Anonym / Wednesday, October 7, 2020 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation እነ አቶ ጁሀር ያህያ እና ወ/ሮ መሬም አህመድ የሰ.መ.ቁ 179607 ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካቾች የአማራ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ.መ.ቁ 03-76478 በ15/8/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት በ16/12/11ዓ.ም በተጻፈ የተሻሻለ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡የጉዳዩ አመጣጥ የአሁን 1ኛ ተጠሪ በስር የአብክመ ጎንደር ዞን አስተዳደር የጎንደር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በአሁን 2ኛ ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በ1960ዓ.ም ተጋብተን 4 ልጆች ወልደን ንብረት አፍርተን ስንኖር ባለመግባባታችን ጋብቻው ሳይፈርስ ተለያይተን ኖረናል፡፡ ስለሆነም አሁን ጋብቻው ፈርሶ 2ኛ ተጠሪ ሌላም ሚስት ስላለው የዘረዘርኩትን ንብረት ለሶስት እንድንካፈል በማለት ዳኝነት ጠይቀው 2ኛ ተጠሪም ባቀረቡት መልስ 1ኛ ተጠሪ ልጅ ወልዳልኛለች እንጂ ጋብቻ የለንም በማለት ተከራክረው ፍ/ቤቱም ጋብቻ አለ የለም? የሚለውን በምስክር እና በሰነድ በማረጋገጥ ጋብቻ እንዳለ በማረጋገጥ ብይን ሰጥቶ 1ኛ ተጠሪ የዘረዘሩትን ንብረቶች ባልና ሚስት የሆኑት 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች እንዲሁም በስር 1ኛ ጣልቃገቦች የነበሩት የአሁን አመልካቾች እንዲካፈሉ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ጉዳዩ በይግባኝ ወደ ክልሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ሄዶ ፍ/ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ በ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪ መካከል ጋብቻ ያለ መሆኑን አረጋግጦ የአሁን 3ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብተው ባለመከራከራቸው የተነሳ የስር የወረዳ ፍ/ቤቱን ውሳኔ በመሻር የአሁን 3ኛ ተጠሪ ጣልቃገብተው እንዲከራከሩ ውሳኔ በመስጠት ጉዳዩን ለስር የወረዳው ፍ/ቤት በመለሰው መሰረት 3ኛ ተጠሪ በስር የወረዳው ፍ/ቤት 2ኛ ጣልቃገብ ሆነው ባቀረቡት የጽሁፍ ክርክር የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበው በፍሬጉዳዩ ላይ ባቀረቡት መልስ 1ኛ ተጠሪ ዘርዝራ ያቀረበችው ንብረት እንዲፈራ ያደረገችው አስተዋጽኦ የለም፤ በ2ኛ ተጠሪ እና በ3ኛ ተጠሪ ጥረት የተፈሩ ንብረቶች ናቸው፤ በ1ኛ ተጠሪ ክስ በተራ ቁጥር 2 ላይ የተጠቀሰው እና አሁን አመልካቾች በዚህ ፍ/ቤት ላቀረቡት የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው አከራካሪው በመሀል አራዳ የሚገኘው ባለሁለት ፎቅ ቤት ከአሁን አመልካቾች ልጆቻችን(በስር ከ1ኛ ጣልቃገቦች) ጋር በሽርክና ስራ ከመጀመራችን በፊት በንጉሱ ዘመን ከቀበሌ የተቀበልነው እኔ እና 2ኛ ተጠሪ ስንሆን እስከ 1983ዓ.ም በመኖሪያ ቤት የምንጠቀምበት 2ኛ ተጠሪ እና እኔ ባለቤቱ 3ኛ ተጠሪ ስንሆን 2ኛ ተጠሪ በእርጅና ምክንያት ስራ ሲያቆም ለገቢ ምንጭ እንዲሆነን ከጋራ ልጆቻችን ጋር የሽርክና ውል ወስደንበታል፡፡ ፎቁም የተሰራው በልጆቻችን ጥረት በመሆኑ የልጆቻችን የ60% ድርሻ መኖሩን ስለማውቅ በነሱ በኩል የቀረበውን የጣልቃገብነት አቤቱታ አልቃወምም፤ ነገር ግን ፍ/ቤቱ በ2ኛ ተጠሪ እና በአሁን አመልካቾች(በስር 1ኛ ጣልቃገቦች) መካከል የተደረገው የሽርክና ውል ፈራሽ ነው የሚልበት ምክንያት ካለው ክፍፍልን በተመለከተ የቤቱ እና ቦታው ግማሽ ሀብት የ3ኛ ተጠሪ በመሆኑ ግማሽ ባለሀብት ናት ይባልልኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡......... Previous Article እነ ወ-ሮ ሰሚራ ጀማል እና አቶ ናስር ሐጎስ የሠ-መ-ቁጥር 188406 Next Article አቶ ደጋረገ ሙሉ እና ወ-ሮ ውብናት ላቀ የሰ-መ-ቁ 181649 Print 18831 Documents to download እነ አቶ ጁሀር ያህያ እና ወ-ሮ መሬም አህመድ የሰ.መ.ቁ 179607(.pdf, 548.54 KB) - 1463 download(s)
"የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ ፕሮጀክት የፍርድ ቤቶችን... "የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ ፕሮጀክት የፍርድ ቤቶችን... Friday, July 17, 2026 0 የዳኝነት ስርዓቱን ዲጂታላይዝ በማድረግ ቀልጣፋና ተደራሽ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ይቻል ዘንድ ላለፋት ዓመታት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ በፌደራል ፍርድ ቤቶች ላይ ሲተገብር የቆየው የቴክኖሎጂ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ያተኮረው የዋይድ ኤርያ ኔትወርክ ፕሮጀክት (Wide Area Network Project) የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ተካሂዷል። Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ... Tuesday, June 30, 2026 289 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር የተቀናጀ አሰራርን በመፍጠር የዳኝነት ስርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል። Read more
ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል... ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል... Monday, June 29, 2026 283 በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለነጻ የህግ ድጋፍ የሚሰጡ የበጎ ፈቃድ ጠበቆች፣ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እና ነፃ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት አስተባባሪዎች የልምድ ልውውጥና ተግባር ተኮር የዉይይት ተካሂዷል። Read more
በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ... በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ... Monday, June 8, 2026 408 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንትነትና ምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ተገኝተው አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይትና ምልከታ አድርገዋል። Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more