Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

እስጢፋኖስ /ዩቡና/ ዲራጎ እና የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 251519

አመልካች በቀን 26/11/2015ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት መጽናቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት ሲሆን ይዘቱ በአጭሩ - አመልካች ድርጊቱ በተፈጸመበት ቦታ ነበርኩኝ እንጂ ድርጊቱን አልፈጸምኩም፤ የተጠሪ ምስክሮች ድርጊቱን ስለመፈጸሜ አላስረዱብኝም፤ ባቀረብኩት ምስክር ወንጀሉን ያልፈጸምኩ መሆኑን አስረድቻለሁ፤የተጠሪ ምስክሮች እርሱን ይመስላል ከማለት ውጪ ድርጊቱን ስለመፈጸሜ አላስረዱም፡፡የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ በማጽናት የወሰነዉ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 23/2 ስር በተደነገገዉ መሠረት የግድያ ወንጀል መፈጸሜ ሳይረጋገጥ በመሆኑ ዉሳኔዉ ከዚህ ድንጋጌ አፈጻጸም ጋር በተያያዘ በሰ/መ/ቁጥር 22069 ስር የተሰጠዉን አስገዳጅ የሕግ ትርጉም የሚቃረን ነዉ፡፡ስለሆነም ተጠሪ ያቀረባቸው ምስክሮች አመልካች ድርጊቱን ስለመፈጸሜ ከጥርጣሬ በላይ ያላስረዱ ስለሆነ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠው የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ ተሽሮ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የሰጠው ውሳኔ እንዲጸናል፡፡የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠዉ የጥፋተኝነት ውሳኔው የሚያጸና ከሆነም አንቀጹ ወደ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 540 እንዲቀየርልኝ እና የ3ኛ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ስለሆንኩ ቅጣቱ በወ/ህ/አንቀጽ 192 መሰረት እንዲገደብልኝ በማለት አመልክቷል፡፡መልካም ንባብ….

Previous Article የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቀበሌ 11/12/08 ሸማቾች ኃ/የተ/ሕ/ሥ/ማ እና አቶ እንኮሳ አመንቴ ሱፋ(9ሰዎች)የሰ.መ.ቁ 249104
Next Article ጠቋሬ ፈለቀ እና አባ ምትኩ ዘዉዴ የሰ.መ.ቁ.253916
Print
5643

Documents to download

  • 251519(.pdf, 865.01 KB) - 604 download(s)

«September 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
31123456
78910111213
14151617181920
21222324252627
2829301234
567891011

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ...

47

ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሠራተኞችን መብት፣ ግዴታና የዲሲፕሊን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናን ጨምሮ ልዩ ልዩ መርሃ-ግብሮችን በማካሄድ ተጠናቋል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመታዊ የሰራተኞች መድረክ...

41

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሰራተኞች መድረክ በዛሬው ዕለት መካሄድ የጀመረ ሲሆን የፍርድ ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሂዷል።

1345678910Last