Selam Warga / Wednesday, June 4, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ወ/ሮ ሰላማዊት ያደሳ እነ አቶ ፀሀዬ ጌታቸው(2ሰዎች) የሠ/መ/ቁጥር 256923 ጉዳዩ አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር እንደባልና ሚስት አብረዉ በኖሩበት ጊዜ ያፈራነዉ ንብረት ነዉ ያሏቸዉን ንብረቶች ለመካፈል ያቀረቡት ክስ አስቀድሞ ዉሳኔ ባገኘ ጉዳይ ለሁለተኛ ጊዜ የቀረበ ክስ ነዉ በሚል ዉድቅ በመደረገ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል በቀረበ የሰበር አቤቱታ መነሻ የተደረገዉን ክርክር የሚመለከት ነዉ፡፡ ክርክሩ በተጀመረበት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች በ1ኛ ተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ የአሁን 2ኛ ተጠሪ ጣልቃ በመግባት የተከራከሩ ሲሆን የክሱ ይዘት በአጭሩ - ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ከቀን 15/04/1999 ዓ.ም ጀምሮ እንደባልና ሚስት አብረን ስንኖር ያፈራነው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ክልል ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 121 የይዞታ መለያ ቁጥር AA000070806106 የሆነና በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ስፋቱ 403 ካሬ ሜትር የሆነ 8 የሚከራዩ ሰርቪስ ቤቶች እና 4 ክፍል ያለው ዋና ቤት እና ቦታ የጋራ ሀብት ስለሆነ ተጠሪ ድርሻዬን እንዲያካፍለኝ በማለት ሌሎች ንብረቶችንም እንደዚሁ በመጥቀስ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ መልካም ንባብ… Previous Article እነ አቶ ዮሐንስ ገ/ሚካኤል(5ሰዎች) እና ወ/ሮ ሃና ደርሶልኝ(2ሰዎች) የሰበር መዝገብ ቁጥር - 256463 Next Article እነ ወ/ሮ ተናኜ ሞላ ብርሐኔ(3ሰዎች) እና አቶ ሳሙኤል ተገኝ ኃይሌ የሰበር መዝገብ ቁጥር - 257774 Print 4853 Documents to download 256923(.pdf, 1.2 MB) - 683 download(s)
"የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ ፕሮጀክት የፍርድ ቤቶችን... "የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ ፕሮጀክት የፍርድ ቤቶችን... Friday, July 17, 2026 0 የዳኝነት ስርዓቱን ዲጂታላይዝ በማድረግ ቀልጣፋና ተደራሽ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ይቻል ዘንድ ላለፋት ዓመታት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ በፌደራል ፍርድ ቤቶች ላይ ሲተገብር የቆየው የቴክኖሎጂ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ያተኮረው የዋይድ ኤርያ ኔትወርክ ፕሮጀክት (Wide Area Network Project) የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ተካሂዷል። Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ... Tuesday, June 30, 2026 289 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር የተቀናጀ አሰራርን በመፍጠር የዳኝነት ስርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል። Read more
ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል... ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል... Monday, June 29, 2026 283 በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለነጻ የህግ ድጋፍ የሚሰጡ የበጎ ፈቃድ ጠበቆች፣ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እና ነፃ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት አስተባባሪዎች የልምድ ልውውጥና ተግባር ተኮር የዉይይት ተካሂዷል። Read more
በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ... በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ... Monday, June 8, 2026 408 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንትነትና ምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ተገኝተው አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይትና ምልከታ አድርገዋል። Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more