Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ወ/ሮ ሙርሽዳ ሁሴን እና ወ/ሮ አልፊያ ሁሴን (13) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 257243 ጉዳዩ የውርስ ንብረት እና የሚስትነት ድርሻ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ጉዳዩ በጀመረበት በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች 1ኛ ጣ/ገብ ፤ከ1ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተጠሪዎች ከሳሽ፤ከ6ኛ እስከ 13ኛ ያሉ ተጠሪዎች እንዲሁ ጣ/ገብ አመልካች ነበሩ፡፡ አሁን ከ1ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተጠሪዎች አሁን በክርክሩ በሌሉ ሁለት ተከሳሾች ላይ ባቀረቡት ክስ የሟች አባታቸው አቶ ሁሴን አህመድ ንብረት የሆኑና በሟች ስም የሚገኙ 1ኛ/ በስር 1ኛ ተከሳሽ እጅ የሚገኝ በአሊቾ ውሪሮ ወረዳ ቀረሶ ቀበሌ ገሸዴ ተብሎ በሚጠራ መንደር የሚገኝ 3 ጥማድ የእርሻ መሬት፤2ኛ/ በስር 2ኛ ተከሳሽ እጅ የሚገኝ በወልቂጤ ከተማ 01 ቀበሌ የሚገኝ በ1050 ካ.ሜ ላይ ያለ የንግድ ቤት እና ከቤቱ የሚገኝ የኪራይ ገቢ፤3ኛ/ በስር 1ኛ ተከሳሽ እጅ የሚገኝ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 03-21138 የሆነ ዶልፊን ተሽከርካሪ፤ 4ኛ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በደቡብ ግሎባል ባንክ በሟች ስም በተከፈቱ ሂሳቦች የተቀመጠ ገንዘብ የሟች የውርስ ሀብት ስለሆነ በድርሻችን ተከሳሾች ያካፍሉን ሲሉ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ… Previous Article ሆሆተ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እናወ/ሮ ዘውዲቱ በዳሶ የሰ/መ/ቁ 256580 Next Article አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ተፈራ ፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 259947 Print 5332 Documents to download 257243(.pdf, 868.34 KB) - 809 download(s)
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ... Tuesday, June 30, 2026 181 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር የተቀናጀ አሰራርን በመፍጠር የዳኝነት ስርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል። Read more
ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል... ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል... Monday, June 29, 2026 196 በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለነጻ የህግ ድጋፍ የሚሰጡ የበጎ ፈቃድ ጠበቆች፣ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እና ነፃ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት አስተባባሪዎች የልምድ ልውውጥና ተግባር ተኮር የዉይይት ተካሂዷል። Read more
በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ... በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ... Monday, June 8, 2026 315 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንትነትና ምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ተገኝተው አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይትና ምልከታ አድርገዋል። Read more
ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ... ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ... Thursday, May 28, 2026 345 በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት የተሰራ ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል (One way mirror) በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት በይፋ ስራ ጀምሯል። Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more