Anonym
/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

አቶ ቀኖ ኩታሳ እና ወ-ሮ መሳይ ገመቹ የሰ-መ-ቁ 180936

ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 303340 በ11/10/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት በ11/11/11ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡የጉዳዩ አመጣጥ የአሁን ተጠሪ በስር በጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የኖኖ ቤንጃ ወረዳ ፍ/ቤት በአሁን አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በክሱ 1ኛ እና 2ኛ ተራ ቁጥር ላይ የተጠቀሰው ስፋቱ እና አዋሳኙ የተጠቀሰው አንድ ባር ሳር ቤት ግምቱ ብር 4000(አራት ሺህ ብር) የሚያወጣ አለን፤ በክሱ ከተራ ቁጥር 3  እስከ 47 የተጠቀሱትን ንብረቶች አመልካች ድርሻዬን እንዲያካፍለኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው አመልካች ባቀረቡት መልስ ከተጠሪ ጋር የኖርነው አስር ወር ብቻ ነው፤ ክስ የቀረበባቸውን ንብረቶች ከቀድሞ ሚስቴ ወ/ሮ ያደሺ ያንካ ጋር ከ1990ዓ.ም ጀምረን ያፈራናቸው ንብረቶች ተጠሪን አይመለከትም፤ ተጠሪ ያላት ንብረት የቤት ውስጥ እቃ ብቻ ሲሆን እነሱም በተራ ቁጥር 12፤13፤14፤15፤19፤20፤23፤24፤26፤27 ሲሆኑ ያልተመዘገቡ ንብረቶች ደግሞ በተራ ቁጥር 3፤4፤5፤6፤16፤18፤21፤22፤25፤28፤29፤30፤31፤35፤36፤46 ሲሆኑ በተራ ቁጥር 46 ላይ የተጠቀሰው ኑግ የለም፤ በተራ ቁጥር 6 ላይ የተጠቀሰው በሬ የቀድሞ ሚስቴ ንብረት ነው፤ በተራ ቁጥር 45 ላይ  የተጠቀሰው ንብረት ተጠሪን ሳላገባት በፊት በ2007ዓ.ም ውስጥ ከቀድሞ ሚስቴ ጋር የገዛነው ነው፤ በተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ የተጠቀሰውን ንብረት አመልካችን ሳላገባት በፊት በ2007ዓ.ም ከቀድሞ ሚስቴ ጋር አፍርተን የባለቤትነት ማስረጃ ስላለን ተጠሪን አይመለከትም፤ በተራ ቁጥር 47 ላይ ተጠሪ የገለጸችውን ቤት በ2007ዓ.ም ከቀድሞ ሚስቴ ጋር ያፈራነው ስለሆነ ተጠሪን አይመለከትም፤ በ27/1/10ዓ.ም የተፈጸመው ውል ደግሞ ተጠሪ የገጠሩ ኑሮ አቅቶኛል ወደ ከተማ አስገባኝ ብላ በሽማግሌ ስለጠየቀችኝ ያደረኩት ውል እንጂ የሰጠኋት ስጦታ የለም፤ ስጦታ አልተሰጠም እንጂ ተሰጥቷል ቢባል እንኳን በመካከላችን የነበረውን አለመግባባት ለመፍታት የተፈጸመ ውል ስለሆነ ውሉ እንዲፈርስልኝ ፤ በ29/8/09ዓ.ም የተፈጸመውን ውል ደግሞ የቀድሞ ሚስቴን ሳላማክራት የፈጸምኩት ውል ስለሆነ  ከቤተሰብ ህጉ የሚቃረን ውል ስለሆነ ውድቅ እንዲደረግልኝ በማለት የተከራከሩ ሲሆን፤  በስር ጣልቃ ገብ የሆኑት ወ/ሮ ያደሺ አንካ (አሁን በሰበር አቤቱታው ላይ የሌሉ) በጣልቃገብነት ገብተው እንዲከራከሩ ተፈቅዶላቸው ባቀረቡት አቤቱታ ከአመልካች ጋር በ1990ዓ.ም ጋብቻ መስርተን አንድ ልጅ እና ንብረት አፍርተን እያለ አመልካች እና ተጠሪ ጋብቻ ፈጽመው ጋብቻቸውን አፍርሰው ወደ ንብረት ክርክር ሲሸጋገሩ ተጠሪ ከአመልካች ጋር ለአስር ወራት ብቻ የኖረች ሲሆን በተራ ቁጥር 1፤2፤6፤7፤8፤9፤10፤11፤31፤32፤33፤34፤37፤38፤39፤40፤41፤42፤43፤44፤45፤47 ላይ ተጠሪ የጠቀሰችው ንብረት እኔ ያፈራሁት ንብረት ስለሆነ ከክርክሩ ይውጣልኝ፤ በ29/8/10ዓ.ም የተደረገውን  የስጦታ ውል በተመለከተ አመልካች ከጣልቃገብ ፍላጎት ውጪ የጋራ ንብረታችን የሆነውን ለ3ኛ ወገን ለማስተላለፍ መብት የሌለው በመሆኑ ውሉ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡..........

Previous Article አቶ ጉዕሽ ሃይሉ ደሞዝ እና ወ-ሮ ፅጌ ገ-ሂወት የሰ-መ-ቁ 180326
Next Article እነ ወ-ሮ የሺወርቅ ፈንታዉ እና ወ-ሮ ፀሀይነሽ ፈንታዉ የሠ-መ-ቁጥር 190450
Print
19512

Documents to download

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

"የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ ፕሮጀክት የፍርድ ቤቶችን...

0

‎የዳኝነት ስርዓቱን ዲጂታላይዝ በማድረግ ቀልጣፋና ተደራሽ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ይቻል ዘንድ ላለፋት ዓመታት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ በፌደራል ፍርድ ቤቶች ላይ ሲተገብር የቆየው የቴክኖሎጂ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ያተኮረው የዋይድ ኤርያ ኔትወርክ ፕሮጀክት (Wide Area Network Project) የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ...

289

‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር የተቀናጀ አሰራርን በመፍጠር የዳኝነት ስርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል።

ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል...

283

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለነጻ የህግ ድጋፍ የሚሰጡ የበጎ ፈቃድ ጠበቆች፣ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እና ነፃ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት አስተባባሪዎች የልምድ ልውውጥና ተግባር ተኮር የዉይይት ተካሂዷል።

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ...

408

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንትነትና ምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ተገኝተው አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይትና ምልከታ አድርገዋል።

1345678910Last