Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

እነ አቶ አመድ ሙሜ(2ሰዎች)የእና ወ/ሮ አሚናት ኡስማንሰ/መ/ቁጥር 254020

ጉዳዩ የገጠር መሬት ውርስን የሚመለከት ሲሆን ጉዳዩ በጀመረበት የሀረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን አመልካቾች ተከሳሽ፤ የአሁን ተጠሪ አውራሽ የሆኑት ወ/ሮ ከዲጃ ዑመር ከሳሽ ነበሩ፡፡ የአሁን ተጠሪ አውራሽ ያቀረቡት ክስም፡- ሟች አባታቸው በ1966 ዓ.ም በሞት የተለዩ መሆኑን፤ሟች አባታቸው እርሳቸውንና ሟች ወንድማቸውን አቶ ዘከሪያ ኡመር የወለዱ መሆኑን፤ሟች ወንድማቸውም የአሁን አመልካቾችን እናት አግብቶ ሲኖር ቆይቶ ልጅ ሳይወልድ እና ሳይናዝ የሞተ መሆኑን፤ ለክርክር መነሻ የሆነው በአራት ቦታ የሚገኘው የገጠር መሬት የሟች አባታቸው እና ክፍፍል ያልተፈጸመበት እንዲሁም ከሟች ወንድማቸው ጋር ሲጠቀሙበት የቆዩ መሆኑን፤ ሟች ወንድማቸው ከሞተ በኋላም የአሁን አመልካቾች እናት እየረዳቻቸው በመሬቱ ስትጠቀም እንደነበር፤ እርሷ ከሞተች በኋላ መሬቱን ተጠሪዎች እንዲለቁ ቢጠየቁ ፈቃደኛ ሊሆኑ አለመቻላቸውን ጠቅሰው መሬቱን ለቀው እንዲያስረክቡኝ እና ከመሬቱ የተገኘውን ጥቅም ጨምረው እንዲከፍሉኝ የሚል ነበር፡፡ ተጠሪዎች ለክሱ ባቀረቡት መልስ ክሱ በይርጋ የተቋረጠ ነው፡፡ ለክርክር መነሻ የሆነውን መሬት እናታችን መብት በመመስረት ንብረትነቱ የመንግስት በሆነ መሬት ላይ ከከሳሽ ወንድም ጋር ባልና ሚስት በመሆን ጋብቻው በሞት ቀሪ እስከሆነበት ጊዜ ድረስ መብት ፈጥረው እየተጠቀሙ የቆዩ በመሆኑ ክሱ ውድቅ እንዲደረግልን በማለት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ….

Previous Article ጠቋሬ ፈለቀ እና አባ ምትኩ ዘዉዴ የሰ.መ.ቁ.253916
Next Article ቻይና ኮሙኒኬሽን ኩባንያ ግንባታ ወንጪ ደንዲ ኢኮቱሪዝም ፕሮጀክት እና ማንዴሳ ጪብሳ የሠ/መ/ቁጥር 256412
Print
4321

Documents to download

  • 254020(.pdf, 832.14 KB) - 538 download(s)

«June 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
25262728293031
1234567
891011121314
15161718192021
22232425262728
293012345

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ...

78

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንትነትና ምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ተገኝተው አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይትና ምልከታ አድርገዋል።

ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ...

97

‎በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት የተሰራ ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል (One way mirror) በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት በይፋ ስራ ጀምሯል።

ለሶሻል ወርክ ባለሞያዎች በተዘጋጀ የስልጠና ማንዋል ረቂቅ...

119

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት በፍትህ ስርዓት ውስጥ የሚያገለግሉ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሞያዎችን ሚና ለማጎልበት የሚያግዝ የስልጠና ማንዋል የመጨረሻ ረቂቅ ሰነድ ላይ የውይይት እና የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሂዷል፡፡ 

‎የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን...

106

በኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ እና የጄሲኢ (JCE) ሰብሳቢ በሆኑት በክብርት ዳኛ ሱዛን ኞኪ ንዱንጉ የተመራው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ላለፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር አጠናቋል።

1345678910Last