Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ቢሮ ዓቃቤ ሀግ እና ወ/ሮ መዓዛ በልስቲየሠ/መ/ቁጥር 248735

ጉዳዩ ያለደረሰኝ ግብይት የማከናወን የወንጀል ክስን የሚመለከት ሆኖ ክሱ የቀረበው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደጀን ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን በአመልካች እና በሰበር ክርክሩ የሌሉት ሁለት ግለሰቦች ላይ ቀርቦ የነበረው ክስ፡- የክልሉን የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 241/2008 አንቀጽ 131/1 እና 119/1 ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር 0052005902 ፤ በንግድ ምዝገባ ቁጥር AM/EG/DEJEN/1/0001230/2010 በተጠሪ ስም የተመዘገበ በደጀን ከተማ 01 ቀበሌ በሚገኘው ሆቴልና ሉካንዳ ቤት የንግድ ሥራ በደረጃ “ለ” ግብር ከፋይነት ተሰማርተው የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅና ባለቤት ሁነው እየሰሩ እያለ ሚያዝያ 6 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 5:50 ሰዓት ላይ ደርብ አበጀና አፀደ ከተማው የተባሉ ደንበኞች አንድ በየአይነቱ ምግብ እና አንድ ሊትር የታሸገ ውሃ ተጠቅመው ደርብ አበጀ የተባለው ለተጠቀሙበት ክፍያ ብር 200.00(ሁለት መቶ) ለአስተናጋጅ ሲሰጥ የብር 135.00 (አንድ መቶ ሰላሳ አምስት) ሽያጭ ያለደረሰኝ ፈጽመዋል የሚል ነው፡፡

ተጠሪም የእምነት ክህደት ቃላቸውን ተጠይቀው ከአዲስ አበባ የሂክምና ቀጠሮ ስለነበራቸው ወንጀሉ ተፈጽሟል በተባለበት ቦታ ያልነበሩ መሆኑን፤ያለደረሰኝ ግብይት ይፈፀም አይፈፀም እንደማያውቁ፤ የድርጅቱን ሥራ በአግባቡ እንዲሰሩ ለሥር ለሥር 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች እንዳሳወቁ ገልጸው ጥፋተኛ አይደለሁም በማለት ተከራክረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ-ሕግ ምስክሮች የሰጡትን የምስክርነት ቃል ሰምቶ ወንጀሉ ተፈጽሟ በተባለት ቀንና ሰዓት ተጠሪ በድርጅቱ ውስጥ አለመኖራቸው በቃቤ-ሕግ ምስክሮች መነገሩን ጠቅሶ አመልካች የሥር 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በተመደቡበት የስራ ኃላፊነት ብቁ ሠራተኞች መሆናቸውን በማመን ወደ ህክምና የሄዱ መሆኑ ተረጋግጧል በሚል በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕጉ ቁጥር 141 መሠረት በነፃ ያሰናበተ ሲሆን፤አመልካች ተጠሪ ከክሱ በብይን በነፃ መሰናበታቸውን በመቃወም ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195 መሠረት መሰረዙን ተከትሎ አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩ የፌደራል በመሆኑ ለክልል ሰበር ሰሚ ችሎት ሊቀርብ አይገባም በሚል ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡      

የሰበር ቅሬታ የቀረበው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩ የፌዴራል ነው በሚል የሰበር አመልካች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ ባለመቀበል የሰጠውን ፍርድ በመቃወም ሆኖ የሰበር ቅሬታው በአጭሩ፡- ተጠሪ በደጀን ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት በሆቴልና ሉካንዳ ቤት ንግድ ዘርፍ በደረጃ “ለ” በክልል ግብር ከፋይነት ተመዝግበው ሲሰሩ በክልሉ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 240/2008 አንቀፅ 79/2 እንዲሁም በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 241/2008 አንቀፅ 19/3 የተመለከተውን ደረሰኝ የመስጠት ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 241/2008 አንቀፅ 131/1 እና 119/1 የተመለከተውን በመተላለፍ በፈፀሙት ወንጀል በደጀን ወረዳ ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦባቸው ክርክር ተደርጎ የወረዳው ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ሥልጣኑ ክርክሩን አይቶ የሰጠውን ውሳኔ የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በይግባኝ ሰሚነቱ የተመለከተውን የመጨረሻ ውሳኔ ያገኘን የክልል ጉዳይ ተጠሪ በክልሉ የደረጃ “ለ” ግብር ከፋይ እንጅ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ባልሆኑበት በክልል ግብር ከፋይነታቸው ለፈፀሙት የወንጀል ጥፋት ተጠያቂ የሚሆኑት በክልል የታክስ አስተዳደር አዋጅ መሆኑ እየታወቀ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር አጣሪው ችሎት ጉዳዩን የማየት የሥረ-ነገር ሥልጣን የለኝም በማለት አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አለመቀበሉ የአማራ ብሔራዊ ክልል ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ ቁጥር 223/2007 አንቀፅ 17/1 ፤ እንዲሁም የክልሉን ፍርድ ቤቶች ለማቋቋም ተሻሽሎ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 281/2014 አንቀፅ 24 ድንጋጌዎችን የሚቃረን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት በሰበር ሰሚ ችሎቱ እንዲታረምላቸው ጠይቃዋል፡፡መልካም ንባብ…

Previous Article አቶ ተገኝ ደምሴ ወንድአፍራሽ እና ወ/ሮ አየለች ደሳለኝ እንዳሻው የሰበር መ/ቁጥር 248810
Next Article ሲቀላ ክፍለ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና ወ/ሮ አረግዋ ጠብቀው የሰበር መዝገብ ቁጥር - 247036
Print
5162

Documents to download

  • 248735(.pdf, 1.07 MB) - 626 download(s)

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ...

192

‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር የተቀናጀ አሰራርን በመፍጠር የዳኝነት ስርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል።

ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል...

208

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለነጻ የህግ ድጋፍ የሚሰጡ የበጎ ፈቃድ ጠበቆች፣ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እና ነፃ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት አስተባባሪዎች የልምድ ልውውጥና ተግባር ተኮር የዉይይት ተካሂዷል።

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ...

335

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንትነትና ምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ተገኝተው አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይትና ምልከታ አድርገዋል።

ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ...

356

‎በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት የተሰራ ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል (One way mirror) በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት በይፋ ስራ ጀምሯል።

12345678910Last