Anonym / Friday, February 25, 2022 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation እነ አቶ ካሳሁን ዘላለም እና የሰሜን ሸዋ ዞን የገቢዎች ዓቃቤ ሕግ የሰ.መ.ቁ 208826 ጉዳዩ ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው፡፡ የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካቾች ላይ በስር ፍርድ ቤት ያቀረባቸው ክሶች ሶስት ሲሆኑ ይዘታቸውም፡- 1ኛ ክስ፡- 1ኛ አመልካች የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 120/1 ድንጋጌን በመተላለፍ በደብረብርሃን ከተማ ቀበሌ 06 ገቢዎች ጽ/ቤት በተጨማሪ እሴት ታክስ ግብር ከፋይነት ተመዝግቦ በሬስቶራንት ንግድ ዘርፍ ተሰማርቶ በመስራት ላይ እንዳለ ሕዳር 08 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 7፡15 ሠዓት ሲሆን በሬስቶራንቱ ውስጥ የምግብ እና የመጠጥ አገልግሎት ለመጠቀም የገቡት አቶ ተክልዬ አስራት እና አቶ ብርቅነርህ ደሳለኝ የተባሉት ግለሰቦች ሁለት ጥብስ፤ ሁለት ቢራ እና ሁለት ድራፍት ከተጠቀሙ በኋላ ለጥብሱ ብር 180፤ ለቢራው ብር 50፤ ለድራፍቱ ብር 24፤ በጠቅላላው ብር 254 / ሁለት መቶ ሀምሳ አራት / ከፍለው ሲወጡ ከሽያጭ መመዝገቢያው መሳሪያ የሚወጣውን ደረሰኝ ቆርጦ መስጠት ሲገባው ደረሰኙን ሳይሰጥ ግብይት የፈጸመ እና ወዲያውኑ እጅ ከፍንጅ የተያዘ በመሆኑ በፈጸመው ያለደረሰኝ ግብይት መፈጸም ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡………… Previous Article የቤጊ ከተማ አስተዳደር እና አቶ ደጉማ ባያ የሰ/መ/ቁጥር 205786 Next Article ወ/ሮ ፀሐይነሽ ወርቁ እነ አቶ አርአያ በዛብህ የሰ/መ/ቁ 211693 Print 19254 Documents to download 208826(.pdf, 1.05 MB) - 2951 download(s)
ለህጻናት ተስማሚ የሆነ የፍትህ ስርዓትን ለማስፈን ያለመ... ለህጻናት ተስማሚ የሆነ የፍትህ ስርዓትን ለማስፈን ያለመ... Wednesday, September 9, 2026 34 በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት፤ ለህጻናት ተስማሚ የሆነ የፍትህ ሂደት ትግበራን በተመለከተ ለመርማሪ ፖሊስ አባላት እና ለክቡራን ዳኞች በሁለት ዙር የተከፈለ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ Read more
BRICS Chief Justices' Forum Concludes BRICS Chief Justices' Forum Concludes Sunday, September 6, 2026 154 September 6, 2026 (Federal Supreme Court) The BRICS Chief Justices forum, hosted by the Supreme Court of India from September 4 to September 6, 2026, has concluded. Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ... Monday, August 31, 2026 77 ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሠራተኞችን መብት፣ ግዴታና የዲሲፕሊን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናን ጨምሮ ልዩ ልዩ መርሃ-ግብሮችን በማካሄድ ተጠናቋል። Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመታዊ የሰራተኞች መድረክ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመታዊ የሰራተኞች መድረክ... Monday, August 31, 2026 116 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሰራተኞች መድረክ በዛሬው ዕለት መካሄድ የጀመረ ሲሆን የፍርድ ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሂዷል። Read more