Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ሰለሞን አርአያ እናእነ ህፃን ዳንኤል ቴውድሮስ ሞግዚት ወ/ሮ የሺ መንግስቱ(5ሰዎች)የሰ/መ/ቁጥር፡- 255592

ጉዳዩ የውርስ ማጣራትን የሚመለከት ሆኖ አቤቱታው በቀረበበት የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት አመልካች 5ኛ ጣልቃ ገብ ፣ 2ኛ ተጠሪ የስር ተጠሪ፤1ኛ ተጠሪ የስር አመልካች፤  ከ3ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተጠሪዎች ደግሞ 3ኛ፤4ኛ እና 6ኛ ጣ/ገቦች ነበሩ፡፡ የክርክሩ አመጣጥ በአጭሩ፡- የአሁን 1ኛ ተጠሪ  ባቀረቡት አቤቱታ የሟች ባለቤታቸው ቴውድሮስ አርአያ ወላጆች የልጃቸው አያት የሆኑት ጀነራል አርአያ ዘርዓይ ጥር 25 ቀን 2003 ዓም እናቱ ወ/ሮ ሰነዳይ ሀይሌ ጥር 04 ቀን 2004 ዓም ከዚህ አለም በሞት የተለዩ መሆኑን፤ባለቤታቸው ከወንድሞቹና እህቶቹ ጋር በመሆን በ29/08/2005 ዓም ወራሽነታቸውን ያረጋገጡ ቢሆንም ውርሱ ሳይጣራ መኖሪያ ቤቱን ሳይከፋፈሉ በጋራ ይዘው ሲጠቀሙበት ቆይተው ከ2006 ዓም ጀምሮ ቤቱን አከራይተው የኪራዩን ገንዘብ እኩል እየተካፈሉ መሆኑን ገልጠው ድርሻቸውን ለይተው ለማወቅና ለማረጋገጥ እንዲችሉ የውርስ ሀብት እንዲጣራ ጠይቀዋል፡፡ መልካም ንባብ…..

Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ጫላእና አቶ ሸዋንግዛው ሽብሩ/ቁጥር የሰ/መ/ቁ 254862
Next Article አቶ ዮሀንስ ካሳዬ እና የፍትህ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 273594
Print
5797

Documents to download

  • 255592(.pdf, 834.83 KB) - 827 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

የፍርድ ቤቶች አመራሮችና ዳኞች በአርባምንጭ ከተማ የችግኝ...

0

ነሐሴ 03/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተመራ የፍርድ ቤቶች ከፍተኛ አመራሮችና ዳኞች ልዑክ በአርባምንጭ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ ተካሄደ

0

ፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና የጉባኤው ሰብሳቢ ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በመክፈቻ ንግግራቸው፤ በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሠረት የተቋቋመው የፌደራል ጉባኤ የዳኝነት ነፃነትና ገለልተኝነትን የመጠበቅ፣ የአሰራር መመሪያዎችን የማውጣትና የማሻሻል እንዲሁም አገራዊ የዳኝነት ሂደቱን የማጠናከር ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለበት ገልጸዋል።

1345678910Last