Selam Warga / Wednesday, June 4, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ደጀኔ ደበላ አልቀረበም እና ኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 251700 ጉዳዩ ይለፍ ወረቀት ሳይይዙ የግብርና ምርቶችን ማጓጓዝ ወንጀል የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ የተጀመረው በሰሜን ሸዋ ዞን ወራ ጃርሶ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡በተጠሪ የቀረበውም ክስ አመልካች የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ያወጣውን የገበያ ቁጥጥርና የምርት ጥራት አዋጅ ቁጥር 234/2013 አንቀፅ 26(3) እና 5 በመተላለፍ ታህሳስ 03 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 4፡00 ሰአት በወራ ጃርሶ ወረዳ ቀሬ ጎሃ ከተማ ቀበሌ 02 ልዩ ቦታው ኬላ ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ የሰሌዳ ቁጥር 3-16932 ኢት በሆነ ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ላይ 220(ሁለት መቶ ሃያ) ኩንታል ባቄላ ግምቱ 836,000 (ስምንት መቶ ሰላሳ ስድስት ሺህ) የሆነውን ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል አቅጣጫ በመጓዝ ላይ እያለ ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ሲደርስ በኬላ ተቆጣጣሪዎች ሲፈተሽ የንግድ ፍቃዱና የመነሻ እና መድረሻ የይለፍ ወረቀት ሳይይዝ በመጓዙ ያለ ፍቃድ የግብር ምርቶችን በማጓጓዝ ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ….. Previous Article እነ ወ/ሮ ዘውዲቱ ድንቁ(2ሰዎች)የቀድሞ አርጋፋ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት (በአሁን አርጋፋ ማዘጋጃ ቤት)የሰ/መ/ቁ፡- 250597 Next Article አቶ ቴዎድሮስ መስፋን ህንፃ ሥራ ተቋራጭእና አዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት (በአሁኑ - የአ/አ ቤ/ልማት ኮርፖሬሽን) የሰበር መ/ቁ 253303 Print 6502 Documents to download 251700(.pdf, 881.19 KB) - 717 download(s)
ለህጻናት ተስማሚ የሆነ የፍትህ ስርዓትን ለማስፈን ያለመ... ለህጻናት ተስማሚ የሆነ የፍትህ ስርዓትን ለማስፈን ያለመ... Wednesday, September 9, 2026 34 በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት፤ ለህጻናት ተስማሚ የሆነ የፍትህ ሂደት ትግበራን በተመለከተ ለመርማሪ ፖሊስ አባላት እና ለክቡራን ዳኞች በሁለት ዙር የተከፈለ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ Read more
BRICS Chief Justices' Forum Concludes BRICS Chief Justices' Forum Concludes Sunday, September 6, 2026 154 September 6, 2026 (Federal Supreme Court) The BRICS Chief Justices forum, hosted by the Supreme Court of India from September 4 to September 6, 2026, has concluded. Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ... Monday, August 31, 2026 77 ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሠራተኞችን መብት፣ ግዴታና የዲሲፕሊን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናን ጨምሮ ልዩ ልዩ መርሃ-ግብሮችን በማካሄድ ተጠናቋል። Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመታዊ የሰራተኞች መድረክ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመታዊ የሰራተኞች መድረክ... Monday, August 31, 2026 116 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሰራተኞች መድረክ በዛሬው ዕለት መካሄድ የጀመረ ሲሆን የፍርድ ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሂዷል። Read more