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ሆቴል፣ የቡና ማበጠሪያ፣ የመጠጥ ማከፋፈያ፣ የመኖሪያ ቤትና መጋዘን፤ በቡና ግብይት ላይ የነበረ አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ብር፣ በአዋሽ ባንክ ያለ 50 የአክስዮን ድርሻ በጋራ ያፈሩ መሆኑንና ተጠሪዎች ጋብቻ ሲፈፅሙ እነዚህ ንብረቶች የአመልካቾች መሆናቸውን በጋብቻ ውላቸው ተስማምተዋል፡፡ እነዚህ ንብረቶች ከፊሎቹ ባሉበት ከፊሎቹ በሽያጭ ሆነ በሌላ መንገድ እየተለዋወጡና እየተቀላቀሉ ብዛታቸው 16 የሆኑ በተጠሪ ስም የተመዘገቡ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፤ በተጠሪ ስም የተመዘገቡ በአዋሽ ባንክ፣ በኦሮሚያ ባንክ፣ በህብረት ባንክ ያሉ አክስዮኖች፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በአዋሽ ባንክ፣ በህብረት ባንክ፣ በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ፣ በኦሮሚያ ባንክ ተጠራቅሞ የሚገኝ ገንዘብ እና ተሸከርካሪዎች በቤተሰብ የተፈሩና በተጠሪዎች የጋብቻ ውል ላይም የቤተሰብ ንብረቶች መሆናቸው ተረጋግጦ እያለ ተጠሪዎች ከዚህ በተቃራኒ በሰበታ ከተማ የሚገኘውን በ 612 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ቤት፣ በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ የሚገኘውን መኖሪያ ቤት እንዲሁም በዚህ ከተማ በ 2,000 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሆቴል ን በመተው ሌሎችን ንብረቶች የተጠሪዎች የጋራ ንብረት ነው በማለት ያስወሰኑ በመሆኑ ውሳኔው ቀሪ እንዲሆን በማለት የመቃወም አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ…

Read more

ቻይና ኮሙኒኬሽን ኩባንያ ግንባታ ወንጪ ደንዲ ኢኮቱሪዝም ፕሮጀክት እና ማንዴሳ ጪብሳ የሠ/መ/ቁጥር 256412

Wednesday, June 4, 2025 5213

ጉዳዩ የጉዳት ካሳ ክፍያን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ደግሞ በተከሳሽነት ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ፡- አመልካች ከደንዲ ሀይቅ እስከ ወንጪ ሀይቅ ያለው መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ኮንትራክተር በመሆን በሚሰራበት ወቅት በደንዲ ወረዳ ገ/ጥራንጉ ሹቤሶሌ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከሚገኘው ስፋቱ አራት ሄክታር በሆነው የእርሻ ይዞታዬ ላይ መንገድ ለመገንባት የቆፈረውን አፈር ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም በተሸከርካሪዎች ጭኖ በመድፋት በመሬቱን ገደላማ በማድረግ ከጥቅም ውጪ በመሆኑ በመሬቱ ላይ ተዘርቶ የነበሩትን የሰነፍ ቆሎ፤ገብስ እና ሚስር ቡቃያዎችን፤ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ በቁጥር 5,900.00(አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ባህር ዛፍ፤10 እግር ጥድ፤እንዲሁም 900 እግር ቀርከሃ ስላወደመብኝ የእጽዋቶቹ እና የሰብል  ግምቱ ለወደፊት ያገኙ የነበረውን የ15 አመት ጥቅም በድምሩ ብር 9,823,000 (ዘጠኝ ሚሊየን ስምንት መቶ ሃያ ሶስት ሺ) የጉዳት ካሳ ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዲከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ከሰዋል፡፡መልካም ንባብ…

Read more

እነ አቶ አመድ ሙሜ(2ሰዎች)የእና ወ/ሮ አሚናት ኡስማንሰ/መ/ቁጥር 254020

Wednesday, June 4, 2025 4856

ጉዳዩ የገጠር መሬት ውርስን የሚመለከት ሲሆን ጉዳዩ በጀመረበት የሀረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን አመልካቾች ተከሳሽ፤ የአሁን ተጠሪ አውራሽ የሆኑት ወ/ሮ ከዲጃ ዑመር ከሳሽ ነበሩ፡፡ የአሁን ተጠሪ አውራሽ ያቀረቡት ክስም፡- ሟች አባታቸው በ1966 ዓ.ም በሞት የተለዩ መሆኑን፤ሟች አባታቸው እርሳቸውንና ሟች ወንድማቸውን አቶ ዘከሪያ ኡመር የወለዱ መሆኑን፤ሟች ወንድማቸውም የአሁን አመልካቾችን እናት አግብቶ ሲኖር ቆይቶ ልጅ ሳይወልድ እና ሳይናዝ የሞተ መሆኑን፤ ለክርክር መነሻ የሆነው በአራት ቦታ የሚገኘው የገጠር መሬት የሟች አባታቸው እና ክፍፍል ያልተፈጸመበት እንዲሁም ከሟች ወንድማቸው ጋር ሲጠቀሙበት የቆዩ መሆኑን፤ ሟች ወንድማቸው ከሞተ በኋላም የአሁን አመልካቾች እናት እየረዳቻቸው በመሬቱ ስትጠቀም እንደነበር፤ እርሷ ከሞተች በኋላ መሬቱን ተጠሪዎች እንዲለቁ ቢጠየቁ ፈቃደኛ ሊሆኑ አለመቻላቸውን ጠቅሰው መሬቱን ለቀው እንዲያስረክቡኝ እና ከመሬቱ የተገኘውን ጥቅም ጨምረው እንዲከፍሉኝ የሚል ነበር፡፡ ተጠሪዎች ለክሱ ባቀረቡት መልስ ክሱ በይርጋ የተቋረጠ ነው፡፡ ለክርክር መነሻ የሆነውን መሬት እናታችን መብት በመመስረት ንብረትነቱ የመንግስት በሆነ መሬት ላይ ከከሳሽ ወንድም ጋር ባልና ሚስት በመሆን ጋብቻው በሞት ቀሪ እስከሆነበት ጊዜ ድረስ መብት ፈጥረው እየተጠቀሙ የቆዩ በመሆኑ ክሱ ውድቅ እንዲደረግልን በማለት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ….

Read more
FirstPrevious45678910111213NextLast

Categories

  • 2011 Expand/Collapse
  • 2012 Expand/Collapse
  • 2013 Expand/Collapse
    Contacts
  • TEL : +251-11-1-55-34-00 /
  •          +251-11-1-11-04-32
  • Fax : +251 111-550278 /
  •          +251 111-565583
  • Email : fscpublicrelation@gmail.com
  • Address: 6 Killo , Addis Ababa, Ethiopia
Quick Links
  • About Us
  • E-Filing 
  • Calendar
  • Press Release
  • Case Tracker
  • FAQ
    Connect With Us
  • Privacy Policy
  • |
  • Site Map
Copyright © The Federal Supreme Court of Ethiopia- All rights reserved
Powered By Bsquare IT Solutions