Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ እና የማነ ግርማይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የሰ.መ.ቁ 246233

የጉዳዩ አመጣጥ ተጠሪ ለግልግል ዳኝነት ጉባኤ በ1ኛ አመልካች ላይ ባቀረበው ክስ በተጠሪ እና በ2ኛ አመልካች(ስር ጣልቃገብ ) መካከል ከወራቤ እስከ በጆበር ያለውን 38.5ኪ.ሜ የመንገድ ስራ ፐሮጀክት ለማከናወን እ.ኤ.አ ሜይ 20 2016 ውል የተፈረመ ሲሆን የውሉም አይነት ስራ ተቋራጩ(2ኛ አመልካች) የዲዛይንና የግንባታ ስራውን በሙሉ በኃላፊነት የሚያከናውንበት ነው፡፡ በውሉ መሰረት ስራ ተቋራጩ የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና የማቅረብ ግዴታ ስላለበት ይህን ተከትሎ ተቋራጩ የውሉን 10% ይኅውም ለብር 45‚844‚565 እ.ኤ.አ ከሜይ 13 2016 ጀምሮ ለአራት አመት ጸንቶ የሚቆይ የቦንድ ፖሊሲ ቁጥሩ በተገለጸ 1ኛ አመልካች የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ሰጥቷል፡፡ በውሉ መሰረት እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 26 2017 የተጀመረው የግንባታ ስራ በ1095 ቀናት ተጠናቆ ለግዜያዊ ርክክብ ብቁ መደረግ ሲገባው እና ከአመት በኋላ ጃንዋሪ 2018 አፈጻጸሙ 30.38% መሆን ሲገባው የስራ ተቋራጩ አፈጻጸም የውሉ 8% ላይ ነበር፡፡ በዛን ግዜም ከውሉ መፈጸሚያ ግዜ 33.8% ባክኖ ነበር፡፡ ተጠሪ ለስራ ተቋራጩ በቂ የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ቢሰጠውም፤ ሶስት የክፍያ ሰርተፍኬቶችም ጸድቀው ገንዘብ ቢከፈለውም፤ የውል ግዴታውን እንዲወጣ ተጠሪና የፕሮጀክቱ አማካሪ ድርጅት ተደጋጋሚ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ ቢሰጡትም ይህን ባለመቀበል የግንባታ ቦታውን ጥሎ በመሄድ አይነተኛና መሰረታዊ የውል ጥሰት በመፈጸሙ ተጠሪ በውሉ መሰረት እ.ኤ.አ በ1/3/18 በተጻፈ ደብዳቤ የ2ኛ አመልካችን(ስራ ተቋራጭ) የስራ ውል አቋርጧል፡፡

የስራ ውል መቋረጡን ተከትሎ 1ኛ አመልካች የዋስትናውን ገንዘብ ገቢ እንዲያደርግ ተጠሪ ቢጠይቀውም የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ የዋስትና ግዴታውን ለመወጣት ፈቃደኛ ባለመሆኑ 1ኛ አመልካች በመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና መሰረት ብር 45‚844‚565 ክፍያ እንዲፈጽም ከተጠየቀበት ግዜ ከ27/6/2010ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር እንዲከፍል እንዲወሰንበት በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ…

Previous Article አቶ ዮሀንስ ካሳዬ እና የፍትህ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 273594
Next Article አቶ ጉዕሽ ካሳ ደሞዝ እና እነ አቶ አማኑኤል ወልደሊባኖስ ተስፋዬ የሠ/መ/ቁጥር 243564
Print
4006

Documents to download

  • 246233(.pdf, 1.05 MB) - 493 download(s)

«April 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
303112345
6789101112
13141516171819
20212223242526
27282930123
45678910

በኢትዮጵያ የአዘርባጃን አምባሳደር ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ...

19

በኢትዮጵያ የአዘርባጃን አምባሳደር እና የአፍሪካ አንድነት ቋሚ ተወካይ የተከበሩ ሩስላን ናሲቦቭ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተገኝተው በጋራ መስራት በሚቻል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

ሀገር አቀፍ የዳኝነት እና የፍትህ አካላት የጋራ መድረክ...

36

ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው አመታዊ ሀገር አቀፍ የዳኝነት እና የፍትህ አካላት የጋራ የምክክር መድረክ (ጆይንድ አፕ ጀስቲስ ፎረም) የፌዴራልና የክልል የዳኝነትና የፍትህ አካላት የጋራ መድረክ የመግባቢያ ሰነድ የፊርማ ስነ ስርዓት በማከናወን ተጠናቋል።

የዳኝነትና የፍትህ አካላት በጋራ የሚመክሩበት፣...

20

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በመክፈቻ ንግግራቸው፤ የሕግ የበላይነት የተረጋገጠባት እና ፍትሕ የሰፈነባት ሀገር ከመገንባት አንጻር በጋራ ስራዎች ላይ ለመምከርና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ የመድረኩ ሚና ከፍተኛ እንደሆነ በማንሳት፤ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በጋራ በመፍታት ተቋማዊም ሆነ የወል ግቦችን ማሳካት እንደሚቻል ገልጸዋል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሰሚ ችሎት የወንጀል...

78

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአውሮፓ ህብረት ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ሁለት የስልጠና ማኑዋሎች ማለትም ተከታታይ የወንጀል ችሎት አመራር ሥልጠና ማንዋል( Training Manual on continuous criminal trials )፣ ድንበር ተሻጋሪ እና ከባድ ወንጀሎች ሥልጠና ሞጁል(Training Module on Trans-Boundary and grave crimes) እንዲሁም "በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሰሚ ችሎት የወንጀል ህግ ትርጉም ውሳኔዎች ስብስብ በጉዳዮች የተደራጁ ልዩ ዕትም" መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የማስተዋወቅ ፕሮግራም አካሂዷል ፡፡

1345678910Last