Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

ሆሆተ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እናወ/ሮ ዘውዲቱ በዳሶ የሰ/መ/ቁ 256580

በከሳሽ የቀረበው ክስ ይዘት በአጭሩ ከአመልካች ፋብሪካ በሚወጣው መርዛማ ጭስ ምክንያት የግል ንብረቴ የሆነውን የሆላንድ ጥጃ ግምቱ ብር 10,000.00 (አስር ሺ) እና የሆላንድ የወተት ላም ብር 170,000.00 (አንድ መቶ ሰባ ሺህ) መስከረም 06 ቀን 2014 ዓ.ም ጥጃዋ ወዲያውኑ ስትሞት ላሚቷ መጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ሞታለች፡፡ስለሆነም የሆላንድ ላሟ ከነጥጃዋ የዋጋ ግምት በድምሩ ብር 180,000.00 (አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ) የሚያወጡ ሲሆን ላሟ ከመታመሟ በፊት በቀን 27 ሊትር ወተት የምትሰጥ ሲሆን የአንድ ሊትር ወተት ዋጋ ብር 40 የሚሸጥ በመሆኑ በቀን ብር 1080 (አንድ ሺህ ሰማኒያ) ሲሆን በወር ብር 32‚400 (ሰላሳ ሁለት ሺህ አራት መቶ ብር) ገቢ ሳገኝ የነበረ ሲሆን ላሟ ለሶስት ወር ከ 9 ቀናት ታማ ምርት በማቆም ስትታከም በነበረበት ያጣሁት ገቢ ብር 106,920.00 (አንድ መቶ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ) ጨምሮ በአጠቃላይ ብር 286 920.00 (ሁለት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺ ዘጠኝ መቶ ሃያ  እንዲወሰንልኝ የሚል ነው፡፡ተጠሪም በሰጡት መልስ ፋብሪካው ሲቋቋም በአካባቢው ላይ ተጽዕኖ የማያደርስ ስለመሆኑ ተረጋግጦ ነው፣ የክርክር መነሻ የሆኑት ጥጃ የሞተችበት እና ላሚቷ የታመመችበት ጊዜ የአመልካች ፋብሪካ ስራ ያልጀመረ በመሆኑ ለላሞቹ ሞት ምክንያት የደረሰው ጉዳት ከፋብሪካው የወጣ ጭስ ሊሆን የማይችል በመሆኑ አመልካች ለተጠሪ ጥጃ እና ላም መሞት ኃላፊነት የለበትም፤ካሳ ለመክፈልም ሊገደድ አይችልም በሚል የቀረበው ክስ ውድቅ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…

Previous Article የኢትዮጵያ መድን ድርጅት እና አቶ አበራ ተፈሪ የሰ/መ/ቁጥር 254101
Next Article ወ/ሮ ሙርሽዳ ሁሴን እና ወ/ሮ አልፊያ ሁሴን (13) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 257243
Print
4924

Documents to download

  • 256580(.pdf, 1.05 MB) - 665 download(s)

«June 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
25262728293031
1234567
891011121314
15161718192021
22232425262728
293012345

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ...

78

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንትነትና ምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ተገኝተው አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይትና ምልከታ አድርገዋል።

ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ...

97

‎በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት የተሰራ ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል (One way mirror) በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት በይፋ ስራ ጀምሯል።

ለሶሻል ወርክ ባለሞያዎች በተዘጋጀ የስልጠና ማንዋል ረቂቅ...

119

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት በፍትህ ስርዓት ውስጥ የሚያገለግሉ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሞያዎችን ሚና ለማጎልበት የሚያግዝ የስልጠና ማንዋል የመጨረሻ ረቂቅ ሰነድ ላይ የውይይት እና የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሂዷል፡፡ 

‎የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን...

106

በኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ እና የጄሲኢ (JCE) ሰብሳቢ በሆኑት በክብርት ዳኛ ሱዛን ኞኪ ንዱንጉ የተመራው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ላለፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር አጠናቋል።

1345678910Last