Selam Warga / Wednesday, June 4, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቀበሌ 11/12/08 ሸማቾች ኃ/የተ/ሕ/ሥ/ማ እና አቶ እንኮሳ አመንቴ ሱፋ(9ሰዎች)የሰ.መ.ቁ 249104 የክሱ ይዘት በአጭሩ፡- በየካ አውራጃ ከፍተኛ 16 ቀበሌ 08 የቀድሞው የቀበሌ አመራሮች የተጠሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በማሰብ ከህብረት ሥራ ማህበር ብር 29.000 (ሃያ ዘጠኝ ሺህ ብር) በብድር መልክ ወጪ ተደርጎ ቤት እንድንገነባ ተፈቅዶልን ቤቶቹን በመገንባት የብድር ገንዘብም ተመልሷል፤ ተጠሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ነዋሪዎች በራሳችን ገንዘብ ቤቶቹን አፍርሰን እንደሰራን በወቅቱ የነበሩ የአመልካች አመራሮች አረጋግጠው በሰነድ ማስረጃ ሰጥተውናል፤ ተጠሪዎች ከ1982/1983 ጀምሮ በሰነድ አልባ በመኖሪያ ቤቶቹን ገንብተን እየኖርን እያለን ከ20 ዓመታት በኋላ አመልካች ለተጠሪዎች ያሰበ በማስመሰል ከፊሎቹን የተጠሪዎች ቤቶች ለልማት ሊፈርሱ ስለሚችሉ የጋራ መኖሪያ ቤት መንግስት እንዲሰጣችሁ እና ቀበሌው እንዲያውቃችሁ በማለት ከሱ ጋር የቤት ኪራይ ውል እንድንዋዋል ሲጠይቀን ተጠሪዎችም የአመልካች ህብረት ሥራ ማህበር አባላት በመሆናቸን እና መንግስታዊ ተቋም ነው ብለን በማመን ከ2ኛ ተጠሪ በስተቀር ከአመልካች ጋር የቤት ኪራይ ውል ልንፈርም ችለናል፤ተጠሪዎች የይዞታ ማረጋገጫ ለመቀበል በሂደት ላይ እያለን አመልካች ከህግም ሆነ ከውል የመነጨ መብት ሳይኖረው እንዳይፈጸም አድርጓል፤ አመልካች ተጠሪዎችን በማታለል ባስፈረመን የኪራይ ውል መነሻነት ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኪራዩን ከፍለው ቤቱን ያስረክቡኝ በማለት ክስ አቅርቦ ተጠሪዎች ቤቱን እንድናስረክብ ተወስኗል፤ ሆኖም ከመነሻው ቦታው በጎርፍ ምክንያት ለህይወታችን እስጊ በመሆኑ ልዋጭ ቦታ እንዲሰጠን የሚመለከተውን አካል ጠይቀን ሲሰጠን በቦታው ላይ ቀበሌው ቤት መስራት ካልቻለ ነዋሪዎች በራሳችን ወጪ እንድንሰራ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት በራሳችን ወጪ ቤት ገንብተን በስማችን ውሃ፣ መብራት እና መሰል መሰረታዊ አገልግሎቶችን አስገብተን የምንኖርበት ቤት በመሆኑ ቤቶቹ የተጠሪዎች ናቸው ተብሎ ይወሰንልን በማለት ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article አቶ ታዬ ከተማ ደጋጋ እናእነ አቶ ሙሉጌታ ታደሰ (3ሰዎች) የሰ/መ/ቁጥር---244417 Next Article እስጢፋኖስ /ዩቡና/ ዲራጎ እና የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 251519 Print 5417 Documents to download 249104(.pdf, 865.58 KB) - 580 download(s)
BRICS Chief Justices' Forum Concludes BRICS Chief Justices' Forum Concludes Sunday, September 6, 2026 4 September 6, 2026 (Federal Supreme Court) The BRICS Chief Justices forum, hosted by the Supreme Court of India from September 4 to September 6, 2026, has concluded. Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ... Monday, August 31, 2026 47 ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሠራተኞችን መብት፣ ግዴታና የዲሲፕሊን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናን ጨምሮ ልዩ ልዩ መርሃ-ግብሮችን በማካሄድ ተጠናቋል። Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመታዊ የሰራተኞች መድረክ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመታዊ የሰራተኞች መድረክ... Monday, August 31, 2026 41 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሰራተኞች መድረክ በዛሬው ዕለት መካሄድ የጀመረ ሲሆን የፍርድ ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሂዷል። Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በቀጣይ የአምስት... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በቀጣይ የአምስት... Friday, August 28, 2026 72 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክቡራን ዳኞች የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን የቀጣይ አምስት ዓመታት (2019-2023) የስትራቴጂክ ዕቅድ ረቂቅ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ አካሂደዋል። Read more