Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

ቻይና ኮሙኒኬሽን ኩባንያ ግንባታ ወንጪ ደንዲ ኢኮቱሪዝም ፕሮጀክት እና ማንዴሳ ጪብሳ የሠ/መ/ቁጥር 256412

ጉዳዩ የጉዳት ካሳ ክፍያን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ደግሞ በተከሳሽነት ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ፡- አመልካች ከደንዲ ሀይቅ እስከ ወንጪ ሀይቅ ያለው መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ኮንትራክተር በመሆን በሚሰራበት ወቅት በደንዲ ወረዳ ገ/ጥራንጉ ሹቤሶሌ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከሚገኘው ስፋቱ አራት ሄክታር በሆነው የእርሻ ይዞታዬ ላይ መንገድ ለመገንባት የቆፈረውን አፈር ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም በተሸከርካሪዎች ጭኖ በመድፋት በመሬቱን ገደላማ በማድረግ ከጥቅም ውጪ በመሆኑ በመሬቱ ላይ ተዘርቶ የነበሩትን የሰነፍ ቆሎ፤ገብስ እና ሚስር ቡቃያዎችን፤ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ በቁጥር 5,900.00(አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ባህር ዛፍ፤10 እግር ጥድ፤እንዲሁም 900 እግር ቀርከሃ ስላወደመብኝ የእጽዋቶቹ እና የሰብል  ግምቱ ለወደፊት ያገኙ የነበረውን የ15 አመት ጥቅም በድምሩ ብር 9,823,000 (ዘጠኝ ሚሊየን ስምንት መቶ ሃያ ሶስት ሺ) የጉዳት ካሳ ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዲከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ከሰዋል፡፡መልካም ንባብ…

Previous Article እነ አቶ አመድ ሙሜ(2ሰዎች)የእና ወ/ሮ አሚናት ኡስማንሰ/መ/ቁጥር 254020
Next Article እነ አቶ ዮሐንስ ገ/ሚካኤል(5ሰዎች) እና ወ/ሮ ሃና ደርሶልኝ(2ሰዎች) የሰበር መዝገብ ቁጥር - 256463
Print
4482

Documents to download

  • 256412(.pdf, 876.52 KB) - 528 download(s)

«June 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
25262728293031
1234567
891011121314
15161718192021
22232425262728
293012345

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ...

5

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንትነትና ምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ተገኝተው አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይትና ምልከታ አድርገዋል።

ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ...

38

‎በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት የተሰራ ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል (One way mirror) በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት በይፋ ስራ ጀምሯል።

ለሶሻል ወርክ ባለሞያዎች በተዘጋጀ የስልጠና ማንዋል ረቂቅ...

61

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት በፍትህ ስርዓት ውስጥ የሚያገለግሉ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሞያዎችን ሚና ለማጎልበት የሚያግዝ የስልጠና ማንዋል የመጨረሻ ረቂቅ ሰነድ ላይ የውይይት እና የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሂዷል፡፡ 

‎የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን...

74

በኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ እና የጄሲኢ (JCE) ሰብሳቢ በሆኑት በክብርት ዳኛ ሱዛን ኞኪ ንዱንጉ የተመራው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ላለፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር አጠናቋል።

1345678910Last