Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት እና አቶ አበራ ተፈሪ የሰ/መ/ቁጥር 254101

ጉዳዩ የጉዳት ካሳን የሚመለከት ሲሆን ክሱ በጀመረበት የፌ/ከ/ፍ/ቤት አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ ነበር፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት የክስ ይዘትም፡- የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-53974 ኢ.ት እንዲሁም ኮድ 3-1775 ኢ.ት ለሆነው ተሽከርካሪያቸው ከአመልካች አጠቃላይ የንግድ ተሸከርካሪ የመድን ዋስትና የገዙ መሆኑን፤ ይህ መድን የተገባለት ተሸከርካሪያቸው በስራ ላይ እያለ በምዕራብ ወለጋ ዞን መንዲ ተብሎ ከሚጠራ አካባቢ ህዳር 17 ቀን 2011 ዓ.ም ያልታወቁ ግለሰቦች አስገድደው እንዲቆም አድርገው ተሸከርካሪውን፤ጭኖት የነበረውን ቢራ እና የሽያጭ ደረሰኞች ይዘው መሰወራቸውን፤ ይህ ስርቆት መፈጸሙን የተጠሪ ወኪል እንዳወቁ ወዲያውኑ ለአመልካች ድርጅት አሶሳ ቅርንጫፍ ማሳወቃቸውን፤ ከበርካታ ክትትል በኋላ ነሀሴ 16 ቀን 2011 ዓ.ም ተሳቢው ምንም ጉዳት ሳይደርስበት የተገኘ መሆኑን እና ዋናው ተሸከርካሪ ግን ተቃጥሎ መገኘቱን፤ ነሀሴ 17 ቀን 2011 ዓ.ም ፖሊስ ባደረገው ሪፖርት ተሽከርካሪው እና ተሳቢው 2,400 ሳጥን ቢራ ጭኖ ከአ.አ ወደ አሶሳ በመጓዝ ላይ እንዳለ ህዳር 17 ቀን 2011 በሌቦች ተሰርቆ ዋናው ተሸከርካሪ በቃጠሎ ከጥቅም ውጭ ሆነ መገኘቱን መግለጹን፤አመልካች ካሳ እንዲከፍል ሲጠየቅ ደርጊቲ የተፈጸመው በሽፍቶች ነው፤ በኋላ  ላይ ደግሞ ድርጊቱ የተፈጸመው በጦርነት እንቅስቃሴ እና መሰል ሁኔታዎች ነው፤ እንዲሁም ስለድርጊቱ መከሰት አላሳወቃችሁኝም በማለት የካሳ ክፍያ ጥያቄአቸወን ውድቅ ማድረጉን ገልጸው ንብረቱ በእሳት ሙሉ በሙሉ የወደመ ስለሆነ በመድን ውሉ ለንብረቱ ከተሰጠው የዋስትና ጣሪያ ብር 2,000,000.00 ከተወሰነው የአደጋ መነሻ ውስጥ ከፍተኛውን 5 % ተቀናሽ በማድረግ 1,900,000.00 ከወጪና ኪሳራ ጋር አንዲከፍል ይወሰንልኝ ሲሉ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…

Previous Article ኤልያስ ዳሪ እና እነ ወ/ሮ ሰናይት አብርሃ (6) ሰዎች የሰ/መ/ቁ. 253783
Next Article ሆሆተ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እናወ/ሮ ዘውዲቱ በዳሶ የሰ/መ/ቁ 256580
Print
3100

Documents to download

  • 254101(.pdf, 877.5 KB) - 439 download(s)

«February 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
2627282930311
2345678
9101112131415
16171819202122
2324252627281
2345678

ሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭት መከላከልና...

0

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፌዴራል ሥነ-ምግባርና ፀረ -ሙስናና ኮሚሽን ጋር በመተባበር በሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና የጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር ላይ ከፍርድ ቤት ዘርፍ ለተውጣጡ የስራ ሃላፊዎች የካቲት 5 እና 6 ቀን 2018 ዓ.ም ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የኢትዮጵያ...

118

የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ቢኒያም ኤሮ ናቸው፡፡

በዳኝነት ስርአቱ ውስጥ ለህጻናት ተስማሚ የፍትህ ስርአትን...

106

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት በዳኝነት ስርአት ውስጥ ለህጻናት ተስማሚ የፍትህ ስርአትን ለማጎልበት ከአጋር ድርጅቶች ጋር የጋራ ውይይት መድረክ በቀን 03/06/2018 ዓ.ም ተካሂዷል።

ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንቶች ...

98

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዲስ ተሿሚ ምክትል ፕሬዚዳንቶች ክቡር አቶ ልዑል ካህሳይን እና ክቡር አቶ ምትኩ ማዳን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመራሮች እና የስራ ሃላፊዎች ጋር በቀን 02/06/2018 ዓ.ም ትውውቅ እና የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በቆይታቸውም የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሪፎርም ተግባራት ላይ ገለጻ እና የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ላይ ማብራሪያ የቀረበላቸው ሲሆን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚገኙ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችንም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

1345678910Last