ጉዳዩ ከዉል ዉጭ የሆነ ኃላፊነትን መነሻ ያደረገ የካሣ ክርክር መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡አመልካች በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በስር ተከሳሾች ዓለማየሁ መኮንን እና ስለሽ አዱኛ ላይ በመሰረቱት ክስ አመልካች በተከሳሽነት ጣልቃ ገብቶ የተከራከረ ነዉ፡፡የክሱም ይዘት ተጠሪ ንብረትነቱ የደንበኛዉ ለሆነ የይርጋ ጨፌ ደረጃ 1 ቡና ከአዲስ አበባ እስከ ጅቡቲ እስከሚጓጓዝ ድረስ እስከሚደርስ በጉዞ ላይ ለሚደርስበት ጉዳት የመድን ሽፋን ሰጥቶ ንብረትቱ የተከሳሾች በሆነ በሰሌዳ ቁጥር 03-00698/08661 በሚታወቅ ተሽከርካሪ 300 ኬሻ ወይም 18,000.00 ኪሎ ግራም ቡና ተጭኖ ሲጓዝ በቀን 13/06/2007 ዓ/ም በአፋር ክልል አዳይቱ አካባቢ ተሽከርካሪ በመገልበጡ 26 ኬሻ ቡና ላይ ጉዳት ድርሶበት በድንጋይ እና ከአፈር ጋር በመቀላቀሉ ለኤክስፖርት እንዳይዉል ሆኖ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ በዚህ ምክንያት ተጠሪ ካሳ ብር 276,963.72 ከፍሏል፡፡ሉና ማስመሪመሪያ ብር 207.20፣ለጥበቃ ብር 4000.00፣ለጉልበት ሠራተኛ ብር 1-875.00፣ለቡና ማፈሻ ሸራ ብር 600.00 በድምሩ ብር 283,045.92 የተከፈለ ሲሆን ከዚህ ላይ የ26 ኬሻ ቡና ቅሪት ለተጠሪ ሠራተኞች ተሸጦ የተሰበሰበ ብር 39,338.90 ተቀንሶ የሚቀረዉን ብር 243,707.02 ክፍያ ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር እንዲከፍሉ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡
የስር ተከሳሾች ለክሱ በሰጡት መልስ ጉዳቱ የደረሰዉ በተሽከርካሪያቸዉ ጥፋት ሳይሆን በአመልካች ተሽከርካሪ ጥፋት እንደሆነ በመግለጽ አመልካች በክርክሩ እንዲገባ እንዲታዘዝ ጠይቀዋል፡፡ እንዲሁም ለደረሰዉ ጉዳት ኃላፊነት እንደሌለባቸዉ፤የተጫነዉን ቡና ደረጃ 2 ሆነ በደረጃ 1 ካሳ መሰላቱ ተገቢ እንዳልሆነ ፣ቅሪቱ በተገቢዉ ዋጋ እንዳልተሸጠና ሌሎች አመልካች እንዲተካለት የጠየቃቸዉን ወጪዎች በተመለከተ የተጋነነ እንደሆነ በመግለጽ ተከራክረዋል፡፡መልካም ንባብ……….