Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

ጠቋሬ ፈለቀ እና አባ ምትኩ ዘዉዴ የሰ.መ.ቁ.253916

ይህ የአፈጻጸም ክርክር የተጀመረዉ በአማራ ክልል በዳህና ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች የሥር ፍርድ ባለመብት፣ የአሁን ተጠሪ የሥር የፍርድ ባለዕዳ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር፡፡ ጉዳዩ ለዚህ ሰበር ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ አመልካች የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.0337693 ሰኔ 15 ቀን 2015 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ በግራ ቀኛዉ መካከል በነበረዉ የይዞታ ክርክር የሥር የወረዳዉ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ ለክርክር መነሻ የሆነዉን ይዞታ ለቆ ለአመልካች እንዲያስረክብ መወሰኑን መዝገቡ ያሳያል፡፡ የአሁን አመልካች ፍርዱን ለማስፈጸም የአፈጻጸም አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን የወረዳዉ ፍ/ቤቱ የአሁን አመልካች በይዞታዉ ላይ ባለመብት ከመሆኑ በፊት የአሁን ተጠሪ በይዞታዉ ላይ ሁለት ክፍል ያለዉን ቤት መስራቱን በማረጋገጥ አመልካች የቤቱን ግምት ለተጠሪ እንዲከፍልና ተጠሪ ይዞታዉን ለቆ ለአመልካች እንዲያስረክብ ብይን መስጠቱን የዉሳኔዉ ግልባጭ ያመለክታል፡፡ በየደረጃዉ ያሉት የክልሉ ፍ/ቤቶችም የቀረበላቸዉን ቅሬታ ዉድቅ በማድረግ የሥር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በማጽናት መወሰናቸዉን የሥር ፍ/ቤት የዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል፡፡ የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ፡፡

የአሁን አመልካች መስከረም 4 ቀን 2016 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ የአሁን ተጠሪ በዋናዉ ጉዳይ ላይ ተከራክሮ የቤት ግምት ካሳ እንዲከፈለዉ የፍርድ ባለመብት ባልሆነበት የሥር ፍ/ቤት በዋናዉ ፍርድ የቤት ግምት ካሳ ጉዳይ ለተጠሪ እንዲከፈል ባልተወሰነበት፣ ተጠሪ በይዞታዉ ላይ በሕገወጥ መንገድ ቤቱን ሲሰራ አመልካች እየተቃወምኩት መሆኑን ተረጋግጦ ባለበት የሥር ፍ/ቤት በዋናዉ ፍርድ መሰረት ለክርክር መነሻ የሆነዉን 10 በ15 ካ.ሜ የሆነዉን ይዞታ ተጠሪ ለአመልካች እንዲለቅ ማስፈጸም ሲገባዉ አመልካች ለተጠሪ የቤቱን ግምት እንዲከፍል መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ እንዲታረምልኝ በማለት በዝርዝር አመልክቷል፡፡መልካም ንባብ….

Previous Article እስጢፋኖስ /ዩቡና/ ዲራጎ እና የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 251519
Next Article እነ አቶ አመድ ሙሜ(2ሰዎች)የእና ወ/ሮ አሚናት ኡስማንሰ/መ/ቁጥር 254020
Print
4400

Documents to download

  • 253916(.pdf, 1.03 MB) - 544 download(s)

«June 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
25262728293031
1234567
891011121314
15161718192021
22232425262728
293012345

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ...

78

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንትነትና ምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ተገኝተው አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይትና ምልከታ አድርገዋል።

ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ...

97

‎በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት የተሰራ ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል (One way mirror) በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት በይፋ ስራ ጀምሯል።

ለሶሻል ወርክ ባለሞያዎች በተዘጋጀ የስልጠና ማንዋል ረቂቅ...

119

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት በፍትህ ስርዓት ውስጥ የሚያገለግሉ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሞያዎችን ሚና ለማጎልበት የሚያግዝ የስልጠና ማንዋል የመጨረሻ ረቂቅ ሰነድ ላይ የውይይት እና የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሂዷል፡፡ 

‎የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን...

106

በኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ እና የጄሲኢ (JCE) ሰብሳቢ በሆኑት በክብርት ዳኛ ሱዛን ኞኪ ንዱንጉ የተመራው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ላለፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር አጠናቋል።

1345678910Last