Selam Warga
/ Categories: CASSATION

ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ በአዋጅ ቁጥር 322/1995 መሰረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተደራጀባቸው ክልሎች ያሉ የክልል ከፍተኛ ፍርድ ሰ/መ/ቁ 271003 ቤቶች

ከክርክሩ መረዳት እንደሚቻለዉ አመልካች ባቀረቡት ክስ በተጠሪ ተቋም ዉስጥ መምህር ስሆን ከተጠሪ ጋር ህዳር 30 ቀን 2009 ዓ/ም በተደረገ የአገልግሎት ስምምነት ዉል ለአራት ዓመት እስከ ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ ከስራ ግዴታ ዉጪ በመሆን የሶስተኛ ድግሪ ስኮላርሽፕ ፕሮግራም ትምህርቴን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተምሬ ለስምንት ዓመት አገልግሎት ለመስጠት ፤ተጠሪ ደግሞ በየወሩ ደመወዝ እና የተለያዩ ክፍያዎችን ሊከፍለኝ የተስማማን እና ይህ ስምምነት በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርቱ የማያልቅ ከሆነ የሚሻሻልበትን አግባብ ለማመቻቸት የተስማማን በመሆኑ በዚህም መሰረት በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርቱን በግዜዉ መጨረስ ስላልቻልኩ ዉሉ እንዲራዘም ጠይቄ ተጠሪ ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ/ም ለሁለት ዓመት ማለትም ከነሐሴ 03 ቀን 2014 ዓ/ም አስከ ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ዉሉን ያራዘመ በመሆኑ ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ/ም የማራዘሚያ ዉል ፈጽመናል ፡፡ 

Print
1928

Documents to download

  • 271003(.pdf, 1.16 MB) - 61 download(s)

«October 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
2829301234
567891011
12131415161718
19202122232425
2627282930311
2345678

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2019 በጀት ዓመት መደበኛ...

1

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2019 በጀት ዓመት መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ዛሬ ተከናውኗል። በመርሃ-ግብሩ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢያለ፣ የዳኝነት ሥራ ዘመኑ በሦስቱም የፌደራል ፍርድ ቤቶች በይፋ መጀመሩን አብስረዋል። ምክትል ፕሬዝዳንቷ በመክፈቻ ንግግራቸው፣ ባለፈው የአምስት ዓመት (2014–2018) ስትራቴጂክ ዕቅድ ዘመን ውጤታማ አፈጻጸም የተመዘገበበት እንደነበር ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የትራንስፎርሜሽን ማዕቀፍ በአገራዊ...

52

አገራዊ የሕግ ተርጓሚዎች መድረክ በባህር ዳር ከተማ ባካሄደው ልዩ ጉባኤ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶችን የ2019 - 2021 ዓ.ም የሚመራ የጋራ የትራንስፎርሜሽን ማዕቀፍ አጽድቋል። ማዕቀፉ የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ ፍርድ ቤቶች በጋራ ሊያሳኩ በሚችሏቸው የዳኝነት ማሻሻያዎች ላይ የጋራ ርዕይ፣ የተቀናጀ አቅጣጫና በውጤት የሚመራ የአፈጻጸም ሥርዓት ለመፍጠር ያለመ ነው።

የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር የፍርድ ቤቱን ዲጂታላይዜሽን አደነቁ

345

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ክብርት ሶፊ ፍሮም ኤምስበርገር በዛሬው ዕለት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሰሩ የዲጂታላይዜሽን ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡ አምባሳደሯ በህብረቱ ድጋፍ የተቋቋሙ ዘመናዊ የችሎት አዳራሾችንና የዲጂታል የመዝገብ አያያዝ ሥርዓቶችን ተመልክተው አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

በወንጀል ውስጥ ገብተው የተገኙ ሴቶችን አስመልክቶ...

518

በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአውሮፓ ህብረት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት፣ በወንጀል ውስጥ ገብተው የተገኙ ሴቶች በዳኝነት ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን ተጋላጭነቶች ታሳቢ ያደረገ የስርዓተ-ችሎት ማጣቀሻ ሰነድ (Bench book) ላይ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

1345678910Last