Anonym / Wednesday, October 7, 2020 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation አቶ ጉዕሽ ሃይሉ ደሞዝ እና ወ-ሮ ፅጌ ገ-ሂወት የሰ-መ-ቁ 180326 ይህ የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ክርክር የተጀመረዉ በመቐለ ከተማ በ02 ቀበሌ ማህበራዊ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ተከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.115041 በ12/09/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።የአሁን ተጠሪ በቀበሌ ማህበራዊ ፍ/ቤት ባቀረበችዉ ክስ ከአመልካች ጋር ያለን ጋብቻ እንዲፈርስ፣ ትዳር ሲንመሰርት በባንክ ወደ አመልካች የሂሳብ ቁጥር ገቢ ያደረኩኝ ገንዘብ እንዲከፍለኝ፣ ለጥሎሽ ከሚገዛ ወርቅ ቀንሶ የወሰደዉ ብር 8190 እንዲከፍለኝ በማለት ዳኝነት ጠይቃለች፣ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ ዘርዝራለች።የአሁን አመልካች በዚህ ክስ ላይ ባቀረበዉ መልስ ተጠሪ ይህን ገንዘብ ለመጠየቅ መብት የለትም፣ ትዳር ሲንፈጽም ባደረግነዉ ዉል እኔም ገንዘብ በመግጠም በመቐለ ከተማ 16 ቀበሌ ዉስጥ የአልኮል ማከፋፈያ ከፍተን ኪራይ ብር 6000 ስንከፍል ቆይተን ስምምነት ስናጣ አሁን ለዋርድያ ብር 500 እየከፈልን እየተጠበቀ ስለሆነ ለትዳር መግጠሚያ ያቀረበችዉን ገንዘብ መጠየቋ ተገቢ አይደለም፣ በትዳር ዉስጥ ትርፍም ኪሳራም የጋራ ነዉ፣ ይህ ንብረት ተቆጥሮ በገንዘብም ሆነ በዓይነት እንዲንካፈል በማለት ተከራክሯል፣ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ ጠቅሷል።………… Previous Article አቶ ወንድማገኝ መንግስቱ ማሞ እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ-መ-ቁ 191629 Next Article አቶ ቀኖ ኩታሳ እና ወ-ሮ መሳይ ገመቹ የሰ-መ-ቁ 180936 Print 17637 Documents to download አቶ ጉዕሽ ሃይሉ ደሞዝ እና ወ-ሮ ፅጌ ገ-ሂወት የሰ-መ-ቁ 180326(.pdf, 496.24 KB) - 1266 download(s)
"የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ ፕሮጀክት የፍርድ ቤቶችን... "የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ ፕሮጀክት የፍርድ ቤቶችን... Friday, July 17, 2026 0 የዳኝነት ስርዓቱን ዲጂታላይዝ በማድረግ ቀልጣፋና ተደራሽ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ይቻል ዘንድ ላለፋት ዓመታት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ በፌደራል ፍርድ ቤቶች ላይ ሲተገብር የቆየው የቴክኖሎጂ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ያተኮረው የዋይድ ኤርያ ኔትወርክ ፕሮጀክት (Wide Area Network Project) የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ተካሂዷል። Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ... Tuesday, June 30, 2026 289 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር የተቀናጀ አሰራርን በመፍጠር የዳኝነት ስርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል። Read more
ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል... ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል... Monday, June 29, 2026 283 በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለነጻ የህግ ድጋፍ የሚሰጡ የበጎ ፈቃድ ጠበቆች፣ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እና ነፃ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት አስተባባሪዎች የልምድ ልውውጥና ተግባር ተኮር የዉይይት ተካሂዷል። Read more
በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ... በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ... Monday, June 8, 2026 408 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንትነትና ምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ተገኝተው አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይትና ምልከታ አድርገዋል። Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more