Anonym / Thursday, October 8, 2020 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation አቶ ደጋረገ ሙሉ እና ወ-ሮ ውብናት ላቀ የሰ-መ-ቁ 181649 ይህ የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ክርክር የተጀመረዉ በአማራ ክልል በሜጫ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ተጠሪ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር አመልካች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.74190 ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ። የአሁን ተጠሪ በሥር በወረዳዉ ፍ/ቤት ባቀረበችዉ ክስ ከአሁን አመልካች ጋር ያለን ጋብቻ እንዲፈርስ፣ በጋራ የፈረናቸዉ ንብረቶች እንዲንካፈል በማለት ዘርዝራ በማቅረብ እንዲወሰንላት ዳኝነት ጠይቃለች።የአሁን አመልካች በዚህ ክስ ባቀረቡት መልስ ተጠሪዋ ባቀረበችዉ የንብረት ጥያቄ ላይ ተገቢ ነዉ ያለዉን ክርክር ያቀረበ ሲሆን፤ በራሱ በኩል ባቀረበዉ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ከተጠሪ ጋር ሊንካፈል ይገባል የሚላቸዉን ንብረቶች በመዘርዘር በመጠየቅ፤ የሰራተኛ እዳ አራት ኩንታል በቆሎ አንድ ኩንታል ዳጉሳ፣ አንድ ኩንታል ጓያ አለብን ልንከፍል ይገባል በማለት ጠይቋል። የአሁን ተጠሪ በዚህ በተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ላይ መልስ ያቀረበች ሲሆን፣ የሰራተኛ የጋራ እዳ አለብን በማለት የቀረበዉም ሐሰት ነዉ፣ ይህ ተቀጠረ የተባለዉ ልጅ የአሁን አመልካች የግል ልጅ ነዉ የእኔም ሶስት ልጆች የግል ነበረኝ የግል ከብቶች ነበራቸዉ እነዚህ ልጆች አብራዉ ከእኛ ጋር ያደጉ ሲሆን ለሰሩበት ልንከፍላቸዉ አልተስማማንም አልቀጠርናቸዉም፣የአሁን አመልካች ልጅ እንደልጅ ከቤት ነበረ እንጂ የተቀጠረ አይደለም።ከዚህ በኋላ የወረዳዉ ፍ/ቤት የሰዉ ምስክሮች በመስማት በሰጠዉ ዉሳኔ የአሁን አመልካች በተከሳሽ ከሳሽነት የጋራ ዕዳ በማለት ያቀረበዉ የሰራተኛ እዳ 6 [ስድስት] ማዳበሪያ እህል በጋራ ሊከፍሉ ይገባል፤ የባልና ሚስት ንብረቶች ላይ ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ ሰጥቷል። የአሁን ተጠሪ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለባህር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበችዉ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ የባልና ሚሰት ንብረት በተመለከተ በተወሰኑ ንብረቶች ላይ የሥር ፍ/ቤት ጉዳዩን ድጋሚ አጣርቶ እንዲወስን የመለሰ ሲሆን፣ የሰራተኛ ዕዳ የተባለዉን የሥር ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።............ Previous Article እነ አቶ ጁሀር ያህያ እና ወ/ሮ መሬም አህመድ የሰ.መ.ቁ 179607 Next Article እነ ወ/ሮ አያልነሽ ፈንቴ እና ወ/ሮ ብርሃኔ ተካ የሰ-መ-ቁ182110 Print 17383 Documents to download አቶ ደጋረገ ሙሉ እና ወ-ሮ ውብናት ላቀ የሰ-መ-ቁ 181649(.pdf, 535.31 KB) - 1675 download(s)
"የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ ፕሮጀክት የፍርድ ቤቶችን... "የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ ፕሮጀክት የፍርድ ቤቶችን... Friday, July 17, 2026 0 የዳኝነት ስርዓቱን ዲጂታላይዝ በማድረግ ቀልጣፋና ተደራሽ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ይቻል ዘንድ ላለፋት ዓመታት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ በፌደራል ፍርድ ቤቶች ላይ ሲተገብር የቆየው የቴክኖሎጂ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ያተኮረው የዋይድ ኤርያ ኔትወርክ ፕሮጀክት (Wide Area Network Project) የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ተካሂዷል። Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ... Tuesday, June 30, 2026 289 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር የተቀናጀ አሰራርን በመፍጠር የዳኝነት ስርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል። Read more
ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል... ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል... Monday, June 29, 2026 283 በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለነጻ የህግ ድጋፍ የሚሰጡ የበጎ ፈቃድ ጠበቆች፣ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እና ነፃ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት አስተባባሪዎች የልምድ ልውውጥና ተግባር ተኮር የዉይይት ተካሂዷል። Read more
በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ... በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ... Monday, June 8, 2026 408 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንትነትና ምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ተገኝተው አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይትና ምልከታ አድርገዋል። Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more