Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

የሰበሶራ ሴኪዩሪቲ ኃ/የተ/የግ/ማ እና ታቦር ሴራሚክስ ውጤቶች አ/ማህበር የሰ/መዝገብ ቁጥር -253253

ጉዳዩ የተጀመረው በሲዳማ ብሄራዊ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የስር ከሳሽ በተከሳሽ ላይ ያቀረበው ክስ ይዘቱ በአጭሩ የፋብሪካውን ደህንነት ለማስጠበቅ የጥበቃ ውል ከተከሳሽ ጋር በ02/05/2014 ዓ.ም መፈፀሙን ተከሳሽ ግዴታውን ባለመወጣት በተለያዩ ጊዜ የከሳሽ ንብረት የተሰረቀ በመሆኑ የንብረቱ ግምት ብር 4,825,295.00 (አራት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሃያ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና አምስት ብር) ጉዳት ያደረሰ በመሆኑ በፍ/ብ/ህ አንቀፅ 2028 መሰረት እንዲከፍል የሚል ነው፡፡ ከተከሳሽ በኩል ለክሱ የተሰጠው መልስ ይዘቱ በአጭሩ ከሳሽ ተሰረቀብኝ ብሎ ያቀረበው 38 ዕቃ በውላችን መሰረት ተቆጥሮ ያልተሰጠ ንብረት በመሆኑ በተከሳሽ ጥፋት ጉዳት አልደረሰበትም፡፡ ጠፉ ከተባሉት ንብረቶች ውስጥ በውላችን አንቀፅ 4.2 መሰረት ያልተረከብኩትና የማላውቀው ነው፡፡ ተሰረቀ ከማለት ውጪ ከየትኛው መጋዘን እንደተሰረቀ እና የትኛው እቃ እንደተሰረቀ በስማቸው ዘርዝሮ አለማቅረቡ እቃዎቹ አለመሰረቃቸውን የሚያሳይ ከመሆኑ በተጨማሪ በተለያዩ ቦታ ላይ እርስ በርስ የሚጋጭ የዋጋ ዝርዝር አቅርቧል፡፡ የጠቀሳቸው እቃዎች ለመያዝ ፍቃድ የለውም፡፡ በስርቆት ጥርጣሬ በተደረገ ቆጠራ የከሳሽ ሰራተኞች በኦዲት ይጠየቃሉ እንጂ ከውጪ እየጠበቁ ያሉ ጥበቃዎች ተጠያቂ ሊሆኑ የሚችሉበት አግባብ ስለሌለ ተከሳሽ ለከሳሽ የሚከፍለው ገንዘብ የለም ተብሎ እንዲወሰን የሚል መልስ ከሰጡ በኃላ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅርቧል፡፡ ዝርዝሩ በአጭር ከሳሽ ጠፍቶብኛል በሚል ምክንያት በመካከላችን ያለውን ውል በ28/01/2014 ዓ.ም አቋርጦ ያለበትን ውዝፍ ደመወዝ የ 10 ወር 834,652.21 (ስምንት መቶ ሰላሳ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ሁለት ብር ከሃያ አንድ ሳንቲም) በተጨማሪ ለተመደቡ ለአራት ጥበቃዎች የ 6 ወር ብር 55,643.47 (ሃምሳ አምስት ሺህ ስድስት መቶ አርባ ሶስት ብር ከአርባ ሰባት ሳንቲም) በውላችን መሰረት ያለማስጠንቀቂያ ውሉን በማቋረጡ ብር 92,739.12 ውል ለማፍረሱ ቅጣት 5,000.00 ብር በአጠቃላይ ብር 990,816.23 (ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሺህ ስምንት መቶ አስራ ስድስት ብር ከሃያ ሶስት ሳንቲም) ከሳሽ ለተከሳሽ እንዲከፍል የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ…

Previous Article የአቶ ጂወይድ ሰይድ ሳሊም እና አቶ አብዱልዋሲ አህመድ ኢብራሂም(2ሰዎች) ሰ/መ/ቁ. 253517
Next Article የአቶ ከበደ ተክለማርያም ወራሾች፡-እነ አቶ ደረጀ ከበደ.(4ሰዎች)እና እነ አቶ ደረጀ ተስፋዬየሰ/መ/ቁ253101
Print
4381

Documents to download

  • 253253(.pdf, 836.43 KB) - 489 download(s)

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

"የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ ፕሮጀክት የፍርድ ቤቶችን...

0

‎የዳኝነት ስርዓቱን ዲጂታላይዝ በማድረግ ቀልጣፋና ተደራሽ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ይቻል ዘንድ ላለፋት ዓመታት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ በፌደራል ፍርድ ቤቶች ላይ ሲተገብር የቆየው የቴክኖሎጂ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ያተኮረው የዋይድ ኤርያ ኔትወርክ ፕሮጀክት (Wide Area Network Project) የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ...

289

‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር የተቀናጀ አሰራርን በመፍጠር የዳኝነት ስርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል።

ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል...

283

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለነጻ የህግ ድጋፍ የሚሰጡ የበጎ ፈቃድ ጠበቆች፣ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እና ነፃ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት አስተባባሪዎች የልምድ ልውውጥና ተግባር ተኮር የዉይይት ተካሂዷል።

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ...

408

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንትነትና ምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ተገኝተው አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይትና ምልከታ አድርገዋል።

1345678910Last