Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

ቻይና ሬል ወይስ ሰቨንዝ ግሩፕ ኦሞ ወንዝ ታርጫ መንገድ ስራ ድርጅት እና አቶ ደረሰ ደሳለኝ -የሰ/ መ/ ቁ 254490

  • ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት የአሁን አመልካች ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 18418 ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም በቀን 05/12/2015 አ.ም ይግባኙ አያስቀርብም በማለት ሰርዞታል፡፡ የአሁን አመልካች በነዚህ ውሳኔዎች ላይ ቅር በመሰኘት ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት በቀን 23/02/2016 አ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ ይዘቱም ተጠሪ በክሳቸው እንዲወሰንላቸው የጠየቁት የዳኝነት መጠን ብር 800,800 (ስምንት መቶ ሺህ ስምንት መቶ ብር) ካሣ ሆኖ እያለ ህጉን ባልተከተለ መንገድ፣ ገለልተኛ ባልሆኑ ሰዎችና ቦታው ላይ እንዳልገኝ ተደርጎ ከቅን ልቦና ውጪ  ከሳሽ ከጠየቀው ዳኝነት በላይ የተሰራዉ የባለሞያ ማጣሪያ አመልካችን እጅግ የሚጎዳ በመሆኑና የሞያው ባለቤት በሆነው በከርሰ ምድር ባለሞያ እንዲጣራ ተደርጎ የተጎዳ ንብረት ካለ በግራ ቀኙ ገማች ኮሚቴ አባላት ተመርጠው እንዲገምቱ ተደርጎ ውሳኔ እንዲሰጠኝ በስር ፍርድ ቤት ጠይቄ እያለ ይህ ሳይደረግ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ተሸሮ ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዲወሰንልኝ በማለት የሰበር አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡ መልካም ንባብ…
Previous Article ዲቢኤል ኢንዳስትሪስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና እነ አቶ ኣረጋዊ ስዩም(5ሰዎች) የሰ.መ.ቁ 255892
Next Article የአቶ ጂወይድ ሰይድ ሳሊም እና አቶ አብዱልዋሲ አህመድ ኢብራሂም(2ሰዎች) ሰ/መ/ቁ. 253517
Print
4390

Documents to download

  • 254490(.pdf, 838.66 KB) - 543 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

‎በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአርባ ምንጭ ማዕከል...

23

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአርባ ምንጭ ማዕከል የተዘረጉትን የኢ-ፋይሊንግ፣ የትራንስክሪፕሽን እና የርቀት ችሎት አገልግሎቶችን በአካል ተገኝተው አስመርቀዋል።

የፍርድ ቤቶች አመራሮችና ዳኞች በአርባምንጭ ከተማ የችግኝ...

0

ነሐሴ 03/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተመራ የፍርድ ቤቶች ከፍተኛ አመራሮችና ዳኞች ልዑክ በአርባምንጭ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ ተካሄደ

26

ፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና የጉባኤው ሰብሳቢ ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በመክፈቻ ንግግራቸው፤ በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሠረት የተቋቋመው የፌደራል ጉባኤ የዳኝነት ነፃነትና ገለልተኝነትን የመጠበቅ፣ የአሰራር መመሪያዎችን የማውጣትና የማሻሻል እንዲሁም አገራዊ የዳኝነት ሂደቱን የማጠናከር ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለበት ገልጸዋል።

1345678910Last