Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

የአቶ ከበደ ተክለማርያም ወራሾች፡-እነ አቶ ደረጀ ከበደ.(4ሰዎች)እና እነ አቶ ደረጀ ተስፋዬየሰ/መ/ቁ253101

ጉዳዩ የውርስ ማጣራትን ተከትሎ የቀረበ የሚስት የንብረት ድርሻን የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ የተጀመረው በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን የአመልካቾች አዉራሽ ሟች አቶ ከበደ ተክለማሪያም አመልካች፣የአሁኑ ተጠሪዎች በሌላ በኩል ተጠሪዎች በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአመልካቾች አውራሽ በስር ፌደራል መጀመሪያ ደረጃ  ፍርድ ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ይዘት በአጭሩ ልጃቸው ሟች ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ ልጅ ሳይወልዱ በመሞታቸው ከባለቤታቸው አስር አለቃ ተስፋዬ ደስታ ጋር ያፈሩት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የቤት ቁጥር 682 የሆነው ንብረት እና ከቤቱ የተሰበሰበው የኪራይ ሀብት በውርስ አጣሪ ተጣርቶ የድርሻዬ እንዲለይ በሚል ያቀረቡ ሲሆን የሟቿ አባት የሆኑት አቶ ከበደ ተክለማሪያም በመሞታቸው አመልካቾች በተተኪ ወራሽነት ወደ ክርክሩ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ተጠሪዎችም በቀረበው አቤቱታ ላይ መልስ በመስጠት የአቤቱታው መነሻ የሆነው የውርስ ሀብቱም ተጣርቶ እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡በውርስ አጣሪው ተጣርቶ የቀረበው ርፖርት ይዘትም የአስር አለቃ ተስፋዬ ደስታ በመ/ቁ 158482 ህዳር 03 ቀን 2013 ዓ.ም የውርስ ሀብት ተጣርቶ በጸደቀው የውርስ ሀብት ሪፖርት አስር አለቃ ተስፋዬ ደስታ ሰኔ 09 ቀን 1995 ዓ.ም ባደረጉት ኑዛዜ መሰረት የክርክር መነሻ በሆነው ቤት እና ይዞታ ላይ የሟች ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ ድርሻ 1/4ኛ ነው የሚል ውሳኔ የተሰጠ በመሆኑ አመልካቾች የሟቿን ድርሻ የቤቱን እንደዚሁም ከኪራይ የሚገኘውን ገቢ 1/4ኛ ድርሻ እንዲካፈሉ የሚል ነው፡፡ግራ ቀኙም በቀረበው የውርስ አጣሪ ሪፖርት ላይ ያላቸውን አስተያየት የሰጡ ሲሆን ፍ/ቤቱም የሟች አስር አለቃ ተስፋዬ ደስታ የውርስ ሀብት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 158482 ላይ ተጣርቶ የፀደቀ ሲሆን በዚህ የጸደቀው የውርስ አጣሪ ሪፖርት ላይ የውርስ ሀብት የሆነውን ቤት ሟች አስር አለቃ ተስፋዬ ደስታ በሰኔ 09 ቀን 1995 ዓ.ም ባደረጉት ኑዛዜ  በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የቤት ቁጥር 682 ከሆነው ቤት እና ይዞታ ላይ የሟች ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ ድርሻ 1/4ኛ መሆኑን ፍ/ቤቱ የቀረበው በውርስ አጣሪ ሪፖርት ተረጋግጧል፣አመልካቾችም ይህን ውሳኔ አላሻሩም፣ከቤት ቁጥር 682 ላይ የሟች ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ የሚስትነት ድርሻ ግማሽ ድርሻ እንደሆነ የሚገልጽ ውሳኔ አላቀረቡም፣አመልካቾች ይህ ውሳኔ ስለመሻሩም ያቀረቡት ማስረጃ የለም፣ ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ የሟች አስር አለቃ ተስፋዬ ደስታ ሚስት ስለመሆኗ እና ቤት እና ይዞታውን በጋራ አፍርተዋል በሚል የተሰጠ ውሳኔ አልቀረበም፣ ሟች ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ ከሟች አስር አለቃ ተስፋዬ ደስታ ጋር በመሆን ያፈሩ በመሆኑ ግማሹ የሟች ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ የሚስትነት ድርሻ ሊሆን ይገባል የሚል ክርክር ሊቀርብ የሚገባው በቤተሰብ ችሎት እንጂ በዚህ በተያዘው ችሎት ባለመሆኑ የሟች ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ ድርሻ ከሆነው                                                                                                                                                                      1/4ኛ ድርሻ ላይ አመልካቾች እያንዳንዳቸው 1/4ኛ ድርሻ አላቸው።የቤት ኪራይን ገቢን በተመለከተ የተሰበሰበው ገቢ በአጠቃላይ ብር 444,400 ስለሆነ ከዚህ ገንዘብ ላይ ሟች ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ ድርሻ ብር 111,100 በመሆኑ ሟች ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ ድርሻ ላይ አመልካቾች እያንዳንዳቸው 1/4ኛ ማለትም ብር 27,775 ብር የሚደርሳቸው ሆኖ ለተለያዩ ጉዳዮች የወጣው ወጪ ብር 108,259.11 በመሆኑ የሟች ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ ድርሻ ብር 27,064.78 ስለሆነ ከዚህ ላይ አመልካቾች እያንዳንዳቸው ብር 6943.75 የሚለከፍሉት ውርስ ሃብት ዕዳ ይሆናል በማለት በውርስ አጣሪ የቀረበውን ሪፖርት አጽድቆታል፡፡መልካም ንባብ…

Previous Article የሰበሶራ ሴኪዩሪቲ ኃ/የተ/የግ/ማ እና ታቦር ሴራሚክስ ውጤቶች አ/ማህበር የሰ/መዝገብ ቁጥር -253253
Next Article ወ/ሮ ጎበኔ ጉዬ እናአቶ ሁሴን ሶራ የሰበር መዝገብ ቁጥር 249911
Print
4375

Documents to download

  • 253101(.pdf, 1.08 MB) - 543 download(s)

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ...

181

‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር የተቀናጀ አሰራርን በመፍጠር የዳኝነት ስርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል።

ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል...

196

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለነጻ የህግ ድጋፍ የሚሰጡ የበጎ ፈቃድ ጠበቆች፣ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እና ነፃ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት አስተባባሪዎች የልምድ ልውውጥና ተግባር ተኮር የዉይይት ተካሂዷል።

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ...

315

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንትነትና ምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ተገኝተው አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይትና ምልከታ አድርገዋል።

ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ...

345

‎በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት የተሰራ ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል (One way mirror) በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት በይፋ ስራ ጀምሯል።

1345678910Last