Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 የጉዳዩ አመጣጥ ተጠሪ ለአመልካች በቁጥር ማዕ/ሠ831በ/1/2 በ4/11/2015ዓ.ም በተጻፈ በቁጥር ማዕ/ሠ831በ/1/1 በ9/10/2015 በተጻፈ የምደባ ደብዳቤ ላይ የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ውስጥ በደረጃ XVIII በመደብ ማስታወቂያ ቁጥር 13/ግብ-1094 የስራ መደብ መጠሪያ የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሆነው መመደባቸውን በመግለጽ ሆኖም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሰራተኞች ምደባ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ከአመልካች ጋር የተወዳደሩት ተወዳዳሪው የትምህርት ደረጃ በዲፕሎማ የእንስሳት እርባታ (Animal Production and Rangeland management) ይዘው የልማት ጣቢያ ሰራተኛ ሆነው የሰሩት የስራ ልምድ አያያዝ ትክክል አይደለም በማለት ባቀረቡት ቅሬታ ላይ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴው ቅሬታው ተገቢ መሆኑን ተገንዝቦ ምደባው እንዲስተካከል በወሰኑት ውሳኔ መሰረት አመልካች የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሆነው የተመደቡበት የስራ ምደባ ከሀምሌ 1 ቀን 2015ዓ.ም ጀምሮ ተነስቷል በማለት በጻፈው ደብዳቤ ያሳለፈውን ውሳኔ አመልካች በመቃወም ለየኢፌዲሪ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስተዳደር ፍርድቤት ባቀረቡት ይግባኝ ያለኝ ዲፕሎማ እንስሳት እርባታ (Animal Production and RangeLand Management) ቢሆንም የተቀጠርኩት እና ለ6 አመት ያገለገልኩት ግን ሁሉንም የግብርና ሙያ ድጋፍ ማድረግ የሚችል አጠቃላይ እርሻ ዲፕሎማ ሙያ በሚጠይቀው ማለትም 2ኛ እና 1ኛ ደረጃ ሁለገብ ልማት ጣቢያ ሰራተኛ እንደቅደም ተከተሉ ነው፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ተፈራ ፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 259947 Next Article አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395 Print 6572 Documents to download 260594(.pdf, 874.35 KB) - 805 download(s)
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ... Tuesday, June 30, 2026 181 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር የተቀናጀ አሰራርን በመፍጠር የዳኝነት ስርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል። Read more
ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል... ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል... Monday, June 29, 2026 196 በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለነጻ የህግ ድጋፍ የሚሰጡ የበጎ ፈቃድ ጠበቆች፣ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እና ነፃ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት አስተባባሪዎች የልምድ ልውውጥና ተግባር ተኮር የዉይይት ተካሂዷል። Read more
በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ... በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ... Monday, June 8, 2026 315 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንትነትና ምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ተገኝተው አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይትና ምልከታ አድርገዋል። Read more
ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ... ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ... Thursday, May 28, 2026 345 በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት የተሰራ ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል (One way mirror) በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት በይፋ ስራ ጀምሯል። Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more