Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

ኤልያስ ዳሪ እና እነ ወ/ሮ ሰናይት አብርሃ (6) ሰዎች የሰ/መ/ቁ. 253783

ጉዳዩ የሽያጭ ውል ይፈጸምልኝ ክስ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ባቀረቡት ክስ 1ኛ ተጠሪ ሚስትና የወራሽ ወኪል ሆነው ከ3ኛ-6ኛ ያሉት ተጠሪዎች ጋር በጋራ በመሆን በድሮ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 3 የይዞታ መለያ ቁጥር AA000040301555 የሆነ በ348 ካ.ሜ ላይ ያለውን ቤትና ይዞታቸውን ጥቅምት 24 ቀን 2011 ዓ/ም በተደረገ የሽያጭ ውል በብር 2,900,000 ሸጠውልኝ በዚህ ውል መሰረት ለሻጮች በየድርሻቸው መጠን እንዲካፈሉት በቼክ ለሁሉም ግማሽ ክፍያው የተከፈላቸው ሲሆን በሽያጭ ውሉ መሰረት ውሉ በተደረገ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሽያጭ ውሉ ፎርማሊቲውን አሟልተው ውሉን በሰነዶች ምዝገባ ጽ/ቤት ቀርበው ሲያስመዘግቡና ቤትና ይዞታውን ከቤቱ አስረጂ ሰነድ ጋር ሲያስረክቡኝ ቀሪውን ገንዘብ ልከፍላቸው የተስማማን ሲሆን ተጠሪዎች በውሉ መሰረት እንዲፈጽሙ በተደጋጋሚ ብጠይቅም 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ፍቃደኛ ሲሆኑ ከ3ኛ እስከ 6ኛ ያሉ ተጠሪዎች ግን ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ተጠሪዎች በውሉ የተጠቀሰውን ቤት ከነይዞታው ቤቱን ከሚመለከቱ ሰነዶች ጭምር እንዲያስረክቡኝ እንዲወሰንልኝ፤ እንዲሁም የቤቱን ስመሀብት ከሻጮች ወደ ገዢ ለማስተላለፍ የሚያስፈልጉ ፎርማሊቲዎችን እንዲያሟሉ ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ….  

Previous Article የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አቶ መጣልኝ መላኩ የሰ.መ.ቁ.252953
Next Article የኢትዮጵያ መድን ድርጅት እና አቶ አበራ ተፈሪ የሰ/መ/ቁጥር 254101
Print
5921

Documents to download

  • 253783(.pdf, 848.53 KB) - 747 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

የፍርድ ቤቶች አመራሮችና ዳኞች በአርባምንጭ ከተማ የችግኝ...

0

ነሐሴ 03/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተመራ የፍርድ ቤቶች ከፍተኛ አመራሮችና ዳኞች ልዑክ በአርባምንጭ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ ተካሄደ

0

ፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና የጉባኤው ሰብሳቢ ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በመክፈቻ ንግግራቸው፤ በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሠረት የተቋቋመው የፌደራል ጉባኤ የዳኝነት ነፃነትና ገለልተኝነትን የመጠበቅ፣ የአሰራር መመሪያዎችን የማውጣትና የማሻሻል እንዲሁም አገራዊ የዳኝነት ሂደቱን የማጠናከር ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለበት ገልጸዋል።

12345678910Last