Anonym / Saturday, October 31, 2020 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation አቶ ረዲ አህመድ እና ወ-ሮ መኪያ ሀሰን የሰ-መ-ቁ 175719 ይህ የባልና ሚስት የንብረት ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.223910 በ10/8/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ። የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የነበረዉ ጋብቻ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍ/ቤት በሰጠዉ ዉሳኔ ጋብቻችን በፍቺ እንዲፈርስ ወስኗል። ስለሆነም አመልካች እና ተጠሪ በጋራ የፈራነዉ በሱሉልታ ከተማ ልዩ ስሙ ድሬ ጀርባ የሚገኘዉ የቤት ቁጥር 632 SUL 2.1 የሆነዉ በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት እንዲንካፈል እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል። የአሁን ተጠሪ በዚህ ክስ ላይ ባቀረቡት መልስ ይህን ቤት ተጠሪ ከአመልካች ጋር የነበረን ጋብቻ ከተቋረጠ በኋላ ተጠሪ ከግለሰብ ገንዘብ ተበድሬ የተሰራ ስለሆነ የጋራ ንብረት ሳይሆን የግል ንብረቴ በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል።……… Previous Article ዳግም አከበረኝ ከ ፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤሕግ Next Article እነ ወ-ሮ ጀማነሽ ቀነኒ፣አቶ አሰፋ ሸቡ እና ወ-ሮ ብርቱካን ሸቡ የሰ-መ-ቁጥር 177205 Print 17974 Documents to download አቶ ረዲ አህመድ እና ወ-ሮ መኪያ ሀሰን የሰ-መ-ቁ 175719(.pdf, 513.35 KB) - 1417 download(s)
"የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ ፕሮጀክት የፍርድ ቤቶችን... "የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ ፕሮጀክት የፍርድ ቤቶችን... Friday, July 17, 2026 0 የዳኝነት ስርዓቱን ዲጂታላይዝ በማድረግ ቀልጣፋና ተደራሽ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ይቻል ዘንድ ላለፋት ዓመታት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ በፌደራል ፍርድ ቤቶች ላይ ሲተገብር የቆየው የቴክኖሎጂ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ያተኮረው የዋይድ ኤርያ ኔትወርክ ፕሮጀክት (Wide Area Network Project) የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ተካሂዷል። Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ... Tuesday, June 30, 2026 289 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር የተቀናጀ አሰራርን በመፍጠር የዳኝነት ስርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል። Read more
ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል... ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል... Monday, June 29, 2026 283 በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለነጻ የህግ ድጋፍ የሚሰጡ የበጎ ፈቃድ ጠበቆች፣ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እና ነፃ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት አስተባባሪዎች የልምድ ልውውጥና ተግባር ተኮር የዉይይት ተካሂዷል። Read more
በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ... በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ... Monday, June 8, 2026 408 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንትነትና ምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ተገኝተው አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይትና ምልከታ አድርገዋል። Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more