ጉዳዩ የቤት ሽያጭ ውል አፈጻጸም የሚመለከት ጉዳይ ነዉ፡፡የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ፡- ክርክሩ የተጀመረው በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን በአሁኑ አመልካቾች ላይ ባቀረበው ክስ አመልካቾች በዱራሜ ከተማ ውስጥ በ460.6 ካ.ሜ ላይ ያላቸውን መኖሪያ ቤት በብር 2,250,000.00 በቀን 24/01/2012 ዓ.ም በተደረገው ውል ሽጠውልኝ ቀብድ ብር 1,000,000 መቀበላቸዉን እንዲሁም የተጠሪ ወኪል በ1ኛ አመልካች የባንክ ሂሳብ ብር 800,000.00 ገቢ በማድረጋቸው በአጠቃላይ ብር 1,800,000.00 የተቀበሉ መሆኑን ገልጾ አመልካቾች በውሉ መሰረት ቤቱን እንዲያስረክቡ እንዲወሰን ይህ ካልሆነ በፍ/ብ/ህ/ቁ.1885(2) መሰረት የተቀበሉትን ቀብድ አጠፌታ እና ገንዘቡ ተከፍሎ እስከሚያልቅ ህጋዊ ወለድ ከወጪና ኪሳራ ጋርእንዲከፍሉ እንዲወሰን በማለት ዳኝነት የጠየቀ ሲሆን አመልካቾች በበኩላቸዉ ባቀረቡት መልስ የቤት ሽያጭ ውል ሲደረግ ቀብድ መሆኑ በውሉ ስላልተገለጸ ቀብድ ነው በሚል አጠፌታ መጠየቅ ተገቢ ስላለመሆኑ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 26996 አስገዳጅ የህግ ትርጉም መስጠቱን፤በውልም ሆነ በወኪላቸው ገንዘብ ያልተቀበሉ ከመሆኑም በላይ የሽያጭ ውሉ በሚመለከተው አካል ፊት ያልተደረገ እና ያልተመዘገበ የማይፀና ረቂቅ ውል በመሆኑ ቤቱን የማስረከብ ግዴታ የለብንም፣የቀብድ ውል የሌለና የባንክ ሰነድ ቀብድ መሆኑን የሚገልጽ አይደለም፣ክሱ ውድቅ እንዲደረግ በማለት መከራካራቸዉን መዝገቡ ያሣያል፡፡ መልካም ንባብ…..