Selam Warga / Wednesday, June 4, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ብርሃን ባንክ አ/ማ እና ብርሃን ባንክ መሠረታዊ የሠራተኞች ማሕበር የሰ/መ/ቁ. 263727 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበር፡፡ ተጠሪ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ/ም ጽፎ ባቀረበው ክስ አመልካች ድርጅት ለሁሉም ሰራተኞች በሚል በተጻፈ ጥቅማጥቅም የተወሰነ መሆኑ ተገልጾ እያለ የቤት አበል በተለምዶ በጽሕፈት መደብ ላይ ያልሆኑ /non-clericals/ የሚሰሩ ሰራተኞች አልከፍልም ማለቱ የእኩልነት መብት የሚጥስ በመሆኑ የቤት አበል እንዲከፈል እንዲወሰን ዳኝነት ጠይቋል፡፡ አመልካች በሠጠው መልስ ደብዳቤው ለሁሉም ሠራተኞች በሚል የተጻፈው የተለያየ የጥቅማጥቅም ሁኔታዎች የተካተቱበት ስለሆነ ነው፣ በጽሕፈት መደብ ላይ ላልሆኑ ሰራተኞች የቤት አበል ጥቅማጥቅም አልተወሰነም፣ ጥቅማጥቅም ሳይወሰን ክፍያ እንዲፈጸም ዳኝነት ሊጠየቅበት አይችልም፣ በተመሳሳይ የሥራ መደብ ላይ ለሚሰራ ሠራተኞች የተለያየ ጥቅማጥቅም እንዲያገኙ ያልተወሰነ በመሆኑ የእኩልነት መብትን አልተጣሰም፣ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል፡፡መልካም ንባብ… Previous Article ተወልደ ግደይ የኤሌክትሪክ ኬብል እና ዋየር ፋብሪካ እናየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰ/መ/ቁጥር 262505 Next Article እነ ወ/ሮ ጌጤ ሙለታ(3ሰዎች) እና ወ/ሮ ብርሃኔ ካባ የሰ/መ/ቁ 249367 Print 5262 Documents to download 263727(.pdf, 845.46 KB) - 611 download(s)
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ... Tuesday, June 30, 2026 181 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር የተቀናጀ አሰራርን በመፍጠር የዳኝነት ስርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል። Read more
ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል... ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል... Monday, June 29, 2026 196 በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለነጻ የህግ ድጋፍ የሚሰጡ የበጎ ፈቃድ ጠበቆች፣ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እና ነፃ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት አስተባባሪዎች የልምድ ልውውጥና ተግባር ተኮር የዉይይት ተካሂዷል። Read more
በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ... በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ... Monday, June 8, 2026 315 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንትነትና ምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ተገኝተው አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይትና ምልከታ አድርገዋል። Read more
ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ... ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ... Thursday, May 28, 2026 345 በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት የተሰራ ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል (One way mirror) በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት በይፋ ስራ ጀምሯል። Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more