Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

እነ አቶ ዮሐንስ ገ/ሚካኤል(5ሰዎች) እና ወ/ሮ ሃና ደርሶልኝ(2ሰዎች) የሰበር መዝገብ ቁጥር - 256463

አመልካቾች ሚያዚያ 2 ቀን 2015 ዓ.ም በተፃፈ የመቃወም አቤቱታ ሟች አባታቸው አቶ ገ/ሚካኤል ኃ/ማርያም በህይወት እያሉ እንዲሁም አባታቸው ከሞቱ በኃላ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ የሆኑት፣ አመልካቾችና የ 96 አመት የሆኑት የግራ ቀኙ እናት ጋር በአልኮልና በለስላሳ ማከፋፈያ እንዲሁም በሸቀጣሸቀጦች ጅምላ ንግድ ስራ ተሰማርተው በቁጥር ስምንት የሆኑ የተለያዩ ተሸከርካሪዎች፤ ደምቢዶሎ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ሆቴል፣ የቡና ማበጠሪያ፣ የመጠጥ ማከፋፈያ፣ የመኖሪያ ቤትና መጋዘን፤ በቡና ግብይት ላይ የነበረ አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ብር፣ በአዋሽ ባንክ ያለ 50 የአክስዮን ድርሻ በጋራ ያፈሩ መሆኑንና ተጠሪዎች ጋብቻ ሲፈፅሙ እነዚህ ንብረቶች የአመልካቾች መሆናቸውን በጋብቻ ውላቸው ተስማምተዋል፡፡ እነዚህ ንብረቶች ከፊሎቹ ባሉበት ከፊሎቹ በሽያጭ ሆነ በሌላ መንገድ እየተለዋወጡና እየተቀላቀሉ ብዛታቸው 16 የሆኑ በተጠሪ ስም የተመዘገቡ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፤ በተጠሪ ስም የተመዘገቡ በአዋሽ ባንክ፣ በኦሮሚያ ባንክ፣ በህብረት ባንክ ያሉ አክስዮኖች፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በአዋሽ ባንክ፣ በህብረት ባንክ፣ በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ፣ በኦሮሚያ ባንክ ተጠራቅሞ የሚገኝ ገንዘብ እና ተሸከርካሪዎች በቤተሰብ የተፈሩና በተጠሪዎች የጋብቻ ውል ላይም የቤተሰብ ንብረቶች መሆናቸው ተረጋግጦ እያለ ተጠሪዎች ከዚህ በተቃራኒ በሰበታ ከተማ የሚገኘውን በ 612 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ቤት፣ በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ የሚገኘውን መኖሪያ ቤት እንዲሁም በዚህ ከተማ በ 2,000 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሆቴል ን በመተው ሌሎችን ንብረቶች የተጠሪዎች የጋራ ንብረት ነው በማለት ያስወሰኑ በመሆኑ ውሳኔው ቀሪ እንዲሆን በማለት የመቃወም አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ…

Previous Article ቻይና ኮሙኒኬሽን ኩባንያ ግንባታ ወንጪ ደንዲ ኢኮቱሪዝም ፕሮጀክት እና ማንዴሳ ጪብሳ የሠ/መ/ቁጥር 256412
Next Article ወ/ሮ ሰላማዊት ያደሳ እነ አቶ ፀሀዬ ጌታቸው(2ሰዎች) የሠ/መ/ቁጥር 256923
Print
5503

Documents to download

  • 256463(.pdf, 853.95 KB) - 557 download(s)

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ...

194

‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር የተቀናጀ አሰራርን በመፍጠር የዳኝነት ስርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል።

ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል...

209

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለነጻ የህግ ድጋፍ የሚሰጡ የበጎ ፈቃድ ጠበቆች፣ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እና ነፃ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት አስተባባሪዎች የልምድ ልውውጥና ተግባር ተኮር የዉይይት ተካሂዷል።

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ...

337

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንትነትና ምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ተገኝተው አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይትና ምልከታ አድርገዋል።

ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ...

359

‎በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት የተሰራ ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል (One way mirror) በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት በይፋ ስራ ጀምሯል።

1345678910Last