Anonym / Saturday, October 3, 2020 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation በአማጋ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጮራ የጋዝና ኬሚካል ውጤቶች ፋብሪካ፣ሂክማ የፈሳሽ ሳሙና ማምረቻ ኃ/የተ/የቡድን ኢንተርፐራይዝ እና ሌሎች የሰ-መ-ቁ 175155 ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የፌ/ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ139054 በ29/5/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ፤ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 172510 በ26/7/11ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ ቅር በመሰኘት በ7/8/11ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረበ ነው፡፡የጉዳዩ አመጣጥ አመልካች በስር የፌ/ከ/ፍ/ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረበው የተሻሻለ ክስ ለከሳሽ በንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/98 መሰረት ለሁለት አይነት የበረኪና ምርቶች ማለትም ለትልቁ ባለ 800 ሚሊ ሊትር SEDEX እንዲሁም ለትንሹ ባለ 300 ሚሊ ሊትር SEDEX በምዝገባ ቁ.LTM/0189/2005 እና LTOW 0186/2005 በቅደም ተከተል የተመዘገበ እና እስከ 28/10/12ዓ.ም ድረስ ጸንቶ የሚቆይ የንግድ ምልክት ምዝገባ ሰርተፍኬት ከኢትዮጵያ አእምሮአዊ ንብረት ጽ/ቤት በ2005ዓ.ም የተሰጠ ሲሆን የንግድ ምልክቶቹ የተመዘገቡት እና ፈቃድ የተሰጠው በቃል እና በስእል(በቅርጽ) (በምስል) ከመሆኑም ባሻገር የቀለም አይነቱ በአዋጁ አንቀጽ 5(2) መሰረት ጥቁር እና ነጭ ነው፡፡ የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ አላማው የተለያዩ እቃዎችን በማምረትና በማከፋፈል ወይም አገልግሎት በመስጠት የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን መልካም ስም እና ዝና ለመጠበቅ እንዲሁም በተመሳሳይ ስራዎች እና አገልግለቶች መካከል ማሳከርን ለማስወገድ እና አንድን ምርት/እቃ ወይም አገልግሎት በቀላሉ ለመለየትና የንግድ ምልክቱ በአገልግሎት ተጠቃሚው (ኮንሲዩመሩ) ላይ ግርታ እንዳይፈጥር ለማድረግ ነው፡፡………… Previous Article እነ አቶ ኪሮስ መኮንን፣አቶ ዳዊት አማረ እና አቶ ኪሮስ ዳኘው የሰ-መ-ቁ- 188807 Next Article እነ አቶ አንበሳው አፈወርቅ እና አቶ አበበ ተገኝ የሠ-መ-ቁጥር 185708 Print 19294 Documents to download በአማጋ ኃ-የተ-የግ-ማህበር ጮራ የጋዝና ኬሚካል ውጤቶች ፋብሪካ፣ሂክማ የፈሳሽ ሳሙና ማምረቻ ኃ-የተ-የቡድን ኢንተርፐራይዝ እና ሌሎች የሰ-መ-ቁ 175155(.pdf, 537.98 KB) - 1625 download(s)
BRICS Chief Justices' Forum Concludes BRICS Chief Justices' Forum Concludes Sunday, September 6, 2026 1 September 6, 2026 (Federal Supreme Court) The BRICS Chief Justices forum, hosted by the Supreme Court of India from September 4 to September 6, 2026, has concluded. Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ... Monday, August 31, 2026 47 ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሠራተኞችን መብት፣ ግዴታና የዲሲፕሊን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናን ጨምሮ ልዩ ልዩ መርሃ-ግብሮችን በማካሄድ ተጠናቋል። Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመታዊ የሰራተኞች መድረክ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመታዊ የሰራተኞች መድረክ... Monday, August 31, 2026 41 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሰራተኞች መድረክ በዛሬው ዕለት መካሄድ የጀመረ ሲሆን የፍርድ ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሂዷል። Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በቀጣይ የአምስት... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በቀጣይ የአምስት... Friday, August 28, 2026 72 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክቡራን ዳኞች የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን የቀጣይ አምስት ዓመታት (2019-2023) የስትራቴጂክ ዕቅድ ረቂቅ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ አካሂደዋል። Read more