Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

እነ ወ/ሮ ተናኜ ሞላ ብርሐኔ(3ሰዎች) እና አቶ ሳሙኤል ተገኝ ኃይሌ የሰበር መዝገብ ቁጥር - 257774

ጉዳዩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን በስር ፍርድ ቤት አመልካቾች ተጠሪዎች ተጠሪ ደግሞ አመልካች በመሆን ተከራክረዋል፡፡በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካቾች ላይ ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ ወላጅ አባት ሟች አቶ ኃይሌ ተገኝ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ኑዛዜ የፈፀሙ መሆኑን አመልካች የሟች ብቸኛ ልጅ መሆኑን ለተጠሪዎች ኑዛዜ በመፈፀም ከሚደርሰው ድርሻ ከሩብ በላይ ጉዳት እንዲደርስበት ያደረገ በመሆኑ ከኑዛዜው እንድነቀል ተደርጊያለሁ ስለዚህ ሟች ፈፀመውታል የተባለው ኑዛዜ እንዲሻርልኝ የሚል ነው፡፡

ከአመልካቾች በኩል የተሰጠው መልስ በአጭሩ ኑዛዜው በህግ ፊት የፀና ነው ሟች ማንም ሰው ሳያስገድዳቸው በራሳቸው ፍቃድና ፍላጎት በትክክለኛ አእምሮ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ፊት ቀርበው የኑዛዜው ሰነድ ተነቦላቸው በምስክሮች ፊት የቁም ኑዛዜ ያደረጉ ስለሆነ ኑዛዜው ህጋዊ መሆኑን ሟች ጥር 29 ቀን 2012 ዓ.ም ባደረጉት የቁም ኑዛዜ በተራ ቁጥር 2፣ 3 እና 4 የተጠቀሱት የኑዛዜ ተቀባዮች በሟች ስም የሚጠሩ መሆናቸውን ኑዛዜ አድራጊው ልጆች ናቸው ብሎ የተቀበላቸውን ግለሰቦች 3ኛ ወገን ተወላጆች ስላልሆኑ የኑዛዜ ስጦታ ሊበረከትላቸው አይገባም ብሎ መከራከር የሟችን በንብረቱ ላይ የማዘዝ መብትን የሚጥስ በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የኑዛዜ ተቀባዮች ተወላጆች አይደሉም ቢባል እንኳን የኑዛዜ ስጦታ ለተወላጅ ብቻ የሚሰጥ መብት ነው የሚል የህግ ድንጋጌ ያለመኖሩን አመልካች ሟች አባታቸው ባደረጉት ኑዛዜ የኑዛዜ ተቀባይ ነው እንጂ በኑዛዜው ከውርስ አልተነቀለም፡፡ አመልካች ከጠየቁት ዳኝነት አንፃር በኑዛዜው የሚደርሳቸውን ድርሻ በትክክል ለይተው አልጠየቁም የሟች ቁም ኑዛዜ ፈራሽ የሚሆንበት በቂ ምክንያት ስላልቀረበ የአመልካች ክስ ውድቅ እንዲደረግ የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ…  

Previous Article ወ/ሮ ሰላማዊት ያደሳ እነ አቶ ፀሀዬ ጌታቸው(2ሰዎች) የሠ/መ/ቁጥር 256923
Next Article አቶ መንገሻ መሮ እና እነ መ/ር መስፍን መንገሻ (2ሰዎች) የሰ/መ/ቁጥር 258429
Print
5707

Documents to download

  • 257774(.pdf, 891.93 KB) - 632 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

‎በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአርባ ምንጭ ማዕከል...

23

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአርባ ምንጭ ማዕከል የተዘረጉትን የኢ-ፋይሊንግ፣ የትራንስክሪፕሽን እና የርቀት ችሎት አገልግሎቶችን በአካል ተገኝተው አስመርቀዋል።

የፍርድ ቤቶች አመራሮችና ዳኞች በአርባምንጭ ከተማ የችግኝ...

0

ነሐሴ 03/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተመራ የፍርድ ቤቶች ከፍተኛ አመራሮችና ዳኞች ልዑክ በአርባምንጭ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ ተካሄደ

26

ፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና የጉባኤው ሰብሳቢ ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በመክፈቻ ንግግራቸው፤ በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሠረት የተቋቋመው የፌደራል ጉባኤ የዳኝነት ነፃነትና ገለልተኝነትን የመጠበቅ፣ የአሰራር መመሪያዎችን የማውጣትና የማሻሻል እንዲሁም አገራዊ የዳኝነት ሂደቱን የማጠናከር ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለበት ገልጸዋል።

1345678910Last