Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

ወ/ሮ የሺ ሽብሩ እና አቶ ከበደ ድንቁ የሰበር መ/ቁ255586

ጉዳዩ የግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች የጋብቻ ፍቺን ተከትሎ በቀረበው የንብረት ክርክር ስምምነት ባልተደረሰባቸው ንብረቶች ላይ የቀረበ ዳኝነትን የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ ተጀመረው በሄጦሳ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ከሳሽ ተጠሪ በሌላ በኩል ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡አመልካች ባቀረቡት ክስ የአመልካች እና ተጠሪ ጋብቻ ፍቺ ውሳኔን ተከትሎ በተደረገው የንብረት ክፍፍል መጋቢት 01 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረግነው የዕርቅ ስምምነት የተወሰኑትን ንብረቶች የተከፋፈልን ሲሆን በስምምነት ያልተከፈልነው በምስራቅ መንገድ፣በምዕራብ ገመቹ ተሾመ፣በሰሜን ብርብርሳ ጅማ፣በደቡብ የሺ ጎሹ የሚዋስኑትን ባለ 60 ቆርቆሮ የመኖሪያ ቤት፣13 ሉክ ቆርቆሮ ኩሽና ቤት፣22 ቆርቆሮ የዕቃ ማጠራቀሚያ፣20 ሉክ ቆርቆሮ ቤተሰብ የሚገቡበት፣ ሶስት ሳር ቤት፣አንድ የከብቶች የሚገቡበት በረት  ሌሎች ንብረቶችንም በዝርዝር በመጥቀስ ተጠሪ እንዲካፍለኝ የሚል ነው፡፡ተጠሪም በሰጡት መልስ የክርክር መነሻ የሆነው ንብረት በስምምነቱ ወቅት የእኔ እንደሆነ በተደረገው ዕርቅ ስምምነት የተደረሰበት በመሆኑ የቀረበው ክስ ውድቅ እንዲደረግ በሚል ተከራክረዋል፡፡መልካም ንባብ…

Previous Article አቶ አየለ ሽፈራው እና ጎባ ወረዳ ፍ/ቤት ጎባ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ. 255190
Next Article ወ/ሮ ቃልኪዳን አስቻለዉ ጸጋሁን እና ክሮስ ካንትሪ ትሬዲንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሰ.መ.ቁ.257068
Print
5189

Documents to download

  • 255586(.pdf, 865.45 KB) - 564 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

‎በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአርባ ምንጭ ማዕከል...

23

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአርባ ምንጭ ማዕከል የተዘረጉትን የኢ-ፋይሊንግ፣ የትራንስክሪፕሽን እና የርቀት ችሎት አገልግሎቶችን በአካል ተገኝተው አስመርቀዋል።

የፍርድ ቤቶች አመራሮችና ዳኞች በአርባምንጭ ከተማ የችግኝ...

0

ነሐሴ 03/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተመራ የፍርድ ቤቶች ከፍተኛ አመራሮችና ዳኞች ልዑክ በአርባምንጭ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ ተካሄደ

26

ፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና የጉባኤው ሰብሳቢ ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በመክፈቻ ንግግራቸው፤ በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሠረት የተቋቋመው የፌደራል ጉባኤ የዳኝነት ነፃነትና ገለልተኝነትን የመጠበቅ፣ የአሰራር መመሪያዎችን የማውጣትና የማሻሻል እንዲሁም አገራዊ የዳኝነት ሂደቱን የማጠናከር ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለበት ገልጸዋል።

1345678910Last