ጉዳዩ የስራ ስንብትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ጽፈው ባቀረቡት ክስ በአመልካች ሆስፒታል ውስጥ በኤክስፐርት ሜዲካል ስፔሻሊስት (ሰርጀሪ) የስራ መደብ ላይ በወር ብር 49,000.00፣ ሃርድሺፕ አሎዋንስ 19,124.00፣ እንዲሁም ለእያንዳንዱ የቀዶ ጥገና ህክምና ብር 1,000.00 እየተከፈላቸዉ ከቀን ግንቦት 07 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ አመልካች የካቲት 19 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ የሁለት ወር የማስጠንቀቂያ ጊዜ በመስጠት ከስራ ከህግ ውጪ ከስራ ያሰናበታቸዉ መሆኑን ጠቅሰዉ የተለያዩ ክፍያዎች እንዲከፈላቸዉ ይወሰንላቸዉ ዘንድ የጠየቁትን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡መልካም ንባብ……