ለዚህ ሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የሥራ ክርክር ሲሆን የተጀመረው በዲማ ወረዳ ፍ/ቤት ነው፡፡ በዚህ ፍ/ቤት ተጠሪ ከሳሽ ሲሆን የአሁን አመልካች ደግሞ ተከሳሽ ነበሩ፡፡ የሰበር አቤቱታዉ የቀረበዉ በዲማ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁ 0028/2014 ጥቅምት 14 ቀን 2014 ዓ.ም ተሰጥቶ በአኝዋ ብሔረሰብ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት እና በጋምቤላ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በተሰጡ ዉሳኔዎች የጸናዉ ዉሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በሚል ነዉ፡፡
ተጠሪ ሚያዚያ 28 ቀን 2014 ዓ/ም በተጻፈ የክስ አቤቱታ ያቀረቡት ክስ ይዘት፡- አመልካች ከሕግ ዉጪ ከሥራ ስላሰናበታቸዉ ወደ ሥራ እንዲመለሱ፤ የተቆረጠ ደመወዝ እና ለደረሰባቸዉ የሞራል ዉድቀት ካሣ እንዲከፈላቸዉ የሚጠይቅ ነዉ፡፡ መልካም ንባብ……..